by Tibebe Belay on Saturday, June 2, 2012 at 10:55am ·
በበዓለ
ኀምሳ በተቀበሉት ቅዱሱ የእግዚአብሔር መንፈስ ኣማካኝነት ሐዋርያት አገልግሎታቸውን ‘ሀ’ ብለው የጀመሩት፣
በየዕለቱ ሰዎች እየተሸከሙ በቤተ መቅደሰ ደጅ ያስቀምጡት የነበረውንና ከእናቱ ማኅጸን ጀምሮ አንካሳ የነበረውን ሰው
በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በመፈወስ ነበር። ይህን ‘ድውይ’ እንዴት ሊፈውሱት እንደቻሉ ለጠየቁዋቸውም የሕዝብ
አለቆችና ሽማግሌዎች በጊዜው የመለሱት መልስም ቀጥተኛና ግልጽ ነበር፡- “እናንተ በሰቀላችሁት፣ እግዚአብሔርም
ከሙታን ባስነሳው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም…. መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን
ለሰዎች የተስጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” (ሥራ.4፡7-12)
ሐዋርያው ጳወሎስም ሰው ሁሉ ኃጢአት ካመጣው የሞት ፍርድ እየዳነ የእግዚአብሔርን ጽድቅ የሚቀበልበትን መንገድ ለሮሜ ሰዎች በጻፈው መልዕክቱ ውስጥ ተመሳሳይ በሆነ ግልጽና ቀጥተኛ በሆነ መንገድ ነበር የገለጸው፡- “ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር፣ እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና፣ በአፉም መስክሮ ይድናልና።” (ሮሜ.10፡9-10)
የሰዎችን መዳንና ወደእግዚአብሔር መመለስ የማይፈልገው ጠላት ዲያብሎስ፣ ሰዎች ይህን ብቸኛ ስም እንዳይጠሩ - ጠርተውም እንዳይፈወሱ የሚጠቀምበት ስልቱ በየዘመናቱ የተለያየ ነው። ለምሳሌ ገና ከጅምሩ ሐዋርያቱን ለማስቆም የሞከረበት ስልቱ ዛቻና ማስፈራራት ነበር። “በነዚህ ሰዎች ምን እንሥራ? የታወቀ ምልክት በእነርሱ እጅ እንደተደረገ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሁሉ ተገልጦአልና፣ ልንሸሽገውም ዘንድ አንችልም፤ ነገር ግን በሕዝቡ ዘንድ እንዳይስፋፋ ከእንግዲህ ወዲህ ለማንም ሰው በዚህ ስም እንዳይናገሩ እየዛትን እንዘዛቸው። ጠርተውም በኢየሱስ ስም ፈጽመው እንዳይናገሩና እንዳያስተምሩ አዘዙአቸው።” (ሥራ.4፡16-18)
በአገራችን ኢትዮጵያ ለዘመናት ከተሰበከው “ልዩ ወንጌል” የተነሳ፣ በተለያዩ እንግዳ ትምሕርቶች ተሸፍኖ የነበረው ይህ አንድና ብቸኛ ስም መገለጥና መሰበክ የጀመረው ከጥቂት አሥርት አመታት በፊት ነበር። “ኢየሱስ ያድናል! መዳን በሌላ በማንም የለም!...” የሚሉ ወገኖች በምድሪቱ ላይ ብቅ-ብቅ ማለት ሲጀምሩ፣ ጠላት የተለመደ ዛቻና ማስፈራራቱን ጀመረ። “በሰንዴና በዘይት ወደአገራችን ከገባው ከዚህ መጤና ሰልባጅ ሐይማኖት ልጆቻችሁን ጠብቁ!... ” እየተባለ በየአውደ ምሕረቱ ሲሰበክ፣ በየዕድሩ ማስጠንቀቂያ ሲነገር… በተቃራኒው ግን “ኢየሱስ ያድናል!!” የሚለው የምሥራች በዚህም በዚያም ያስተጋባ ነበር።
ዛሬ ጠላት ይህን አንድና ብቸኛ የሆነውን ስም የሚሸፍንበት ስልቱን ፈጽሞ ቀይሮአል። አሁን ዛቻና ማስፈራራቱ ወደ ማደናገርና ማወናበድ ተለውጦአል። “ኢየሱስ ያድናል!! መዳን በሌላ በማንም የለም!!... ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር፣ እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህ” የሚለውን ግልጽና ቀጥተኛ ወንጌል፣ “አርሱ እግዚአብሔር ነው አይደለም?? አማላጅ ነው ወይስ ተማላጅ?? ከአብና ከወልድ ማን ይበልጣል??... “ በሚሉ ጥያቄ መሰል ማደናበሪያ ቃላት ይሸፍንና ወንድሞችን ማለቂያ ወደሌለው ሙግት ውስጥ ይከታቸዋል። አላማውም ሰዎች “ኢየሱስ እርሱም ክርሰቶስና ጌታ እንደሆነ በአፋቸው እነዳይመሰክሩ - መስክረውም እንዳይድኑ፤ እግዚአብሔርም ከሙታና እንዳስነሳው በልባቸው እንዳያምኑ - አምነውም እንዳይጸድቁ ነውና የተሳካለት ይመስላል። ነገር ግን ይህ ስኬቱ ለጊዜው ነው። የወንጌሉ ብርሐን በጨለማው የሰዎች ልብ ውስጥ ይበራል። ጉልበት ሁሉ በኢየሱሰ ስም ይንበረከካል!!! መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክራል!!!!!!!

No comments:
Post a Comment