እንደ መግቢያ.
ፍጥረታዊው ዓለም የመንፈሳዊው አለም ጥላ ነው:: "አስቀድሞ ፍጥረታዊው ቀጥሎ መንፈሳዊው" እንዲል መጽሓፍ, በእግዚአብሔር ዕቅድና ፕላን መሰረት እኛ የሰው ልጆች ቀድመን የተገኘንበትም ሆነ የተገለጠልን ፍጥረታዊው አለም ነው:: የመጀመሪያው ሰው አዳም በገነት ነበረ ሲባል ብዙዎች የሚያስቡት በሰማይ ወይም በማይታየው መንፈሳዊው አለም ውስጥ ሆኖ ነገር ግን ኃጢአትን ሲያደርግ ከላይ ከሰማይ ወይም ከማይታየው መንፈሳዊ ዓለም ወደዚህ ወደሚታየው ፍጥረታዊው ዓለም እንደወደቀ ነው:: ነገር ግን እውነቱ የመጀመሪያው ስው የተገኘውም የነበረውም በዚሁ ፍጥረታዊው ዓለም ውስጥ ሆኖ የተገኘበትም ዓላማ እግዚአብሐርን እንዲያውቅ ድምጹንም እንዲሰማ ከእርሱም ጋር ፍጹም ሕብረት እንዲኖረውና በፍጹም ጸጥታና ሰላም ውስጥ እንዲኖር... ደግሞም እግዚአብሔር በፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ላይ የበላይ ገዥና አስተዳዳሪ , በዚህ በሚታየው ዓለም ውስጥ የማይታየው እግዚአብሔር መቅደስና መገለጫ, የማይታየውን እግዚአብሔርን ከሚታየው ፍጥረት ጋር የሚያገናኝ ድልድይ...እንዲሆን የነበረ ሲሆን ይህም አዳም የነበረበት ስብዕና (state of being) በራሱ 'ገነት' ይባላል::
ይህ የመጀመሪያው ሰው ሲፈጠር ግን ለዚህ ለተፈጠረበት የእግዚአብሔር ዓላማ ፍጹምና ብቁ ሆኖ አይደለም:: ይልቁንም ወደዚህ ፍጽምናና ብቃት ይደርስ ዘንድ የሚያስችለውንና ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠውን ትዕዛዝ መጠበቅ ነበረበት:: ለዚህም ነው እግዚአብሔር ይህንን ሰው በሕይወትና በሞት መካከል ያስቀመጠው:: ይህም ምርጫ በሁለቱ ዛፍ ተምሳሌትነት (symbol) የተገለጠ ነው:: ስለዚህ ይህ ሰው በሰይጣን ተፈትኖ በኃጢአትና በአለመታዘዝ ሲገኝ ይህንን ስብዕናውን አጣ:: በዚህ ፍጥረታዊ ዓለም ውስጥ በመንፋሳዊው ብርሓን ይመላለስ የነበረው ሰው ራሱን በመንፈሳዊ ጨለማ ውስጥ አገኘ:: "ኃጢአት" የሚለው የአማርኛችን ቃል ትርጉምም ከምንፈጽማቸው "የሥጋ ስራ" ባለፈ መልኩ "ብርሃን" የተባለውን እግዚአብሔርን አጥተንና ከእርሱም ተለይተን የምንገፋውን የጨለማ ኑሮ ሁሉ የሚያካትት ነው:: "Hamartia" የሚለውም የግሪኩ ቃል Missing the mark ወይም Mistaken identity ተብሎም ይተረጎማል::
መንፈሳዊው ጨለማ የእግዚአብሔር አለመኖር (the absence of God) ሲሆን እግዚአብሔር የሌለው ግን ለወደቀው ሰው አእምሮና መረዳት እንጂ እግዚአብሔርስ ለአንዲት ሰከንድ እንኩዋን ከፈጠረው ፍጥረት ተለይቶ አያውቅም:: ሕያዋን ሆነን የምንንቀሳቀሰው በማን ሆነና!! (ሥራ 17:22-31)
"ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛ ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር:: በዓለም ነበረ: ዓለሙም በእርሱ ሆነ: ዓለሙም አላወቀውም:: የእርሱ ወደሆነው መጣ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም:: ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከስጋ ፍቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም "
(ዮሃ 1:9-13)
በአዳም ኃጢአትና መተላለፍ ምክንያት አጥተነው የነበረውና እግዚአብሔር ለእኛና በእኛ በሰው ልጆች ያለው የከበረ ዓላማ፣ ምሥጢሩ ሁሉ የተቋጠረው በክርስቶስ ነው:: የክርስቶስ መገለጥ ደግሞ የዚህ የእግዚአብሔር የዘመናት ምሥጢር መገለጥ ነው:: ይህም የእግዚአብሔር ምሥጢር - ክርስቶስ በእኛ ሕይወት ይገለጥ ዘንድ፣ በእርሱም ያለው የእግዚአብሔር ዓላማ በእያንዳንዳችን ሕይወት ፍጻሜውን ያገኝ ዘንድ ጅማሬውና መሠረቱ፣ እርሱ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ በማመን ከእግዚአብሔር መወለዳችን ነው:: በዚህ በሚታየውና ለመንፈሳዊው ዓለም ጥላ በሆነው ፍጥረታዊው ዓለም ውስጥ እንደምናየው ደግሞ የተወለደ ሁሉ ያድጋል:: "የመናፍስት አባት" ከተባለው ከእግዚአብሔር የተወለድን እኛማ እንዴት!!! በዚህ "ሦስቱ የመንፈሳዊ ሕይወት እድገት ደረጃዎች" በሚለው ርዕስ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጆች የተባልን እኛ እግዚአብሔር በልጁ ወዳዘጋጀልን የከበረ ሕይወት እስክንደርስ ድረስ የምናልፍባቸውን የመንፈሳዊ ሕይወት እድገት ደረጃዎች በሦስት ከፍለን እናያቸዋለን::

No comments:
Post a Comment