by Tibebe Belay ·
በቀደመው ኪዳን ይቀርቡ የነበሩ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቁርባን፣ የኃጢአትና የበደል መሥወዕት እንዲሁም የቅድስናና የደህንነት መሥወዕቶች ሁሉ፣ ምሳሌነታቸው ይመጣ ስላለው የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር። የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት አካባቢ ወደ ምድር የመጣበትን የአባቱን ዓላማና ፈቃድ ለመፈጸም ልክ በሠላሳ ዐመቱ በሰዎች መካከል በይፋ በተገለጠበት ጊዜ፣ በመንገድ ጠራጊው በዮሃንስ በኩል የመጣው የእግዚአብሔር ምስክር “እነሆ የዓለምን ሁሉ ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ!” የሚል ነበር። ለሦስት ዓመት ተኩል ያህልም በእርሱ በነበረው የእግዚአብሔር መንፈስ “መልካም እያደረገና ለዲያብሎስ የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ” የእግዚአብሔርን መንግሥት ከሰበከ በህዋላ፤ በተካፈለው ሥጋና ደም በኩል ከሰይጣንና ከዚህ ክፉ ዓለም የመጣበትን ፈተና ሁሉ አሸንፎ በፍጹም ቅድስና የጠበቀውን ነውርና ዕድፍ የሌለውን ራሱን ለዓለም ሁሉ የሚሆን የኃጢአትና የበደል መሥዋዕት አድርጎ በመስቀል ላይ አቀረበ። አባቱም ይህንን ቅዱስና ሕያው መሥዋዕት ተቀበለ። የዓለምን ሁሉ ኃጢአትና በደልም በእርሱ ላይ አኖረ። ስለዚህም በአዳም በደል ምክንያት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ገብቶ የነበረው ጠላትነት በክርስቶስ ሞት ተወግዶ መታረቅ ሆነ። “… እግዚአብሔርም በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፣ በደላቸውንም አይቆጥርባቸውም ነበር፤….” (2ቆሮ. 5፡19)
አለማወቃቸው ነው እንጂ፤ እግዚአብሔር ዘር፣ቀለም፣ ጾታ፣ ሐይማኖት…. ሳይለይ፣ በየትኛውም ዓለም - በማንኛውም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ የሰው ልጆችይቅርታንና ምሕረትን አድርጎአል። ነገር ግን ኃጢአትን በተመለከተ በክርስቶስ ኢየሱስ የተገለጠው የእግዚአብሔር ዓላማ ይቅርታ ማድረግ ብቻ አይደለም። ማዳንም ነው!!! ሰዎች የኃጢአት ይቅርታ ማግኘት ብቻ ሳይሆን፣ ከኃጢአት ኃይልና ሕግ ነጻ መውጣት ይኖርባቸዋል። ከኃጢአት መዳን የሚባለውም ይሀ ነው። ከኃጢአት መዳን ማለት ደግሞ ከሞት መዳንም ማለት ነው። ለዚህም ነው በሞቱ ዓለሙን ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ያስታረቀው ብቻ ሳይሆን በሕይወቱ የሚያምኑትን ሁሉ የሚያድነው መሲሕ ገና ከመጸነሱ እንዲህ የሚል የምሥራች በመላእክት አንደበት ለዮሴፍ የተነገረው፡- “እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።” (ማቴ.1፡21)
የኃጢአት ይቅርታ በማግኘትና ከኃጢአት በመዳን መካከል ያለውን ልዩነት ለመረዳት፣ በተለይ ሐዋርያው ጳውሎስ ለሮሜ ክርስቲያኖች የጻፋቸውን የመጀመሪዎቹን ስምንት ምዕራፎች በጸሎትና (እግዚአብሔር በመንፈሱ እንዲያስተምረን) በጽሞና ሆነን ማጥናት ያስፈልጋል። ይህን መልዕክት በጥንቃቄ ስናጠና፣ በመልዕክቱ ውስጥ “ኃጢአት” የሚለው ቃል በሁለት መልኩ ተገልጦ እናገኘዋለን። የመጀመሪያው በእግዚአብሔር ፊት የተደረገ በደል ወይም በድርጊት የተፈጸመ ኃጢአትን (Committed Sin) የሚመለከት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ሰዎች ይህን በደልና ኃጢአት ይፈጽሙ ዘንድ በውስጣቸው ሆኖ የሚያነሳሳቸውን የኃጢአት ሕግ (The principle or the law of sin) የሚመለከት ነው። ማንኛውም ከሥጋና ከደም የተወለደ ሰው ሁሉ ወደዚህ ዓለም የሚገባው ከዚህ የኃጢአት ሕግ ጋር ነው። ለዚህም ነው ንጉሡ ዳዊት “እነሆ በዓመፃ ተጸነስሁ፣ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ” በማለት ይህን እውነት አስቀድሞ የገለጸው። ወንድሞቼ፣ ሰው ከፊተኛው አዳም የተካፈለውን ይህን የኃጢአት ሕግ ከሆነ “የውርስ ኃጢአት” የሚል ስም የሰጡት፤ ሰው ሁሉ ክርስቶስ ኢየሱስ በቀራንዮ መስቀል ላይ በከፈለው ዋጋ ወይም ደግሞ እነርሱ እንደሚያምኑት በሕጻንነቱ ሲጠመቅ ከዚህ “የውርስ ኃጢአት” አልዳነም - አይድንምም። ይህን እውነት በቅጡ ለመረዳት ከላይ በሁለት መልኩ የከፈልነውን ሀሳብ አንድ በአንድ እንመልከት፡-
1. በእግዚአብሔር ፊት የተደረገ በደል ወይም በድርጊት የተፈጸመ ኃጢአት (Committed sin)
“ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና፣ የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤“ (ሮሜ.3፡23)
ሰው በአዳም አለመታዘዝ ምክንያት ከእግዚአብሔር ከተለየበት ማለዳ ጀምሮ ነው ዓመጽን መለማመድ የጀመረው። ይህም በአዳም የበኩር ልጅ በቃየን የተገለጠ ነው። እኔ ገና ከሕጻንነቴ ጀምሮ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ የሰራሁትን በደልና ኃጢአት ልቆጥረው አልችልም። ይሄ ጉዳይ ደግሞ የእኔ ብቻ ሳይሆን፣ ከስጋና ከደም በመወለድ ወደዚህ ዓለም የመጡ የሰው ልጆች ሁሉ ታሪክ ነው። በእግዚአብሔር ፊት የፈጸምነውና እየፈጸምን ያለነው በደል፣ የተለማመድነውም ኃጢአት አይነቱ የአንዳችን ከአንዳችን ቢለያይም ያው ሁሉም ዓመጽ፣ ሁላችንም አመጸኞች ነን። በውጭ ሲታዩ የመላእክት ልጆች የሚመስሉት የሐይማኖት አባቶችም ሆኑ፣ ሰዎች ሁሉ እያዩት በመንገድ ላይ የሚወላገደው ሰካራም ያው ኃጢአተኞች ናቸው። ሐይማኖት የፈጠረውን ግብረ-ገብ ከልጅነቱ ጀምሮ እየፈጸመ ያደገው “የሞራል ስው” እና ወላጆቹ ሲያደርጉ ያየውን ዛፍና ወንዝ እያመለከ ያደገውም ብላቴና በእግዚአብሔር ፊት በደለኞች ናቸው። ያኔ በክርስቶስ ፊት ሊወግሩዋት ድንጋይ ተሸክመው የመጡት ሐይማኖተኞችም ሆኑ፣ በምንዝር የተያዘችው ያቺ ሴት…. ሁሉም ኃጢአትን በመሥራታቸው የእግዚአብሔር ክብር የጎደላቸው የአዳም ዘሮች ናቸው። ስለዚህ “እግዚአብሔር ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን ከኃጢአት በታች ዘግቶታል” (ሮሜ.11፡32)
ታድያ፤ እግዚአብሔር ሁሉን የማረው፣ በዘመናት መካከል ሰዎች የፈጸሙትን በደል ሁሉ እንዳልፈጸሙት አድርጎ የቆጠረው፣ የተወው፣ የረሳው …. በቀራንዮ መስቀል ላይ በቀረበው የኃጢአትና የበደል መሥዋዕት፣ ጌታ የኢየሱስ ክርስቶሰ በከፈለው ውድ ዋጋ…. ነው። ከእንግዲህ ሰዎች ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቃቸውን ይወቁ!! በእነርሱና በእግዚአብሔር መካከል የነበረው የጥል ግድግዳ በመስቀሉ ደም እንደፈረሰ ይመኑ!!! ከምሕረቱና ከጸጋው ባለጠግነት ይጠግቡ ዘንድ በክርስቶስ በሆነው ቤዛነት በኩል እየቀረቡ “የእግዚአብሔርን ጽድቅ” ይቀበሉ!!! በፊት ያደረጉትን ኃጢአት ሁሉ ይቅር ብሎ፣ በደላቸውን ላይቆጥር እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም አዲስ ኪዳን አድረጎአልና!!!!!!
“ሁሉ ኃጢአትን ሰርተዋልና፣ የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ። እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስረያ አድርጎ አቆመው፤ ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ስለመተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፤” (ሮሜ.3፡23-25)

No comments:
Post a Comment