በአዳም አለመታዘዝ ምክንያት በፊቱ ወዝ - በጉልበቱ ድካም ፣ ካለው በዋጋ ገዝቶ፣ ከሌለው እጁን ዘርግቶ ለሥጋው የሚሆነውን የዕለት እንጀራ እንዲበላ በእግዚአብሔር ተረግሞ የነበረው ሰው፤ “የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነው” ወደተባለለት አምላኩ ቀርቦ፣ እንዲያው - በነፃ - ያለምንም ዋጋና ክፍያ፣ ከሕይወት ውሃና እንጀራ በልቶና ጠጥቶ የተራበች ነፍሱን ያጠግብ ዘንድ መንገዱ የትኛው ነው?? አለመታዘዝና ውድቀት ያለበሰውን መንፈሳዊ ጉስቁልና - የኃጢአትና የዓመጽ ድሪቶ አውልቆ የጽድቅና የክብር ሸማ የሚለብሰውስ ምን ቢያደርግ ነው?? ሰው ከሞትና ከሲዖል የሚያመልጥበት መንገዱ ስንት ነው??....
ለእነዚህ ጥያቄዎች የማያዳግም መልስ የሰጠው እግዚአብሔር፣ በአንድያ ልጁ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል የገለጠውን ብቸኛ የጽድቅና የሕይወት መንገድ የሚቃወመውና የሚያጣምመው ዲያብሎስ፣ በአገልጋዩ በሐይማኖት በኩል ለሰዎች ብዙ ሐሰተኛ ምርጫዎችን አቅርቦላቸዋል። መልካም ሥራ ቢሰሩ - ቢጾሙ ቢጸልዩ፣ ለድሆች ቢሰጡ፣ በቀን አምስት ወይም ሰባት ጊዜ ቢጸልዩና ቢሰግዱ፣ ልዩ ልዩ "መንፈሳዊ ስፍራዎችን" ቢጎበኙ፣ ከሰዎች ርቀው ከአውሬ ጋር በጫካ ቢኖሩ - ገዳም ገብተው ቅጠል ከበሉና ጥሬ ከቆረጠሙ፣…. ወደ ጽድቅ በሚወስደው መንገድ ላይ ስለመሆናቸው አንዳች እንዳይጠራጠሩ ነግሮአቸዋል። ደግሞም ሰው ሁሉ ደካማ አይደለምና ከእርሱ ይልቅ የበረቱትን “ጻድቃን - ሰማዕታት”፣ ለእግዚአብሔር ቅርብ የሆነችውን “ወላዲተ አምላክ”፣ ወይም ቅዱሳን መላዕክቱን… እነርሱን በግንባር ማግኘት ስለማይቻል “ይህን ሊመስሉ ይችላሉ” ብሎ ለቀባው ሰዕላቸው “የአክብሮት ስግደት” እየሰገደ ቢለማመን… “በዕለተ ቀናቸው” ወይም “በበዐለ ንግሣቸው”፤ ጧፍ ዣንጥላውን፣ ዕጣን ዘቢቡን… ስዕለት መሥዋዕት አድርጎ ቢያቀርብ፣ ድግስ ደግሶ ቢያበላ ቢያጠጣ፤ …. ችግሩን ለእግዚአብሔር ነግረው፣ ወደ ሕይወት የሚያስገባውን በር እንደሚያስከፍቱለት አስተምሮአቸዋል። ….. እነዚህ ሁሉ ግን ሐይማኖት የጠረጋቸው የሲዖል መንገዶች ናቸው።
“በታች ካለው ከሲዖል ያመልጥ ዘንድ፣ የሕይወት መንገድ አስተዋዩን ሰው ወደላይ ይወስደዋል።” (ምሳሌ 15፡24)
አዳም ባለመታዘዝ ሲወድቅ፣ ከሕይወት ዛፍ ወስዶ እንዳይበላና በኃጢአት በተበላሸው በዚያ ማንነቱ ለዘላለምም ሕያው ሆኖ እንዳይኖር እግዚአብሔር ወደሕይወት ዛፍ የሚወስደውን መንገድ በኪሩቤልና በምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍ ዘግቶት ነበር። ከዚህም የተነሳ ሰው ከአምላኩ ተለይቶ በመንፈሱ ሞተ፤ ነፍሱም እረፍትና ሰላም ያጣች ተቅበዝባዥ ሆነች፣ ሰውነቱም በተለያዩ ጥቃቅን ተሐዋስያን የሚጠቃና በደዌ የሚማቅቅ አቅመ ቢስ እየሆነ፣ በእርጅና እየደከመና እየጎበጠ ወደተገኘበት አፈር መመለስ ጀመረ። ከእግዚአብሔር በተወሰነለት የጽድቅና የሕይወት መንገድ ላይ ሳይሆን፣ ዓመጽና ኃጢአት በሞላበት የሞትና የሲዖል መንገድ ላይ ራሱን አገኘ። ነቢዩ ኢሳይያስ ይህን ሁኔታ “እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፣ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ….” በማለት ገልጦታል።
ሰው ዬትኛውንም ዓይነት ብልሐትና ጥበብ፣ ጉልበትና ኃይል.... ቢጠቀም፣ በምድር ላይ ያሉትን እንሰሳት ሁሉ መሥዋዕት አድርጎ ቢያቀርብ፣ በቀን ውስጥ የቻለውን ያህል ሲሰግድና ሲለማመን ቢውል፣.... የማንም ልመናና ጸሎት፣ ምልጃና ዕንባ… እግዚአብሔር የዘጋውን ይህን የሕይወት መንገድ ሊያስከፍት አይችልም። እግዚአብሔር የዘጋውን ማን ሊከፍተው ይችላል?? ታድያ እርሱ ይህን ወደሕይወት ዛፍ የሚወስደውን መንገድ የዘጋው እስከወዲያኛው ላይከፍተው ነበር?? ሰውስ ወደቀደመው ክብሩ የሚመለስበት ተስፋ የለውም?? የሰው ልጅ አሁን በሚኖርበት የሐዘንና ሰቆቃ፣ የጉስቁልናና የስቃይ ኑሮ፤ በጨለማው ገዢ የባርነት ቀንበር ስር እየማቀቀ ዘመኑን አንዲገፋ ለዘላለም ተፈርዶበታል?? ..... በጭራሽ!! እንዲህ ዓይነቱ ጭካኔ ከእግዚአብሔር ይራቅ!!
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዐለሙን እንዲሁ ወዶአልና” (ዮሃ.3፡16)
“እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደሰጠን፣ ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው። ልጁ ያለው ሕይወት አለው፣ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።” (1ዮሃ.5፡11-12)

የዛሬ 2000 ዓመት አካባቢ፣ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ለመስቀል ሞት አሳልፎ ሲሰጥ፣ በአዳም አለመታዘዝ ሰበብ በኪሩቤልና በምትገለባበጥ ሰይፍ ተጠብቆ ወይም ተዘግቶ የነበረውና ወደሕይወት ዛፍ የሚወስደው መንገድ ለሰው፣ ይልቁንም ለሚያምኑ ሁሉ እንደተከፈተ የተረዳን ስንቶች ነን?? ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ መስቀል ላይ የመጨረሻ ትንፋሹን ተንፍሶ እና በታላቅ ድምጽ “ተፈጸመ” በማለት ጮሆ ነፍሱን ሲሰጥ፣ በኢየሩሳሌም ምድር እጅግ አስገራሚ ነገር ሆነ፤ ….. ፀሐይ ጨለመች፣ የቤተ መቅደሱም መጋረጃ ከመካከሉ ተቀደደ። የዚህ መጋረጃ መቀደድ ተምሳሌትነቱ፣ በአዳም በደል ምክንያት በሰዎችና በእግዚአብሔር መካከል የነበረው የጥል ግድግዳ መፍረሱና፣ ሰዎች ሁሉ በክርስቶሰ ኢየሱስ ባለ እምነት በኩል ወደ እግዚአብሔር እየቀረቡ ከሕይወት ምንጭ እንዲያው - በነፃ የሚጠጡበት፣ ከሕይወት እንጀራም የተራበች ነፍሳቸውን የሚያጠግቡበት መንገድ መከፈቱ ነው።
“እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” (ዮሃ.14፡6)
እግዚአብሔር የዛሬ 2000 ዓመት አካባቢ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውን ይህን አንድና ብቸኛ መንገድ ከገለጠበት ጊዜ ጀምሮ፣ የጽድቅና የሕይወት ጠላት የሆነው ዲያብሎስ፣ ሲችል ይህን ብቸኛ የሕይወት መንገድ በግልጽ እየዘጋና እየተቃወመ፣ ሳይችል ደግሞ ሌላ አማራጭና ሐሰተኛ መንገዶችን እያቀረበ፣ እግዚአብሔር በልጁ በኩል እንዲሁ - በእምነት ብቻ ከሰጣቸው ሕይወት ሰዎችን ለማሳትና ለማጉደል የተጠቀመው ፖለቲካን ወይም ኢኮኖሚን ብቻ ሳይሆን፣ በተለይም ሐይማኖትን ነው። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ የቀደደውን መጋረጃ በትምሕርቶቻቸው መልሰው የሰፉ፣ እርሱ በሥጋው ያፈረሰውን የጥል ግድግዳ በተረቶቻቸው መልሰው የገነቡ የፖለቲካ ካድሬዎች ሳይሆኑ የሐይማኖት መሪዎችና አስተማሪዎች ናቸው። ዛሬ ግን ዘመን መጣ!! ሓይማኖት በሰዎች አዕምሮ ላይ የጣለውን መጋረጃ እግዚአብሔር በመንፈሱ ኃይልና በቃሉ ሥልጣን እየገፈፈ ነው!! ለሰው ልጆች የሰጠውም ብቸኛው ሕይወትና የሕይወት መንገድ፣ እርሱም ክርስቶስና ጌታ የሆነው የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ፣ ስሙ በኢትዮጵያ ሰማያት ላይ እያስተጋባ ነው!! ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!!!!!!
No comments:
Post a Comment