Friday, June 29, 2012

ሦስቱ የመንፈሳዊ ሕይወት እድገት ደረጃዎች!! (ክፍል 1)

እንደ መግቢያ.

ፍጥረታዊው ዓለም የመንፈሳዊው አለም ጥላ ነው:: "አስቀድሞ ፍጥረታዊው ቀጥሎ መንፈሳዊው" እንዲል መጽሓፍ, በእግዚአብሔር ዕቅድና ፕላን መሰረት እኛ የሰው ልጆች ቀድመን የተገኘንበትም ሆነ የተገለጠልን ፍጥረታዊው አለም ነው:: የመጀመሪያው ሰው አዳም በገነት ነበረ ሲባል ብዙዎች የሚያስቡት በሰማይ ወይም በማይታየው መንፈሳዊው አለም ውስጥ ሆኖ ነገር ግን ኃጢአትን ሲያደርግ ከላይ ከሰማይ ወይም ከማይታየው መንፈሳዊ ዓለም ወደዚህ ወደሚታየው ፍጥረታዊው ዓለም እንደወደቀ ነው:: ነገር ግን እውነቱ የመጀመሪያው ስው የተገኘውም የነበረውም በዚሁ ፍጥረታዊው ዓለም ውስጥ ሆኖ የተገኘበትም ዓላማ እግዚአብሐርን እንዲያውቅ ድምጹንም እንዲሰማ ከእርሱም ጋር ፍጹም ሕብረት እንዲኖረውና በፍጹም ጸጥታና ሰላም ውስጥ እንዲኖር... ደግሞም እግዚአብሔር በፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ላይ የበላይ ገዥና አስተዳዳሪ , በዚህ በሚታየው ዓለም ውስጥ የማይታየው እግዚአብሔር መቅደስና መገለጫ, የማይታየውን እግዚአብሔርን ከሚታየው ፍጥረት ጋር የሚያገናኝ ድልድይ...እንዲሆን የነበረ ሲሆን ይህም አዳም የነበረበት ስብዕና (state of being) በራሱ 'ገነት' ይባላል::

ይህ የመጀመሪያው ሰው ሲፈጠር ግን ለዚህ ለተፈጠረበት የእግዚአብሔር ዓላማ ፍጹምና ብቁ ሆኖ አይደለም:: ይልቁንም ወደዚህ ፍጽምናና ብቃት ይደርስ ዘንድ የሚያስችለውንና ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠውን ትዕዛዝ መጠበቅ ነበረበት:: ለዚህም ነው እግዚአብሔር ይህንን ሰው በሕይወትና በሞት መካከል ያስቀመጠው:: ይህም ምርጫ በሁለቱ ዛፍ ተምሳሌትነት (symbol) የተገለጠ ነው:: ስለዚህ ይህ ሰው በሰይጣን ተፈትኖ በኃጢአትና በአለመታዘዝ ሲገኝ ይህንን ስብዕናውን አጣ:: በዚህ ፍጥረታዊ ዓለም ውስጥ በመንፋሳዊው ብርሓን ይመላለስ የነበረው ሰው ራሱን በመንፈሳዊ ጨለማ ውስጥ አገኘ:: "ኃጢአት" የሚለው  የአማርኛችን ቃል ትርጉምም ከምንፈጽማቸው "የሥጋ ስራ" ባለፈ መልኩ "ብርሃን" የተባለውን እግዚአብሔርን አጥተንና ከእርሱም ተለይተን የምንገፋውን የጨለማ ኑሮ ሁሉ የሚያካትት ነው:: "Hamartia" የሚለውም የግሪኩ ቃል Missing the mark ወይም Mistaken identity ተብሎም ይተረጎማል::

መንፈሳዊው ጨለማ የእግዚአብሔር አለመኖር (the absence of God) ሲሆን እግዚአብሔር የሌለው ግን ለወደቀው ሰው አእምሮና መረዳት እንጂ እግዚአብሔርስ ለአንዲት ሰከንድ እንኩዋን ከፈጠረው ፍጥረት ተለይቶ አያውቅም:: ሕያዋን ሆነን የምንንቀሳቀሰው በማን ሆነና!! (ሥራ 17:22-31)
"ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛ ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር:: በዓለም ነበረ: ዓለሙም በእርሱ ሆነ: ዓለሙም አላወቀውም:: የእርሱ ወደሆነው መጣ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም:: ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከስጋ ፍቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም "
(ዮሃ 1:9-13)

በአዳም ኃጢአትና መተላለፍ ምክንያት አጥተነው የነበረውና እግዚአብሔር ለእኛና በእኛ በሰው ልጆች ያለው የከበረ ዓላማ፣ ምሥጢሩ ሁሉ የተቋጠረው በክርስቶስ ነው:: የክርስቶስ መገለጥ ደግሞ የዚህ የእግዚአብሔር የዘመናት ምሥጢር መገለጥ ነው:: ይህም የእግዚአብሔር ምሥጢር - ክርስቶስ በእኛ ሕይወት ይገለጥ ዘንድ፣ በእርሱም ያለው የእግዚአብሔር ዓላማ በእያንዳንዳችን ሕይወት ፍጻሜውን ያገኝ ዘንድ ጅማሬውና መሠረቱ፣ እርሱ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ በማመን ከእግዚአብሔር መወለዳችን ነው:: በዚህ በሚታየውና ለመንፈሳዊው ዓለም ጥላ በሆነው ፍጥረታዊው ዓለም ውስጥ እንደምናየው ደግሞ የተወለደ ሁሉ ያድጋል:: "የመናፍስት አባት" ከተባለው ከእግዚአብሔር የተወለድን እኛማ እንዴት!!! በዚህ "ሦስቱ የመንፈሳዊ ሕይወት እድገት ደረጃዎች" በሚለው ርዕስ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጆች የተባልን እኛ እግዚአብሔር በልጁ ወዳዘጋጀልን የከበረ ሕይወት እስክንደርስ ድረስ የምናልፍባቸውን የመንፈሳዊ ሕይወት እድገት ደረጃዎች በሦስት ከፍለን እናያቸዋለን::    

ሦስቱ የመንፈሳዊ ሕይወት እድገት ደረጃዎች! (ክፍል 2)

"ልጆች ሆይ ኃጢአታችሁ ስለስሙ ተሰርዮላችኋልና ይህን እጽፍላችኋለሁ: አባቶች ሆይ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ: ጎበዞች ሆይ ክፉውን አሸንፋችኋልና እጽፍላችኋለሁ..." 1ዮሓ 2:12-13

በእግዚአብሔር ዘላለማዊ እቅድና ሓሳብ መሰረት በፍጥረታዊው አለም መገኘታችንና በዚህም ዓለም ያለውን ፍጥረታዊ ህይወት መለማመዳችን (ፍጥረታዊው ሕይወት  ኃጢአትና አመጽ የሞላበት የጨለማ ሕይወት እንዳልሆነ ልብ ይሏል) ወደ መንፈሳዊውና ሰማያዊው ሕይወት ለመድረስ ለምናደርገው መንፈሳዊ ጉዞ እንደ ምሳሌና ማስረጃ ነው:: አንድ ሰው - ሙሉ ሰው ሆኖ በዚህ ምድር ላይ መንቀሳቀስ ከመጀመሩ በፊት የአባቱ ዘርና የእናቱ እንቁላል በእናቱ ማሕጸን ውስጥ ከተገናኙ በሗላ የሚከናወነው የጽንስ ሂደት ደግሞም መወለዱና ማደጉ የሚነግሩንና የሚያስተምሩን የጠለቀ መንፈሳዊ እውነታ አለ::

=>"ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም; በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ::" (1ጴጥ.1:23);
=>"ለፍጥረቱ የበኩራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን" (ያዕ1:18)
=>"ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው, እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከስጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም::" (ዮሓ1:12-13)
=>"ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል:" (1ዮሓ5:1)

በነዚህ የተባረኩ ሐዋርያዊ ትምህርቶች መሰረት, ወደዚህ ፍጥረታዊ ዓለም ከሥጋና ከደም የተወለደ አንድ ሰው፣ ወደመንፈሳዊው ዓለም - ከእግዚአብሔርዳግመኛ ይወለድ ዘንድ አስፈላጊና መሰረታዊ የሆኑ ሁለት "ነገሮችን" እናገኛለን:: "የማይጠፋው ዘር"የተባለው የእግዚአብሔር ቃልና እና እምነት:: "እምነት ከመስማት - መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው፣" በመንፈስ የሚገለገለውንና "የመዳናችሁ ወንጌል" የተባለውን "የእውነት ቃል" በእምነት መቀበላችን ነው ከእግዚአብሐር ዳግመኛ የሚወልደን:: የዚህን ህያው እውነት መሰረት የምናገኘው ደግሞ የእምነት አባት ከተባለው አብርሃምና ትውልድ ሁሉ ብጽዕናዋን ከሚመሰክርላት ድንግሊቱ ማርያም ሕይወት ነው::

የሣራ ማህጸን ደርቋል; የእርሱም ጉልበት ደክሟል:: ነገር ግን አብርሃም, የተሰጠውን ተስፋ, የመጣለትንም የእግዚአብሐር ቃል በእምነት ይዞ ሲበረታ በራዕይ የመጣለትና "ወደ ሰማይ ተመልከት ከዋክብትንም ልትቆጥራቸው ትችል እንደሆነ ቁጠር - ዘርህም እንዲህ ይሆናል::"  የሚለው የእግዚአብሔር ቃል ሥጋ ሆነ!! የተጠበቀውም የተስፋው ዘር ተወለደ::

ለአንድ ወንድ ታጨች እንጂ ወንድ ፈጽሞ አልደረሰባትም: ማሕጸኗም አልተከፈተም - ድንግል ነች:: ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርስዋ ገብቶ "ማርያም ሆይ, በእግዚአብሔር ፊት ጸጋን አግኝተሻልና አትፍሪ:: እነሆም ትጸንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ..." የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል አመጣላት:: አንድ ጥያቄ ነው የጠየቀችው: "ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል?" "መንፈስ ቅዱስ ባንቺ ላይ ይመጣል, የልኡሉም ኃይል ይጸልልሻል.." የመልአኩ መልስ ነበር:: ከዚያም "እነሆኝ የጌታ ባርያ እንደቃልህ ይሁንልኝ" ብላ የመጣላትን ቃል በእምነት ስትቀበል ለዘመናት ሲጠበቅ የነበረው የተስፋው ዘር, አለማት የተፈጠሩበት የእግዚአብሔር ቃል በድንግሊቱ ማሕጸን ውስጥ ሥጋ ሆነ- ጊዜውም ሲደርስ አዳኙ ተወለደ::

በዓለም ሁሉ - በዘመናት መካከል የሚሰበከውና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሚገለገለው የመዳናችን ወንጌል የሆነው ክርስቶስ - የእግዚአብሔር ቃል - ዘር ነው:: እርሱ ኃጢአታችንን በደሙ ያነጻ በሞቱም ከአብ ጋር ያስታረቀን በትንሳኤውም የሞትን መውጊያ የሰበረ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ የሚሰበከውን የወንጌል ቃል በእምነት በተቀበልን ጊዜ በመንፈሳችን ማሕጸን ተዘርቶ በመለኮት ጥበብና እውቀት አዲስና መንፈሳዊ ሰው አድርጎ ይወልደናል:: የሰማነውን የእውነት ቃል በእምነት በተቀበልን ጊዜ በአዲስ ልደት የእግዚአብሔር ልጆች እንሆናለን:: ለዚህም ነው ሓዋርያው ጴጥሮስ "እንግዲህ ክፋትን ሁሉ ተንኮልንም ሁሉ ግብዝነትንም ቅናዓትንም ሓሜትንም አስወግዳችሁ, ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደሆነ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደተወለዱ ሕጻናት ተንኮል የሌለበትን የቃሉን ወተት the pure milk of the word ተመኙ::" የሚለን:: (1ጴጥ1:1-3)

በመንፈሳዊው ሕይወት ይህ የመጀመርያው የእድገት ደረጃችን ሲሆን, በዚህ ጊዜ አዲስ የተወለዱ ሕጻናት ፍቅርን, እንክብካቤንና ጥንቃቄን እንደሚሹ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የመዳናቸውን ወንጌል ሰምተውና የሕያው እግዚአብሔር ልጅ የሆነውን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኛቸውና ጌታቸው አድርገው የተቀበሉ አዳዲስ ክርስቲያኖችም የሚያስፈልጋቸው ይኽው ጥንቃቄና እንክብካቤ ነው:: ለዚህም ነው ሓዋርያው ዮሃንስ "ትልቁ የበጎች እረኛ" ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መንጋውን በሦስት የመንፈሳዊ እድሜ ደረጃ ከፍሎ እንደሰጣቸው እንዲሁ "ልጆች፣ጎበዞች፣ አባቶች" እያለና የመልእከቱንም ጭብጥ በሶሶት ደረጃዎች ከፍሎ ሲጽፍ የምናገኘው:: "ልጆች ሆይ ኃጢአታችሁ ስለስሙ ተሰርዮላችኋልና እጽፍላችኋለሁ!!!" (የሚቀጥል)               

ሦስቱ የመንፈሳዊ ሕይወት እድገት ደረጃዎች! (ክፍል 3)

1. ልጅነት

"ልጆች ሆይ ኃጢአታችሁ ስለ ስሙ ተሰርዮላችኋልና እጽፍላችኋለሁ" 1ዮሓ 2:12

በክርስቶስ በማመን ዳግመግኛ በምንወለድበት ጊዜ ጴጥሮስ እንዳለው "አሁን እንደተወለዱ ሕጻናት" ነን:: ተፈጥሮአዊ ልደታችንም እንደሚያስተምረን ለማደግም ሆነ አካባቢያችንን ለመለማመድ ጊዜ ይወስድብናል:: ወላጆቻችን በሚሰጡን ፍቅርና እንክብካቤ ቀስ በቀስ ዙሪያ ገባችንን እያየን አካባቢያችንን ማወቅና ሁኔታዎችን መለማመድ እንጀምራለን:: በዚህ ጊዜ ውስጥ የተለያዩ ጥፋቶችን ብናደርግ, ለምሳሌ መኝታችን ላይ "ተፈጥሮአዊ ግዴታችንን" ብንፈጽም, ወይም ለመራመድ ስንሞክር ብንወድቅ የሚቆጣን ወይም ሊቀጣን አለንጋ የሚያነሳ ወላጅ ጤነኛ አይደለም:: በልጅነታችን የምንፈጽማቸው ጥፋቶች ሁሉ ያለ እውቀት የሚፈጸሙ ብቻ ሳይሆኑ ወደላይ የሚያሳድጉን መሰላለሎቻችን ናቸው:: ለዚህም ነው ለሕጻናት ከፍቅርና ከእንክብካቤ ምግባቸውንም በየጊዜው ከመመገብ በቀር ቁጣም ሆነ ቁንጥጫ የማይስማማቸው::

ከእግዚአብሔር ዘንድ እውነተኛ የመጋቢነትን አደራ የተቀበሉ አገልጋዮች, በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ አዲስ የተወለዱ መንፈሳዊ ሕጻናትን የሚመግቡበት ጥበብ አላቸው:: ለነዚህ ሕጻናት መሰረታዊ የተባሉትንንና በወተት የተመሰሉትን መንፈሳዊ ምግቦች ከማዘጋጀት በተጨማሪ ምናልባት በሕይወት አካሄዳቸው ላይ የሚከሰተውን የትኛውም አይነት ድካም እንዴት አድርገው መሸከም እንዳለባቸው ያውቁታል:: በተለይም እነዚህ መንፈሳዊ ሕጻናት በሕይወታቸው ላይ በሚያዩት ድካም ተስፋ እንዳይቆርጡና በኃጢአት እንዳይከሰሱ ስለኃጢአታቸው የተከፈለውን ዋጋ ማሳየትና እንደ ሓዋርያው ዮሓንስ "ልጆች ሆይ ኃጢአትን እንዳታድርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ:: ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው:: እርሱም የኃጢአታችን ማስተሰረያ ነው::" (1ዮሓ 2:1) እያሉ ዘወትር ማነቃቃትና ማበረታታት ይጠበቅባቸዋል:: ዛሬ በብዙ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ያለው ችግር, ሕጻናት - ሕጻናት እንዲሆኑ ጊዜ አይሰጣቸውም:: ትናንት ያጠመቁትን መንፈሳዊ ሕጻን ዛሬ "ሽንቱን ሲሸና" ቢያገኙት ሙልጭ አድርገው ይገርፉታል, (በቃሉ አለንጋ)::

ልጅ ሳለን እንደ ልጅ ማሰባችን, እንደ ልጅ መናገራችንና እንደልጅ መቁጠራችን ጤነኛ ነው:: በልጅ ሃሳብ የሚፈርድ ሰው ግን ጤነኛ አይደለም:: ሕጻናት ቃላትን ከአፋቸው ለማውጣት, አረፍተ ነገር ለመስራትና ሃሳባቸውን ለመግለጥ የሚያደርጉት መፍጨርጨር የማያስቀውና በዚህ የማይደሰት ወላጅ የለም:: ከአልጋ ወርዶ ለመዳህ, ወንበር ተድግፎ ለመቆም, ቆሞም በትክክል ለመራመድ... የሚያደርጉት ጥረት እንዴት ደስ ያሰኛል!!! ደግሞም ሁልጊዜ እየተኮላተፉና ዳዴ እያሉ እንዲኖሩም የሚመኝ አባት አይኖርም:: ሁሉም ወላጅ ልጆቹን ወደ ት/ቤት የሚልከው ልጆቹ በትክክል መናገርና ማሰብ ሲጀምሩሩ ለማየት ከመጓጓት ነው:: ነገር ግን በዚህ ጊዜ በየትኛውም የሕይወት እንቅስቃሴአቸው አቅጣጫ ለሚመጣው ችግር የሕጻናቱ ዋስትና የወላጆችቻቸው ፍቅርና እንክብካቤ ነው::

በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በመንፈሳዊ እግሮቻችን ቆመንና መንፈሳዊውን ጉዞ ራሳችንን ችለን መጓዝ እስኪሆንልን ድረስ የሚያበረታንና የሚያሳድገን ከየአጥቢያ ቤተክርስቲያኖቻችን የምናገኘው መንፈሳዊ አገልግሎት ነው:: በተለይ - በተለይ, ካለማደጋችን የተነሳ በሕይወታችን ላይ በምናየው ድካም በኃጢአት እንዳንወቀስ ስለበደላችንና ስለኃጢአታችን የፈሰሰውን የልጁን የኢየሱስ ክርስቶስ ደም እለት - እለት እንድናስብ የሚያግዙን መጽሓፍ ቅዱሳዊ ትምሕርቶችና መንፈሳዊ ዝማሬዎች, በጠላት ዲያብሎስ እንዳንከሰስ የሚረዱን ዋንኛ መሳሪያዎቻችን ናቸው:: በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ስንወድቅ የሚያነሳን ዘላለማዊው የእግዚአብሔር ምሕረት የቆመው, በቀራንዮ መስቀል ላይ በተገለጠው የእግዚአብሔር ፍቅርና ልጁ በከፈለው ዋጋ ላይ ነው:: በየዕለቱ ከእግዚአብሔር ዘንዽ ለምናገኘው ይቅርታና ምሕረት ዋስትናችን በአብ ዘንድ ያለን ጠበቃ ነው::

ዛሬ ብዙዎች በድካማቸው የሚወቀሱትና ደግሞም መፍትሄ ፍለጋ በተለያዩና መጽሓፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ መንገዶች የሚንከራተቱት ስለኃጢአታቸውና ስለድካማቸው የተከፈለውን ይህንን የከበረ ዋጋ በትክክል የሚያሳያቸው እረኛ በማጣታቸው ነው:: ዛሬም ለእነዚህ ወንድሞቻችንና እሕቶቻችን የእግዚአብሔር መንፈስ ያለው ሓዋርያዊ መልእክት "ልጆች ሆይ ኃጢአትን እንዳታድርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ:: ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው:: እርሱም የኃጢአታችን ማስተሰረያ ነው::" የሚለው ነው:: (የሚቀጥል)

ሦስቱ የመንፈሳዊ ሕይወት እድገት ደረጃዎች! (ክፍል.4)

by Tibebe Belay on Monday, January 30, 2012 at 7:29am

ልጅነት!(ካለፈው የቀጠለ)

"ልጆች ሆይ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ: ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው:: እርሱም የኃጢአታችን ማስተስሪያ ነው:: ለኃጢአታችን ብቻ አይደለም: ነገር ግን ለዓለም ሁሉ ኃጢአት እንጂ::" 1ዮሃ.2:1-2

ከአለም ፍጥረት ጀምሮ ከታረደው በግ የተነሳ በዘመናት መካከል የተገለጠውና የሚገለጠው የእግዚአብሔር ምሕረት ፍጻሜና ወሰን የለውም:: በዚህ ዘመን ያሉ መንፈሳዊ ሕጻናት ሊረዱት የሚገባው ነገር ይህ ነው:: በልጅነታችን ዘመን የምንፈጽማቸው ኃጢአቶች በእግዚአብሔር ዘንድ ያለውን የምሕረት ጉልበት አይገዳደሩትም:: እርሱም የዓለምን ሁሉ ኃጢአት ያስወገደው የእግዚአብሔር በግ ነው:: የሰማዩ አባት ከስጋችን ድካምና በልጁ ሕይወት ካለማደጋችን የተነሳ ትናንት የፈጸምነውን በደል አያስታውሰውም:: ዛሬና ነገ ልንፈጽማቸው የምንችላቸውን ስሕተቶችም በቀራንዮ መስቀል ላይ ከተሰዋው በግ የተነሳ በፊቱ የሉም:: ከሳሻችን ዲያብሎስ የሚመዘው የክስ መዝገብ ሁሉ በሰማያዊው ችሎት ከአብ ዘንድ ካለን ጻድቅ ጠበቃ የተነሳ ውድቅ ናቸው::

በዚህ ዘመን ያሉ መንፈሳዊ ሕጻናት በክርስቶስ የተገለጠውን የእግዚአብሔር ፍቅር, ጸጋና ምሕረት በሙላት እንዳያጣጥሙ የሚከላከላቸው; ከውጭም (ሰዎችንና ሁኔታዎችን እየተጠቀመ) ከውስጥም (ባልበሰለውና ባላደገው አእምሮና ህሊናቸው አማካኝነት) ሆኖ የሚከሳቸው ከሳሽ ዲያብሎስ ነው:: ልጆች ሆይ! ዛሬ አንድ የምስራች እነግራችኋለሁ:: በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት የሚባል ነገር የለም:: እርሱ አምላካችን ይህንን ችግር ለአንዼና ለመጨረሻ ጊዜ በቀራንዮ መስቀል ላይ ፈጽሞ አስወግዶታል:: ይሄ ተራ የሃይማኖት ዶክትሪን አይደለም:: በመስቀሉ ላይ የተፈጸመውን ይህን የከበረ የእግዚአብሔር ሥራ ማየት ይሆንላችሁ ዘንድ እግዚአብሔር የልቦናችሁን ዓይኖች ያብራ!!
በኃጢአታችን ምክንያት ጠላት በአእምሮችን ላይ የሚያመጣው ክስና ተጽእኖ በራሱ እስራት ነው:: ዛሬ ብዙዎቻችን ክርስቲያኖች ሆነን, ደግሞም የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን መንፈሳችን እየመሰከረልን ነገር ግን ገና ከሞት ፍርሃት ፈጽመን ነጻ መውጣት ያልቻልንበት ምክንያት ጠላት በአእምሮአችንና በህሊናችን ውስጥ ከሚፈጥረው የኃጢአት ክስ የተነሳ ነው:: ነገር ግን ከቡር በሆነው የክርስቶስ ደም አንድ ጊዜ በተከፈለው ዋጋ የመዋጀታችን ምሥጢር ከእግዚአብሔር ዘንድ በሚመጣ ሰማያዊ መገለጥና ብርሃን ሲበራልን, በህይወታችን ዙሪያ በምናያቸው መንፈሳዊ ድካሞች አንከሰስም::
ኃጢአት ምንጩ ስጋዊ አእምሮ ነው:: ከዚህ አእምሮ ፈጽሞ ነጻ መውጣት እስኪሆንልን ድረስ በኃጢአት ድካም መኖራችን ግድ ነው:: በመጀመሪያዎቹ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ዘንድ ይታይ የነበረው ድካም (ቅናት, ክርክር, መለያየት...) በክርስቶስ አእምሮ ያለማደጋቸውና ከስጋዊ አእምሮ ያለመላቀቃቸው ውጤት ነው:: ሓዋርያው ጳውሎስ በዚህ ድካማቸው አልፈረደባቸውም:: ይልቁኑም ከዚህ ድካም ይበረቱ ዘንድ የሚያስችላቸውንና ላሉበት መንፈሳዊ ሕይወት ደረጃ የሚመጥናቸውን የወተት ቃል (መሰረታዊ የክርስትና ትምህርቶች) እንደመገባቸው የተናገረውን ቃል በ1ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 3:1-4 እንዲህ ተጽፎ እናገኘዋለን:: "እኔም ወንድሞች ሆይ የስጋ እንደመሆናችሁ በክርስቶስም ሕጻናት እንደሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልኩም:: ገና ጽኑ መብል ለመብላት አትችሉም ነበረና ወተት ጋትኋችሁ: ገና ስጋውያን ናችሁና እስከ አሁን ድረስ አትችሉም:: ቅናትና ክርክር ስለሚገኝባችሁ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደላችሁምን? እንደ:- ሰው ልማድስ አትመላለሱምን? አንዱ እኔ የጳውሎስ ነኝ, ሁለተኛውም:- እኔ የአጵሎስ ነኝ ቢል ሰዎች ብቻ መሆናችሁ አይደለምን?" (ዛሬ በዚህ ዘመን የሚገኙ ወንድሞቼም አንዱ:- እኔ "ኦርቶዶክሳዊ" ነኝ ቢል, ሁለተኛውም :- እኔስ "ፕሮቴስታንት" ነኝ ቢል, በመካከላቸውም ቅናትና ክርክር, መለያየትና ስድብ... ቢኖር ሰዎች ብቻ መሆናቸው አይደለምን? ደግሞም ሕጻናትና ሥጋውያን ናቸውና የሚያስፈልጋቸው ጠንካራ ምግብ ሳይሆን ወተት ነው::)
ከላይ እንዳልነው ክቡር በሆነው በክርስቶስ ደም የመዋጀታችን ምሥጢር ሲገባን ዛሬ በመንፈሳዊ ሕይወታችን ላይ በምናየው ድካም አንከሰስም:: ይሄ ማለት ግን እለት እለት ኃጢአትን እንደውሃ የመጨለጥ ነጻነት እናገኛለን ማለት አይደለም:: ደሙ የሰጠን ነጻነት ሕያው እግዚአብሔርን በእውነትና በመንፈስ ሆነን የምናመልክበትን ነጻነት ነው:: እግዚአብሔርን በክርስቶስ ኢየሱስ ሆነን በነጻነት ስናመልክ ደግሞ ከክብሩ ዙፋን የሚፈሰው ጸጋና ምህረት ከአፉም የሚወጣው ህያው ቃል የዕለት እንጀራችን ይሆናል:: ያኔ ዕለት - ዕለት አእምሮአችን እየታደሰ, በአንድ በኩል ጠላት በኃጢአታችን ምክንያት ከሚያመጣብን ክስ ነጻ እየወጣን በሌላ በኩል ደግሞ የኃጢአት ምንጭ ከሆነው ስጋዊ አእምሮ እየተላቀቅን እንመጣለን::(የሚቀጥል)

Thursday, June 28, 2012

"ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ..." ክፍል 3.

by Tibebe Belay on Thursday, March 29, 2012 at 6:11am ·

"ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያ የነበረውንና የሰማነውን: በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም: እጆቻችን የዳሰሱትን እናወራለን:: ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን: ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለም ሕይወት እናወራላችኋለን: እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወአላችኋለን:: ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው:: ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን እንጽፍላችኋለን::" (1ዮሃ.1:1-5)

በእርሱ በነበረው የእውነት መንፈስ, ሓዋርያው ዮሃንስ በወንጌሉም ሆነ በመልዕክቶቹ ውስጥ ትኩረት ሰጥቶ ይጽፍ የነበረው, በመጀመሪያ በእግዚአብሔር ዘንድ ስለነበረውና እግዚአብሔርም ለእኛ ስላዘጋጀው, ኋላም በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት ስለገለጠውና በእኛም ይገለጥ ዘንድ ስለወደደው ሕይወት ነው። እኛም በዚህ መልዕክታችን ውስጥ ትኩረት ሰጥተን እያየን ያለነው, እንኖረውና እንተነፍሰው ዘንድ እግዚአብሔር ከዘላለም ዘመናት በፊት የወሰነልን ሕይወት ክርስቶስ መሆኑን ነው። በእርግጥ ዮሃንስ በመልዕክቱ ላይ ሲናገር እንደምናገኘው በመጀመሪያ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስለነበረው ስለዚህ ዘላለማዊ ሃሳብ ለመረዳት በመንፈሳዊ አዕምሮ እያደጉና እየየበለጸጉ ወደመንፈሳዊ አባትነት ደረጃ ማደግን ይጠይቃል:: በመጀመሪያ የነበረውን ሊረዱ ብቃትን ከእግዚአብሔር ዘንድ ያገኙት "አባቶች" ናቸውና:: (1ዮሃ.2:14)

በመጽሓፍ ቅዱሳችን ውስጥ በግልጽ ተጽፎ እንደምናገኘው, የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ሃሳብ ሰውን በመልኩ እንደምሳሌው መፍጠር ነው:: በእርግጥ በዘፍጥረት መጽሃፍ በምዕ.1:26-28 ላይ ያለውን ቃል ስናነብ, ወይም ደግሞ እግዚአብሔር የመጀመሪያውን ሰው ከምድር አፈር አበጅቶ በዔደን ገነት እንዳኖረው የሚናገረውን የመጽሃፉን ሁለተኛ ምዕራፍ ስንመለከት, ይሄ የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ሃሳብ ማለትም ሰውን በመልኩ እንደምሳሌው መፍጠሩ ያለቀና የተጠናቀቀ ጉዳይ እንደሆነ እናስባለን:: እንዲያውም ብዙዎቻችን በእግዚአብሔር መልክና ምሳሌ የተፈጠረው ሰው ያ ከምድር አፈር የተበጀው ሰው እንደሆነም እናምናለን:: ነገር ግን መንፈሳዊ ዓይኖቻችን ተከፍተው ወይም ደግሞ እጅግ የጠለቀውን የመለኮት ሃሳብ በመልዕክቶቻቸው እየጻፉ ለእኛ እንዳስተላለፉልን ሓዋርያት በእግዚአብሔር ጥበብና ማስተዋል የበለጸገ መንፈሳዊ አዕምሮ ቢሆንልን; "በመጀመሪያ በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረው" - ዓለም ሳይፈጠር - ከዘላለም ዘመናት በፊት እግዚአብሔር ለክብራችን የወሰነውን የከበረ ሕይወት ክርስቶስ መሆኑን መመልከት እንችል ነበር::

"እንዲሁ ደግሞ:- ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል: ኋለኛው አዳም ግን ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ:: ነገር ግን አስቀድሞ ፍጥረታዊው ቀጥሎም መንፈሳዊው ነው እንጂ መንፈሳዊው መጀመሪያ አይደለም:: የፊተኛው ሰው ከመሬት መሬታዊ ነው: ሁለተኛው ሰው ከሰማይ ነው:: መሬታዊው እንደሆነ መሬታውያን የሆኑት ደግሞ እንዲሁ ናቸው: ሰማያዊው እንደሆነ ሰማያውያን የሆኑት ደግሞ እንዲሁ ናቸው:: የዚያንም የመሬታዊውን መልክ እንደለበስን የሰማያዊውን መልክ ደግሞ እንለብሳለን::" (1ቆሮ.15:45-49)

በእግዚአብሔር ዕቅድና ሃሳብ መሰረት ሰው አስቀድሞ ይኖረውና ያውቀው ዘንድ የተወሰነው ፍጥረታዊውንና ምድራዊውን ሕይወት ነው:: እግዚአብሔር የመጀመሪያውን ሰው ከምድር አፈር አበጅቶ በዔደን ገነት ሲያኖረው የዚህ ሰው ኑሮ የጀመረው ፍጥረታዊና ምድራዊ ከሆነው ሕይወት ነው:: ምንም እንኳን የዚህ ሰው ሕይወት ገና ሰማያዊና መንፈሳዊ ባይሆንም ነገር ግን ወደዚህ የላቀ ሕይወት የሚወስደው መንገድ ለእርሱ ዝግ አልነበረም:: እግዚአብሔር ይህንን ሰው በሁለት ምርጫዎች መካከል ማለትም በሕይወትና በሞት መካከል ሲያስቀምጠውም ለሕይወት በሚሆን መታዘዝ እግዚአብሔር ወደወሰነለት የከበረ መልክ እንዲደርስ ነበር:: ነገር ግን ያ ሰው በራሱ ምርጫና አለመታዘዝ ከዚህ የከበረ ሕይወትና መልክ እንደወደቀ እናውቃለን:: በዚህም ምክንያት እኛ ሁላችን ከዚህ ሰው የተካፈልነው ፍጥረታዊውንና ምድራዊውን ሕይወት ብቻ ሳይሆን ሞት ያለበትን ስጋዊውንና በኃጢአት የተበላሸውን የወደቀ ሕይወት ነው::

የዛሬ 2000 ዓመት አካባቢ በሥጋ የመጣው የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ, ከላይ ባነበብነው የጳውሎስ መልዕክት መሰረት በሁለት የተለያዩ ስሞች ተገልጦ እናገኘዋለን:: "ኋለኛው አዳም - The last Adam" እና "ሁለተኛው ሰው - The second Man":: የመጀመሪያው ሞቱን የሚያመለክት ሲሆን በመስቀል ላይ ሞቱ በኃጢአት ምክንያት የተበላሸውንና የወደቀውን ሰው አሮጌ ሕይወት ከመንገድ ጠርቆ በማስወገዱ ለዚያ አሮጌ ትውልድ እርሱ የመጨረሻው ሰው ሆኖአል:: በመሆኑም በእግዚአብሔር አቆጣጠር ያ የወደቀው ሰው ዛሬ የለም:: "አሮጌው ነገር አልፎአል!!!" በትንሳኤው ደግሞ በእግዚአብሔር ዘንድ በመጀመሪያ የነበረውና እግዚአብሔር ለክብራችን የወሰነው የከበረ ሕይወት - ክርስቶስ - ሕይወትና አለመጥፋት - የዘላለም ሕይወት ወደ ብርሃን ወጥቶአል:: በእርግጥ ሁለተኛው ሰው ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው, ሰማያዊ ነው, መንፈሳዊ ነው, የእግዚአብሔር መልክ ነው... ሕይወታችንም እርሱ ነው - ክርስቶስ!!!

"ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ..." (ክፍል 2)

by Tibebe Belay
|

"በዚያ ዘመን ከእስራኤል መንግስት ርቃችሁ, ለተስፋውም ቃልኪዳን እንግዶች ሆናችሁ, በዚህም ዓለም ተስፋን አጥታችሁ, ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያ-ለ-ክ-ር-ስ-ቶ-ስ ነበራችሁ" ኤፌ.2:12

በክፍል 1 መልእክታችን በጥቂቱ ለማየት እንደሞከርነው, እግዚአብሔር ለእኛ ለሰው ልጆች የሰጠንና የወሰነልን የከበረ ሕይወት ክርስቶስ ነው:: ሓዋርያው ዮሃንስም በ1ኛ መልእክቱ ምዕራፍ አንድ ከቁጥር አንድ እስከ አራት ላይ እንዳመለከተን የዛሬ 2000 ዓመት አካባቢ የተገለጠው ከዘላለም ዘመናት በፊት በርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረውና እግዚአብሔር ለእኛ ያዘጋጀው ሕይወት ነው:: ይህ ሕይወት የሚገኘው ደግሞ ከአብና ከልጁ ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በሚኖረን ሕብረት እንደሆነ በግልጽ ተጽፎ እናገኛለን:: እግዚአብሔር የዘላለምን ሕይወት እንዲሁ ሰቶናል:: ይህም ሕይወት ያለው ደግሞ በልጁ ነው:: ለዚህም ነው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ "በእግዚአብሔር እመኑ - በእኔም ደግሞ እመኑ... አባት ልጁን ይወዳል, ሁሉንም በእጁ ሰቶታል:: በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው:: በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቁጣ በርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም... እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ, አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይቺ የዘላለም ሕይወት ናት.." እያለ ሲናገር የምናገኘው::

ከላይ ሓዋርያው ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች በጻፈው መልእክቱ ላይ የምናነበው ቃል, የዛሬ 2000 ዓመት አካባቢ ክርስቶስ በስጋ ከመምጣቱ በፊት ወይም እግዚአብሔር ከዘላለም ዘመናት በፊት የወሰነልን የከበረ ሕይወት ከመገለጡ በፊት እንኖር የነበረበትንና "የእግዚአብሔር ሕዝብ" በተባሉት እስራኤላውያን ዘንድ "አሕዛብ" እየተባልን እንጠራበት የነበረበትን ሁኔታ የሚያመለክት ነው:: በዚህ ዓለም ተስፋ አጥተን እንኖር የነበረው ከእግዚአብሔር ተለይተን ያ-ለ-ክ-ር-ስ-ቶ-ስ ያለ ሕይወት - ሙታን ከመሆናችን የተነሳ ነው:: በእርግጥ ዛሬ ደግሞ በተራችን የዘላለምን ሕይወት ተስፋ በክርስቶስ ኢየሱስ አግኝተን ከእግዚአብሔር ጋር መስማማት በሆነልን በእኛ ዘንድ "አሕዛብ" ተብለው የሚጠሩት "ከእግዚአብሔር ተለይተው ያ-ለ-ክ-ር-ስ-ቶ-ስ" የሆኑት ሁሉ ናቸው:: እነዚህ ያለክርስቶስ "ያለ እግዚአብሔር ሕይወት" የሚኖሩት አሕዛብ ዛሬ ያሉበትን ሁኔታ ሓዋርያው እንዲህ በማለት ገልጾታል:: "እንግዲህ አሕዛብ ደግሞ በአእምሮአቸው ከንቱነት እንደሚመላለሱ ከ እንግዲህ ወዲህ እንዳትመላለሱ እላለሁ: በጌታም ሆኜ እመሰክራለሁ:: እነርሱ ባለማወቃቸው ጠንቅ በልባቸውም ደንዳናነት ጠንቅ ልቡናቸው ጨለመ: ከእግዚአብሔርም ሕይወት ራቁ: ደንዝዘውም በመመኘት ርኩሰትን ሁሉ ለማድረግ ራሳቸውን ወደ ሴሰኝነት አሳልፈው ሰጡ:: እ-ና-ን-ተ ግ-ን ክ-ር-ስ-ቶ-ስ-ን እንዲህ አልተማራችሁም..." ኤፌ.4:17-24

ክርስቶስ ሕይወታችን ነው ማለታችን; በመንፈሳችን ከፍታ ላይ የሚኖርና በነፍሳችን ማሕጸን የተጸነሰ የዘላለም ሕይወት - የጽድቅ, የቅድስና, የጥበብ, የእውቀት...ሁሉ ምንጭ ነው ማለታችን ነው:: ክርስቶስ ሕይወታችን ነው ስንል; በመጽሓፍ ቅዱሳችን ውስጥ "የመንፈስ ፍሬ" ተብሎ የተዘረዘረው የጽድቅ ሕይወት የሚገኝበት ዘር ነው ማለታችን ነው:: (ፊሊ.1:9-11) በሰውነታችን ሁሉ የሚዘዋወረው ደም በምድር ላይ በምንኖርበት ዘመን ሁሉ ለስጋችን የሕይወት - የኃይልና ጉልበት ምንጭ እንደሆነ ሁሉ; ክርስቶስም ለመንፈሳዊ ኑሮአችን የሕይወትን የቅድስና ምንጭ, የመንፈስ ኃይልና የጽድቅ ጉልበት ነው:: እግዚአብሔር ከዘላለም ዘመናት በፊት ሰውሮት የነበረው, በነቢያት የተነገረውና, በወንጌል የተሰበከው ደግሞም የዛሬ 2000 ዓመት በኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት የገለጠው የከበረ ምሥጢር ይህ ነው:: "ምሥጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእኛ ዘንድ (in us) መሆኑ ነው" (ቆላ.1:27)
· · · Share · Delete


"ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ...!" (ክፍል 1)


እግዚአብሔር ሁሉን የሰራው በልጁና ለልጁ ነው:: ዓለማትን የፈጠረውም ሆነ በአዳም አመጽና በደል ምክንያት ከርሱ የተለየውን ፍጥረት የዋጀው ደግሞም በዘመናት መጨረሻ ሁሉን የሚጠቀልለውና ወደራሱ የሚመልሰው በልጁ ነው:: ይሄ ምሥጢር ታላቅ ነው!! ከዘላለም ዘመናት ጀምሮ ክርስቶስ - የሕያው እግዚአብሔር ልጅ በእግዚአብሔርና በፍጥረቱ መካከል ቆሞአል:: እርሱ የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነውና, የማይታየው እግዚአብሔር ለፍጥረቱ ራሱን የገለጠው በእርሱ ነው:: ደግሞም ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኩር ነውና እግዚአብሔር ፍጥረቱን ሁሉ ያጋጠመውም በእርሱ ነው:: እግዚአብሔር ከእርሱ የሆነውን ሁሉ የሰጠን በክርስቶስ ነው:: እኛም ከእግዚአብሔር የሆነውን ሁሉ የምንቀበለው ብቻ ሳይሆን እርሱ ያለንን ሁሉ የምንሆነው በክርስቶስ ነው:: ምንም እንኳን ሓይማኖት በሃሰተኛ ምላሱ ሌላ ትርጉም ቢሰጠውም, ያኔ - ያዕቆብ በካራን ምድር, ድንጋይ ተንተርሶ በተኛበት ስፍራ ባለመው ሕልሙ እግዚአብሔር የገለጠለትም ይሄንኑ ምሥጢር ነው:: (ዘፍ.28:10-13)

"መቼም ብዙ አማልክትና ብዙ ጌቶች አሉ: ነገር ግን በሰማይ ሆነ በምድርም ሆነ አማልክት የተባሉ ምንም ቢኖሩ ለእኛስ ነገር ሁሉ ከርሱ የሆነ እኛም ለርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን: ነገር ሁሉ በርሱ በኩል የሆነ እኛም በርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን::" (1ቆሮ.8:5-6)

ከክርስቶስ ውጪ እግዚአብሔርንና ከእግዚአብሔር የሆነልንን ነገር መፈለግ ከንቱ ድካም ነው:: ለዚህም ነው የቀደሙት ሓዋርያት እግዚአብሔርን በአገለገሉበት የሕይወት ዘመናቸው ሁሉ "የእግዚአብሔር ምሥጢር" የተባለውን ክርስቶስን ለሰዎች ሁሉ ለመግለጥ የተጋደሉት:: ለዚህም ነው ክርስቶስን እንጂ ራሳቸውንም፣ እናቱንም፣ መላእክትንም... ያልሰበኩት:። የጽድቅና የሕይወት ጠላት የሆነው ዲያብሎስ ግን በዋና ሠራተኛው ሓይማኖት በኩል በዘመናት መካከል ዛሬም በእኛ ዘመን ብዙዎችን ከእውነትና ከሕይወት መንገድ ያወጣው ይሄን ምሥጢር - ክርስቶስን በተለያየ ዘዴና ብልሃት በመሸፈን ነው። ዛሬ የብዙዎች ቅንዓት ሓይማኖታቸውና እርሱም ቀርጾ የሰጣቸው "ቀኖና" የሆነበትም ምሥጢር በዚህ የወንጌል ጠላት ከመጭበርበራቸው የተነሳ ነው።

እግዚአብሔር ለእኛ የወሰነውና ክብር የሞላበት ሕይወት ያለው በክርስቶስ ብቻ ሳይሆን ክርስቶስ ራሱ ነው። ወንድሞቼ በዮሃንስ ወንጌል ምዕራፍ 1:1-5 ላይ የሰፈረውን ጥልቅ ትምሕርት የሚጠቅሱት ሓይማኖት ቀርጾ ስለሰጣቸው "የሥላሴ ምስጢር" ለመሟገት እንጂ እግዚአብሔር ከዘላለም ዘመናት በፊት ለነርሱ የወሰነላቸውንና የሰጣቸውን የከበረ ሕይወት - ክርስቶስን ሊያዩበት አይደለም:: "በርሱ ሕይወት ነበረች ሕይወትም የሰው ብርሓን ነበረች" የሰው ልጅ ክርስቶስን ማየት ካልሆነለት በቀር በጨለማ ይኖራል እንጂ ወደብርሃንን አይመጣም። ክርስቶስን ካላገኘ በቀር ዕረፍትም ሆነ ሰላም፣ ሕይወትም አይሆንለትም:: "እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው:: ልጁ ያለው ሕይወት አለው: የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም::" (1ዮሃ.5:11-12)

ሕይወታችን ክርስቶስ ነው:: በክርስቶስ ያለው ሕይወት የኛ ሕይወት ነው:: ግንድና ቅርንጫፎቹን ማን ሁለት አደረጋቸው?? አካልና ራስስ ተለያይተው መኖር ይችላሉን?? "አካልም አንድ እንደሆነ ብዙም ብልቶች እንዳሉበት ነገር ግን የአካል ብልቶች ሁሉ ብዙዎች ሳሉ አንድ አካል እንደሆኑ ክርስቶስ ደግሞ እንዲሁ ነው::" (1ቆሮ.12:12) ክርስቶስም ደግሞ እንዲሁ ነው!! ክርስቶስም ደግሞ እንዲሁ ነው!! ክርስቶስ እንዴት ነው??? ክርስቶስ ብዙ ብልቶች ነገር ግን አንድ አካል ነው:: ክርስቶስንና ቤተ ክርስቲያንን - አካሉን - እኛን ማን ነው ሁለት ናቸው ብሎ የሰበከው?? "ሰው አባቱንና አናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ስጋ ይሆናሉ:: ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው!!! እኔ ግን ይህን ስለክርስቶስና ስለቤተ ክርስቲያን እላለሁ::" ኤፌ.4:31-32

ክርስቶስ የአካሉ ራስ ነው:: ራስነቱም ጌትነቱንና ገዢነቱን ብቻ ሳይሆን የሕይወት ምንጭነቱንም የሚያመለክት ነው። ምንም እንኳን ዛሬ ሓይማኖት በነሰነሰው መርዝ በቤተክርስቲያን መካከል መለያየት ሆኖ በአካሉ - በእኛ ያለው ሕይወት ሲታይ ይህን ባይመሰክርም, እግዚአብሔር ግን በእውነት በልጁ የጠራቸውን ልጆቹን በከበረው የክርስቶስ ሕይወት ከዚህ መርዝ ሊያነጻና ሊቀድስ በቅዱስ መንፈሱ እየተጋ ነው:ዓይናችን ተከፍቶ ማየት ከሆነልን, እኛ ባለንበት በዚህ ዘመን እግዚአብሔር ይህን የከበረ ሥራውን በቅዱሳኑ መካከል እየፈጸመ ነው:: "ከቤቱ መድረክ በታች" የሚወጣው የሕይወት ውኃ (ሕዝ.47፡1-12)፣ ሐይማኖት በተለያዩ እንግዳ ትምሕርቶች የበከለውንና ያረከሰውን የልጆቹን አእምሮ እየፈወሰ, ሃሳባቸውንም እየቀደሰ ነው:: ይህ ሥራው ሲፈጸም, ሕይወታችን የሆነው ክርስቶስ በቃላችንም በኑሮአችንም መገለጥና መታየት ይጀምራል:: አሜን ይሁን!!!!!
· ·  


እስከ መጨረሻው የሚጸና እርሱ ይድናል!!!!

by Tibebe Belay on Wednesday, April 18, 2012 at 9:50pm ·

ሐይማኖት በተለይም የፕሮቴስታንቱን ዓለም ካጭበረበረበት ጉዳዮች አንዱና ዋንኛው የመዳን ነገር ነው፡፡ አንድ አማኝ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኙ አድርጎ በተቀበለበት ቅጽበት እንደዳነ (ከምን እንደሆነ ባይነገረውም) ተሰብኮለታል፡፡ ስለዚሀም ይህ አማኝ የምድር ሕይወቱን በምንም አይነት ድካም ውስጥ ሆኖ ቢጨርስም የሰማይ ደጆች ለእርሱ የተዘጉ አይሆኑም፡፡ የሃይማኖት መምሕራን እንደነገሩት እንደርሱ ክርስቶስን የግል አዳኛቸው አድርገው ያልተቀበሉቱን እግዚአብሔር "በእሳት ባሕር" ውስጥ ለዘላለም ሲለበልባቸው፣ እርሱን ግን “አዲሲቱ ኢየሩሳሌም” በምትባልና ከወርቅ በተሰሩ ሕንፃዎችና አውራ ጎዳናዎች በተንቆጠቆጠች “ከተማ” ውሰጥ ሐሴት እያደረገ የሚኖርበትን ‘ዘላለማዊ ጸጋ* ያለብሰዋል፡፡ እውነቱ ግን ከዚህ በእጅጉ የራቀ መሆኑን የምንገነዘበው፣ (ለብዙዎች አስደንጋጭ ዜና ቢሆንም)በመጽሓፍ ቅዱሳችን ውስጥ የተገለጠውን እውነት በቅዱሱ የእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት መረዳት ከሆነልን ብቻ ነው፡፡

ሓዋርያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በጻፈው ሁለተኛው መልእክቱ በምዕራፍ 10፡1-13 ላይ ስለ እስራኤላውያን በተናገረው ክፍል ላይ እንዲህ የሚል ጠንካራ ቃል ተጽፎ እናገኛለን፡-
“እግዚአብሔር ከእነርሱ በሚበዙት ደስ አላለውም በምድረ በዳ ወድቀዋለና።…. ይህም ሁሉ እንደምሳሌ ሆነባቸው፣ እኛንም የዘመናት መጨረሻ የደረሰብንን ሊገስጸን ተጻፈ።”

አንድ ኢየሱሰ ክርስቶሰን እንደ ግል አዳኙ በመቀበል ዳግመኛ የተወለደ ከርስቲያን፣ ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ምድር ለመውረስ በባሕር መካከል የተሻገሩትንና ከሙሴ ጋር ለመተባበር በደመናና በባሕር የተጠመቁትን እስራኤላውያንን ይመስላል። እስራኤላውያኑ ሙሴን ለመተባበር መጠመቃቸው፣ እርሱ የሚላቸውን በመስማትና በመታዘዝ ደግሞም ቀን በደመና ሌሊት በእሳት አምድ የሚመራቸው የእሥራኤል ቅዱስ በሚያሳያቸው መንገድ ሁሉ እየተጉዋዙ ወደተሰጣቸው የበረከት ምድር ለመግባት ነበር። ከላይ ባነበብነው የጳውሎስ መልእክትም ሆነ ከአጠቃላዩ የእሥራኤላውያን ታሪክ እንደምናነበው ግን ከግብጽ ክወጡት መካከል ኢያሱና ካሌብ ብቻ ድል በመንሳት የተሰጣቸውን ተስፋ ሲወርሱ በብዙ ሺዎች የሚቆጠረው ሕዝብ የምድረ በዳውን ፈተና አላለፈም። ክፉ ነገር ተመኙ፣ ጣዖትን አመለኩ፣ ሴሰኑ፣ ጌታን ተፈታተኑ፣ አንጎራጎሩ ወይም አጉረመረሙ…. ስለዚህም የተሰጣቸውን ተስፋ ሳይወርሱ በምድረ በዳ ወድቀው ቀሩ፡፡ ይህም የዘመናት መጨረሻ የደረሰብንን እኛን ሊገስጸን ተጻፈ።

ጌታ ኢየሱስ ከርሰቶሰ ከኣባቱ ከይሖዋ በተቀበለውና መልአኩን ልኮ ለዮሓንስ በገለጠለት በራዕይ መጽሓፍ ውስጥ ለሰባቱ አብያተ ክርሰቲያናት የላከውን ደብዳቤ ስናነብ፣ በእያንዳንዱ ደብዳቤ መዝጊያ ላይ፣ “መንፈስ ለኣብያተ ከርሰቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ፣ ድል ለነሳው….” የሚል የከበረ ተስፋ የያዘ ቃል ተጽፎ እናገኛለን፡፡ እስቲ በሰምርኔስ ወዳለው የቤተ ክርስቲያን መልአክ በተጻፈው መልእክት መዝጊያ ላይ ድል ለሚነሱት የተገባላቸውን ተስፋ እንመልከት።
“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል የነሳው በሁለተኛው ሞት አይጎዳም።”
ሁለተኛው ሞት ምንድነው???
“ድል የሚነሳ ይህን ይወርሳል፣ አምላክም እሆነዋለሁ፣ እርሱም ልጅ ይሆነኛል። ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ፣ የርኩሳንም የነፍሰ ገዳዮችም (በቅዱሱና በጻድቁ አምላክ ሚዛን፡ ነፍሰ ገዳዮቹ ቢን ላደንና ሒትለር ብቻ ሳይሆኑ ወንድማቸውን የሚጠሉቱም ጭምር ሁሉ ናችው) የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም፣ ጣዖትንም የሚያመልኩ የሓሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፣ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።” ራዕይ 21፡7- 8

ክርስቲያን ሆይ! እስራኤላውያኑ በግብጽ ምድር ላይ መጥቶ ከነበረው የሞት መቅሰፍት በበጉ ደም ተሸፍነው ወይም ፋሲካ ሆኖላቸው እንዳመለጡ፣ ነገር ግን የአምላካቸው ግብና ዓላማ የምድረ በዳውን ፈተና አልፈውና ሰባቱን የአሕዛብ ነገሥታት በጦርነት ድል ነስተው ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር እንዲወርሱ እንደነበር፣ ለአንተም ያለው ዓላማ ይኸው ነው። በእምነት መንገድህ ላይ ልዩ - ልዩ ፈተና አለ። የነዚህ ፈተናዎች ምንጩ በሥጋና በደምህ ውስጥ ያሉት “የሥጋ ምኞት፣ የዓይን አምሮትና ስለ ገንዘብ መመካት (the pride of life) ናቸው። እነዚህን ፈተናዎች የቀደመው አባትህ በዔደን ገነት ተፈትኖት ወድቁዋል፣ እስራኤላውያኑ በምድረ በዳ ጉዞአቸው ወቀት ተፈትነውት ወድቀዋል። እነሆ የምሥራች!! የእምነትህ ጀማሪና ፈጻሚ የሆነው የህያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱሰ ክርስቶሰ እነዚህን ሁሉ ፈተናዎች በሥጋ ዘመኑ ተፈተኖ በድል አልፎአቸዋል። ዛሬም በአንተው ውስጥ ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆኖ በሥፍራ ሁሉ ድል በመንሳቱ ሊያዞርህና በነዚሀ ጠላቶችህ ራሰ ላይ ሊያቆምህ የታመነ ነው። ታዘዘው! የተሰጠህ የዘላለም ሕይወት ተስፋ በእምነት፣ በትዕግስት፣ በጽናትና በመታዘዝ የሚወረስ ነውና!!!!
“የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድትወርሱ መጽናት ያስፈልጋችሁዋል።” ዕብ.10፡36

እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን!!!!

by Tibebe Belay on Thursday, May 10, 2012 at 10:30am ·

“የሐይማኖት ነጻነት” ከፈጠራቸው ግርግሮች አንዱና ዋንኛው፤ ሰዎች ሁሉ አማልክቶቻቸውንና ነቢያቶቻቸውን በፈለጉበት ጊዜና ሥፍራ ለወደዱት ሁሉ መስበክና ማስተዋወቅ እንዲችሉ መፍቀዱ ነው። የምንኖረው ለጊዜውም ቢሆን በሰዎች ሥጋዊ አእምሮ ውስጥ ተሰውሮ የተቀመጠው እባብ በሚያስተዳድረው ዓለም ውስጥ በመሆኑ ይህ ለምን ሆነ አይባልም። ነገር ግን በዚህ ሁሉ ግርግርና ሁካታ መሀል እግዚአብሔር ለዓለሙ ሁሉ ስለሰጠው አንድና ብቸኛ የሕይወትና የደህንነት ምንጭ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጸጋንና ቅባትን እንደተቀበለ የወንጌል ሰባኪ፣ በታላቅና ከፍ ባለ ድምጽ መናገራችንን አናቆምም። “እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን!!!”

ለኣራት መቶ ዓመታት ያህል በግብጽ ምድር በአስከፊ ባርነት ውስጥ ኖረው የነበሩት እሥራኤላውያን፣ በኃይለኛው የእሥራኤል አምላክ ክንድ ከዚህ ባርነት ተፈትተው ይግዋዙበት በነበረበት ምድረ በዳ ውስጥ በአምላካቸውና ከፊት ሆኖ ይመራቸው በነበረው ነቢይ ላይ ከተናገሩት ክፉ ቃል የተነሳ የእግዚአብሔር ቁጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ። እየተነደፉ ይሞቱም ዘንድ እግዚአብሔር እባቦችን በሕዝቡ መካከል ሰደደ። እጅግ ብዙ ሰዎችም ሞቱ። ነገር ግን የእግዚአብሔር ሰው ሙሴ ስለ ሕዝቡ ወደእግዚአብሔር ጸለየ። “እግዚአብሔርም ሙሴን፡- እባብን ሠርተህ በኣላማ ላይ ስቀል፤ የተነደፈውም ሁሉ ሲያዩት በሕይወት ይኖራል አለው። ሙሴም የናሱን እባብ ሠርቶ በዓላማ ላይ ሰቀለ፣ እባብም የነደፈችው ሰው የናሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ።” (ዘኁ. 21፡8-9)

ንጉሱ ዳዊት፡- “እነሆ በዓመፃ ተፀነስሁ፣ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ።” ብሎ መናገሩ፣ ከአዳም የተገኘ የሰው ዘር በሙሉ - ነጩ ጥቁሩ፣ ዓረቡ አበሻው፣ እስላሙ ቡዲስቱ፣ 'ክርሰቲያኑ' 'አረመኔው'፣ ሳይነቲስቱ 'ጎዳና ተዳዳሪው'፣ ፕሬዝዳነቱ የቀን ባለሙያው፣... ወደዚህ ዓለም የሚወለድበትን የኃጢአትና የዓመፅ ሕግ ወይም ዘር ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። ይህ የኃጢአትና የዓመፅ ዘር ደግሞ በዔደን ገነት ሴቲቱ የተባበረችውና ከእርስዋም ጋር ጋብቻ የፈጠረው እባብ ነው። እርሱ የኃጢአትና የሞት ምንጭና ምክንያት ነው። እርሱ የእግዚአብሔር => የሕይወት - የጽድቅ - የቅድስና… ጠላት ነው። “የኃጢእት ደመዎዝ ሞት ነው === ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነው ==== ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነው ==== በሀሳባችሁ ጠላቶች ነበራችሁ === እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞቱ ዘንድ አላችሁና===

እግዚአብሔር በሰው ሁሉ ላይ የሆነውን ይህን የኃጢአትና የዓመፅ ዘር ከምንጩ ለማድረቅ የእባቡን ራስ የቀጠቀጠው፣ ጠላትነትን ያስወገደውና ሞትን የሻረው… በውጤቱም ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሐን በማውጣት የጽድቅንና የቅድስናን ምንጭ የከፈተው…. ሙሴ፣ እሥራኤላውያን እየተነደፉ የሞቱበትን እባብ በምድረ በዳ በዓላማ ላይ ከፍ አድርጎ እንደሰቀለ፤ የዛሬ ሁለት ሺኅ ዓመት አካባቢ “የምድር እምብርት” በተባለችው በቀራንዮ ከፍታ ላይ፣ አንድያ ልጁ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ “በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ” በመስቀል መከራ እንዲሞት በፈቀደ ጊዜ ነው። እግዚአብሔር በመካከላቸው በሰደደው እባብ የተነደፉ ሁሉ ሙሴ በዓላማ ላይ ከፍ አድርጎ የሰቀለውን የናስ እባብ ሲመለከቱ በመካከላቸው ከገባው የሞት መቅሰፍት እያመለጡ በሕይወት እንደኖሩ፣ ዛሬም የኃጢአትና የሞት ምንጭ በሆነው “የቀደመው እባብ” የተነደፉ ሁሉ፣ በቀራንዮ መስቀል ላይ ከፍ ብሎ የተሰቀለውን የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲያዩ - ሲያምኑ በሕይወት ይኖራሉ።

=>“ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።” (ዮሐ.3፡14-15)
=>“ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደተሰቀለ እናውቃለን፤ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቆአልና።” (ሮሜ.6፡6)

“እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል….”

by Tibebe Belay on Thursday, May 17, 2012 at 10:42am ·

ጊዜው በአገራችን ኢትዮጵያ የመንግሥት ለውጥ የተደረገበት ወቅት ነው። መቼም በዘመናችን የሚገኙ የአፍሪካ ‘ነገሥታት’ (ከአንዱ በስተቀር) የሚታወቁት፤ የቀደሙትን ማለትም የተኩዋቸውን ‘ነገሥታት’ መልካም ሥራ ሳይሆን የፈጸሙትን በደልና ግፍ፣…. ገመናቸውን ሁሉ  ጉድጉዋድ ቆፍረው፣ ፋይል በርብረው… ወደ ብርሐን እያወጡ በበደለኝነት በመክሰስና እነርሱ ግን በነዚህ “ግፈኞች” ነውር ላይገኙ ተስፋ በመስጠት ነውና፤ በእኛም አገር ይኸው ታሪክ የተደገመበት ጊዜ ነበር። 1983-84።

በወቅቱ “የቀይ ሽብር ወንጀለኞች” የሚል ስም የተሰጣቸው የደርግ ባለስልጣናትና “የበታች ሹመኞች” ከያሉብት ታድነው፣ በየኣካባቢው በሚገኙ የቀበሌ አዳራሾች፣ በየበደሉት ሕዝብ ፊት እየቀረቡ “አውጫጭኝ” ይካሄድ ነበር። እኔም ይሄንኑ ‘ስርዓት’ ለመከታተል ቦሌ አካባቢ በሚገኘውና ዛሬ “ሻላ” ተብሎ በሚጠራው አዳራሽ ውስጥ ተገኝቼአለሁ። በኣዳራሹ ግድግዳ ላይ “የቀይ ሽብር ሰለባዎች” ናቸው የተባሉ ወጣቶች ፎቶ ተሰቅሎአል። በመድረኩም ላይ ‘ወንጀለኞቹ’ ለሕዝብ እይታ ቀርበዋል። በአዳራሹ ውስጥ የነበረው ድባብ እጅግ ያስፈራል። ልጆቻቸውን በከፍተኛ ድብደባና ጥይት ያጡ ወላጆች እየተነሱ ይህንን ግፍ በፈጸሙት ‘ወንጀለኞች’ ላይ ጣቶቻቸውን እየጠቆሙና ድምጻቸውን ከፍ እያደረጉ የቻሉትን ያህል የቁጣና የስድብ ውርጅብኝ ያወርዱባቸዋል። ‘ወንጀለኞቹም’ አንገታቸውን ሰብረው አይናቸውን እያቁለጨለጩ ውርጅብኙን ‘በጸጋ’ ይቀበላሉ።

ይሄ ‘ትይንት’ ለረጅም ሰዓታት ቀጥሎአል። በዚህ ግርግር መሀል በድንገት አንድ አዛውንት ተነስተው የወጣቶቹ ፎቶ ተሰቅሎ ወደነበረበት ግድግዳ አመሩ። ከፎቶዎቹም መሀል አንዱን አንስተው ‘ወንጀለኞቹ’ ወደተቀመጡበት መድረክ ቀረቡ። ፊታቸውንም ወደሕዝቡ አዙረው እጅግ ልብ በሚሰብር ሁኔታ ስቅስቅ ብለው አለቀሱ። በአዳራሹ መሀል የሚገኝ አንድ ወጣትም በተለየ ሁኔታ አብሮአቸው ያለቅስ ነበር። ከረጅም ደቂቃዎች በህዋላ አዛውንቱ በተቻላቸው መጠን ራሳቸውን ገዝተው ሲያበቁ፣ በከፍተኛ ድምጽ “እግዚአብሔር ይመስገን!!” ብለው ጮሁ። የአዳራሹ ሁካታ ጥይት የተተኮሰ ያህል በከፍተኛ ዝምታ ተሞላ። “እግዚአብሔር ይመስገን!!” አሉ በድጋሚ። “አባታችን ሆይ የሚለውን ጸሎት መጸለይ ካቆምኩ አስራ ሰባት ዓመቴ።” በመድረኩ ላይ የተኮለኮሉት ‘ምስኪኖችም’፣ ‘ጠላቶቹን’ በቁጣና በስድብ ለመበቀልም ሆነ እንደእኔ በዚህ “የበቀል መድረክ” ላይ የሚከናወነውን ስርዐት ለመከታተል አዳራሹን የሞላው ሕዝብ አፉን ከፍቶ፣ ዓይኑን አፍጥጦ ከኣዛውንቱ የሚወጣውን ቃል በአንክሮ መከታተል ጀመረ። አዛውንቱ ቀጠሉ፡-

“አባታችን ሆይ የሚለውን ጸሎት መጸለይ ካቆምኩ ይኸው ድፍን አስራ ሰባት ዓመቴ። በዚህ ጸሎት ውስጥ ‘እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል፣ በደላችንን ይቅር በለን’ የሚል ቃል አለ። ታድያ እኔ የልጄን ገዳይ ይቅር ሳልል እንዴት አፌን ሞልቼ እግዚአብሔርን በደሌን ይቅር በለኝ ልበለው??? እግዚአብሔር ይመስገን!!! ከዛሬ ጀምሮ አምላኬን በደሌን ይቅር በለኝ እለዋለሁ። እግዚአብሔር አምላኬ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ እኔን በደለኛውን ይቅር እንዳለኝ፣ ይኸው ዛሬ የልጄን ገዳይ ይቅር አልኩት፣” አሉና በመድረኩ ላይ ከተኮለኮሉት ሰዎች መሀል አንዱን እቅፍ አድርገው ሳሙት። እጅግ በጣም የሚደንቀው ነገር፣ እኒህ አዛውንት በይቅርታ የሳሙት ሰው በቤታቸው ውስጥ እንጀራቸውን የበላ፣ በችግሩ የደረሱለት… ‘የቅርብ ሰው’ መሆኑ ነው።

በኣዳራሹ ውስጥ ነግሶ የነበረው የበቀልና የቁጣ መንፈስ ለጥቂት ደቂቃዎች ገሸሽ አለ። ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ያ አዛውንቱ ሲያለቅሱ በተለየ ሁኔታ አብሮአቸው ሲያለቅስ የነበረ ወጣት በከፍተኛ ቁጣና ንዴት፡- “አይሆንም አባዬ!! እኔ የአንዱን ወንድሜን ገዳይ በሕግ እበቀለዋለሁ…” እያለ በመጮህ “ለያዥ ለገናዥ” አስቸገረ። አባትየው በብዙ ለመኑት። እርሱ ግን “የሕግ ሰው” በመሆኑ የወንድሙን ገዳይ በሕግ እንደሚፋረደው አጥብቆ ተናገረ።

ጥቂት ዓመታት አለፉ፤ የወንድሙን ገዳይ በሕግ እንደሚፋረደው የተናገረው ወጣት በድንገተኛ ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። አሁንም ጥቂት ዓመታት አለፉ፤ እኒያ አዛውንት ሌሎች የምሕረት ዓመታት ተጨምረውላቸውና ዕድሜ ጠግበው በደላቸውን ይቅር ካላቸው ጌታ ጋር ተገናኙ። እንደገና ጥቂት ዓመታት አለፉ፣ በነፍስ ግድያ የተወነጀለው ሰው የፍርዱን ጊዜ በሚጠባበቅበት ወህኒ ውስጥ ጌታ አገኘው። መቼስ ወህኒ ቤት ሰዎች የተለያየ ‘እውቀት’ እየቀሰሙ የሚወጡበት ትምሕርት ቤት ነውና ይሄም ሰው የፍርድ ጊዜውን አጠናቆ ከወህኒ ሲወጣ እዚያው ቦሌ አካባቢ ከሚገኝ አንድ የወንጌላውያን ቤተ ክርሰቲያን ውስጥ የበረታ አገልጋይ ሆነ።

“እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ፡- በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ! ስምህ ይቀደስ፣ መንግሥትህ ትምጣ፣ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፣ የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፣ እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፣ ከክፉም አድነን እንጂ ወደፈተና አታግባን፣ መንግሥት የአንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ አሜን። ለሰዎች ኃጢኣታቸውን ይቅር ብትሉ፣ የሰማዩ ኣባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችሁዋልና፤ ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ፣ አባታችሁም ኃጢኣታችሁን ይቅር አይላችሁም።” (ማቴ.6፡9-15)      
· · · Share · Delete

የክርስቲያኖች ሕብረትና አንድነት!! (ክፍል 1)

by Tibebe Belay on Thursday, May 31, 2012 at 7:21am ·

እግዚአብሔር በቅዱስ መንፈሱ ነቢዩ ሕዝቅኤልን ወዲያና ወዲህ የተበታተኑና የደረቁ አጥንቶች ወደሞሉበት ሸለቆ ወሰደውና እንዲህ ብሎ ጠየቀው፡- “የሰው ልጅ ሆይ፣ እነዚህ አጥንቶች በሕይወት ይኖራሉን???” (ሕዝ.37፡ 1-14)
ይህን ጥያቄ የተጠየቁት፣ አንዲትዋ የክርስቶስ አካል - ቤተክርሰቲያን ጠላት በዘራው ክፉ የመለያየት ዘር፣ ሰዎችም ራሳቸው በፈጠሩዋቸው የተለያዩ እንግዳ ትምሕርቶች ሰበብ ወደተለያዩ ሐይማኖታዊ ቡድኖች ከመከፋፈልዋ የተነሳ ሕዝቅኤል በሸለቆው ውስጥ እንዳያቸው የደረቁ አጥንቶች በየስፍራው ተበታትና እና ሕይወት አጥታ ባለችበት በዚህ ዘመን ያሉት እርሰዎ ቢሆኑ ምን ብለው ይመልሳሉ???

በግምት ከአሥራ አምስት አመታት በፊት፣ የሚያራምዱት ሐይማኖት ለምድራችን መፍትሔ ያመጣ ዘንድ እግዚአብሔር ለዘመኑ የወሰነውና የሰጠው ሐይማኖት እንደሆነ ከሚሰብኩ ወገኖች ጋር የመነጋገር ዕድል አግኝቼ ነበር። ዋናው ስብከታቸው “ፍቅርና አንድነት” ነው። “እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፣ ደቀመዛሙርቴ እንደሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።” የሚለውን የክርስቶስ ትምሕርት ጠቀሱልኝና፡- “ይሄ ምልክት በዚህ ዘመን ባሉ ክርሰቲያኖች ዘንድ ይታያልን?? ዛሬ ‘ክርስትና’ በሚለው ስም የሚታወቁ ቢያንስ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሐይማኖቶች አሉ። በተለያዩ ጊዜያት በሐይማኖት ሰበብ ሌሎችን መግደላቸውን፣ እርስ በእርስም መገዳደላቸውን እና በፍቅር ተስማምተው አለመኖራቸውን ትተን፣ አንዳቸው ካንዳቸው ጋር የሚግባቡበት አስተምህሮ አላቸው??....” እያሉ በጥያቄ ያጣድፉኝ ጀመር። ከዚህም የተነሳ ‘ክርስትና’ ‘የዓለም ብርሐን’ ሊሆን ቀርቶ ራሱም በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እንደሚገኝ ሰበኩኝ። ጨምረውም አንድ ምሳሌ ነገሩኝ፡-
 “አንድ ሰው፣ አንድ ብርጭቆ በእጁ ይዞ ነበር። ይህም ሰው የያዘውን ብርጭቆ ከእጁ ቢለቀው ከወለሉ ላይ ወደቀና አንዱ ብርጭቆ ወደ ብዙ ስብርባሪነት ተለወጠ። ክርስትናም እንዲሁ ነው። ከእግዚአብሔር እጅ ወድቆ ወደብዙ ስብርባሪነት ተለውጦአል።” ሰዎቹ በድል አድራጊነት መንፈስ ስብከታቸውን ቀጠሉ። “እስቲ አንድ ‘ሎጂክ’ እንጠይቅህ፣ እነዚያ የብርጭቆ ስብርባሪዎች ተመልሰው ውሀ ሊይዝ የሚችል አንድ ብርጭቆ ሊሆኑ ይችላሉን??”

በዚህ ቅጽበት ነው ሕዝቅኤልን የተበታተኑና የደረቁ አጥንቶች ወደሞሉበት ሸለቆ የወሰደው የእግዚአብሔር መንፈስ እኔንም በእጄ የያዝኩትን መጽሐፍ እንድከፍት ያነሳሳኝ። እኔም በተራዬ ቀጠልኩ፡-
“ልክ ናችሁ ወንድሞቼ፣ በ’ሎጂክ’ የብርጭቆው ስብርባሪዎች ተመልሰው ውሀ ሊይዝ የሚችል አንድ ብርጭቆ ላይሆኑ ይችላሉ። ሆኖም ግን እስቲ በእጄ በያዝኩት መጽሐፍ ቅዱሰ ውስጥ እግዚአብሔር ነቢዩ ሕዝቅኤልን የጠየቀውን አንድ ተመሳሳይ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፡- በሸለቆ ውስጥ ወዲያና ወዲህ የተበታተኑና የደረቁ አጥንቶች እንደገና ተመልሰው በሕይወት ሊኖሩ ይችላሉን?” የሰዎቹን መልስ ትተን የሕዝቅኤል መልስ ግን፡- “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ታውቃለህ!!” የሚል ነበር። በ'ሎጂክ' ለሚያምን ሰው የደረቁ አጥንቶች ተመልሰው በሕይወት አይኖሩም። ለዓለም ሁሉ ብርሐን እንድትሆን እግዚአብሔር በምድር ላይ ያስቀመጣት አንዲት አካል - ቤተ ክርስቲያንም ወደ ተለያዩ ሐይማኖታዊ ቡድኖች ተለውጣና እዚህና እዚያ ተበታትና ስትታይ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቀበለችውንና፣ የሕይወት ምንጭ አድርጎ ለዓለሙ ሁሉ የሰጠውን አንድያ ልጁን ክርስቶስን ለሌሎች ልታካፍል ቀርቶ፣ ለራስዋም ይህን የሕይወት ራሰ ገፍታ ሕይወት የሌላት ደረቅ አጥንት ሆናለች። ነገር ግን እግዚአብሔር ዘመን አመጣ!! በራሳቸው የማመዛዘን ችሎታ ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር ቃልና መንፈስ ተመርተው በደረቁ አጥንቶች ላይ ትንቢት የሚናገሩ ሕዝቅኤሎችን በስፍራ ሁሉ እያስነሳ ነው።    እግዚአብሔርም ሕዝቅኤልን እንዲህ አለው፡- “በነዚህ የደረቁ አጥንቶች ላይ ትነቢት ተናገር እንዲህም በላቸው፡- እናንተ የደረቃችሁ አጥንቶች ሆይ!! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፣ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤….” ሕዝቅኤል እግዚአብሔር እንደተናገረው በነዚያ የደረቁ አጥንቶች ላይ ትንቢት ሲናገር፣ በመጀመሪያ የሆነው ነገር ድምጽና መናወጥ ነበር። ዛሬ ከመቼውም ጊዜ በላይ በክርስቲያኖች መካከል ያለው ድምጽና መናወጥ የእግዚአብሔር ቃልና መንፈስ የፈጠረው ነው። ለአንዳንዶች በዚህ ግሩፕ ውስጥ እየሆነ ያለው ነገር ግራ ይገባቸዋል። እንዲያውም “የክርስቲያኖች ሕብረትና አንድነት” የሚለው ስም እንደማይገባውም ይናገራሉ። ምክንያቱም የሚታየው ነገር አንድነት ሳይሆን፣ በቀድሞው ዘመን በሰናዖር ምድር እንደሆነው አይነት የቁዋንቁዋ መደበላለቅና ትርምስ ነው። ይህ ትርምስና መናወጥ የተፈጠረው በእግዚአብሔር ቃልና መንፈስ መሆኑን የተረዱት ግን ጥቂቶች ናቸው። እግዚአብሔር ዛሬ በቃሉ የብዙዎችን አሮጌ ሰማያት (ሐይማኖት የፈጠረውን አሮጌ አስተሳሰብና አመለካከት) እያናወጠ ነው። በዚህ ግሩፕ ውስጥ የምንሰማውም ድምጽ ይሄ መናወጥ የፈጠረው ነው። ነውጡ በጠላት የተዘራውንም ክፉ የመለያት ዘር ከሥሩ ይነቅላል። ከእግዚአብሔር ያልሆነውንና ሰዎች ከሕያው ቃሉ ውጪ በራሳቸው የፈጠሩአቸውን እንግዳ ትምሕርቶች፣ በእነዚህም ትምሕርቶች የተገነባውን አሮጌ አስተሳሰብና አመለካከት፣ ይሄ አስተሳሰብና አመለካከት የሰራውንም ቅጥር ያፈርሳል።

ሕዝቅኤል በተናገረው ትንቢት አማካኝነት ከተፈጠረው ድምጽና መናወጥ በህዋላ የሆነው ነገር የሚያስደንቅ ነው። “አጥንቶችም አጥንት ከአጥንት ጋር ተቀራረቡ።” (የሚቀጥል) 

የእግዚአብሔር ምስክር!!!

by Tibebe Belay ·

"አብ አባት ያልሆነበት ቅጽበት እንደሌለ ሁሉ ወልድም ልጅ ያልሆነበት ቅጽበት እንደሌለ እወቁ ተረዱ፤ በአብና በወልድ መካከል የጊዜ መቀዳደም እንደሌለ እወቁ ተረዱ፡፡" የሚለው ምስክርነት የማን ነው???

‘አባቶች’ ስለክርስቶስ ሲናገሩ፡- "ከብርሐን የተገኘ ብርሐን፣ ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ፣ የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ፣... ነው" ብለውናል። እዚህ ላይ ጥያቄዎችን እንጠይቅ፡- "ተገኝ - ተወለደ" ሲሉ ምን ማለታቸው ነበር? 'መቼ' ተገኘ?? 'መቼስ' ተወለደ?? የዛሬ 2000 ዓመት? ወይስ "ዓለም ሳይፈጠር?"  ከተወለደስ እንዴት በአባትና በልጅ መካከል "የጊዜ መቀዳደም" የለም ተባለ?? ካልተወለደስ እንዴት "ልጅ" ተብሎ ተጠራ?

በእርግጥ ክርስቶሰ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ እናውቃለን፣ ነገር ግን "መቼና እንዴት ተወለደ?" የሚለውን ጥያቄ ከመጠየቅ በቀር መልስ ማግኘቱ ስለከበደ ነው ክርስቶስ የማይመለስ ጥያቄና የማይደረስበት ምሥጢር ደግሞም በዘመናት መካከል እየበዛና እየጨመረ ለመጣው የክርሰቲያኖች መከፋፈልና መለያየት ምክንያት የሆነው። አይደለም ይሄን የጠለቀውንና ከሰው አስተሳሰብና አዕምሮ በላይ የሆነውን የመለኮት ምሥጢር ቀርቶ፣ የሥነ - ሕይወት ምሁራን ከሚሰጡን ጥቃቅን መረጃዎች በቀር የእኛም አጥንት በእናቶቻችን ማሕጸን ውስጥ እንዴት እንደተዋደደ የምናውቀው ነገር የለም።

ነገር ግን ይህ የዘመናት ምሥጢር የማይገለጥ አይደለም። አብ ከሳበው በቀር ወደ ወልድ ሊመጣ የሚችል ማንም እንደሌለ ሁሉ፣ አብ ካልገለጠለት በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም። አብ ራሱን ለሰዎች የሚገልጠው ደግሞ በልጁ ስለሆነ "ወልድ ካልገለጠለት በቀር አብን የሚያውቅ የለም፣"። ሰለዚህ ከሁሉ አስቀድሞ አብ ወልድን የገለጠልን ውይም ደግሞ እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረው፣ "በርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፣ እርሱን ስሙት" ብሎ ነው። ይሄንኑ መገለጥ፣ ይኸው የሰማይ አባት ለጴጥሮሰ ሲገልጥለት፣ በዚያ መገለጥ ላይ የእያንዳንዳችን እምነትና ሕይወት - ቤተ ክርሰቲያን ተመሰረተች። "አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ።"  ወንድሞቼ ሆይ!! ክርስቶስ ዓለም ሳይፈጠር እንዴትና በምን ሁኔታ እንደነበር፣ ወይም ደግሞ "በዓለም ፍጻሜ" እነዴት እንደሚገለጥ ለማወቅ ከመጣራችሁ አስቀድሞ፣ ዛሬ እምነታችሁና ሕይወታችሁ የቆመበትን መሠረት እወቁ። ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?... ሰዎች የሰውን ልጅ ማንም ይበሉት፣ ምክንያቱም የሰውን ምስክር ብንቀበል የእግዚአብሔር ምስክር ከእርሱ ይበልጣልና። ዋናውና ተፈላጊው ነገር እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረው ነው። ስለዚህ እናንተስ ማን እንደሆነ ትላላቸሁ?? ለዚህ ጥያቄ የምትሰጡት መልስ ነው እግዚአብሔር በጽዮን በመሠረተው፣ ነቢያቱ አስቀድመው በተናገሩትና ሐዋርያቱ በሰበኩት ጠንካራ ዐለት ላይ እንድትቆሙ፣ በእምነታችሁም ሆነ በሕይወታችሁ ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ እንድትኖሩ የሚያደርጋችሁ።

“ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- እነሆ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፤ የተፈተነውን፣ የከበረውን መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ የሚያምንም አያፍርም።” ኢሳ.28፡16

ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ የሰማው ወንጌል የመሠረተውም በዚህ ጠንካራ ዐለት ላይ ነበር። ሓዋርያው የነገረውን ሁሉ በጥንቃቄ ከሰማ በህዋላ፣ “እነሆ ውሀ እንዳልጠመቅ ምን ይከለክለኛል??” ብሎ በጠየቀ ጊዜ፣ የፊሊጶስ መልስ “በፍጹም ልብህ ብታምን ተፈቅዶልሀል፤” ነበር። ኢትዮጵያዊውም፡- “ኢየሱሰ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አምናለሁ።” በማለት የሰማው ወንጌል በውስጡ የፈጠረለትን እምነት በአንደበቱ መስክሮ፤ ሕይወቱንም ሆነ እምነቱን በተፈተነው፣ በከበረውና በጸናው ዐለት ላይ አገኘ።

ወንድሞች ሆይ! ስለ ክርሰቶስ ማንነት የሚኖረን ትክክለኛ እውቀትና መረዳት የሚነሳው ክዚህ መሠረት ላይ ነው። ማንም እምነቱንና ሕይወቱን ብቻ ሳይሆን ስለክርስቶስ ያለውን እውቀትና መረዳት ከዚህ እግዚአብሔር ስለልጁ ከመሰከረው መገለጥ ላይ ካልጀመረ፣ ክርስትናው ሐይማኖት ይሆነው እንደሁ እንጂ፣ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚያደርስና በሰዎች ትምሕርት ያልተበከለ እውነተኛና “ቀጥተኛ” እምነት አይሆነውም። የተመሠረተ ይታነጻል፣ ደግሞም ይደመደማል። የተወለደ ያድጋል፣ ብሎም ሙሉ ሰው ይሆናል። እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱሰ የሰጠን የዘላለም ሕይወትም ሆነ፣ ስለ እግዚአብሔር ልጅ ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚኖረን ዕውቀትና መረዳት ሙሉና ፍጹም የሚሆነው፣ ሰዎች የራሳቸውን ግምትና አስተሳሰብ ስለነገሩን ሳይሆን፣ አንደኛ ክርስቶስ ራሱ በትንሳዔው ሀይል አማካኝነት ለቤተክርስቲያን በሰጣቸው ስጦታዎች መጠቀም የቻልን እንደሁ፤  (ኤፌ.4፡11-16) እንዲሁም ክርስትና ማለት ክርስቶስን መከተል ወይም የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት መሆን ነውና፤ ስለ ሕያው እግዚአብሔር ልጅ ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚኖረን ዕውቀትና መረዳት ሙሉና ፍጹም የሚሆነው፣ በየዕለት - ከዕለት ሕይወታችን እርሱን በመታዘዝ መከተል ከሆነልን ነው። (ዮሃ.14፡21)             

ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስና ጌታ ነው!!!!

by Tibebe Belay on Saturday, June 2, 2012 at 10:55am ·

በበዓለ ኀምሳ በተቀበሉት ቅዱሱ የእግዚአብሔር መንፈስ ኣማካኝነት ሐዋርያት አገልግሎታቸውን ‘ሀ’ ብለው የጀመሩት፣ በየዕለቱ ሰዎች እየተሸከሙ በቤተ መቅደሰ ደጅ ያስቀምጡት የነበረውንና ከእናቱ ማኅጸን ጀምሮ አንካሳ የነበረውን ሰው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በመፈወስ ነበር። ይህን ‘ድውይ’ እንዴት ሊፈውሱት እንደቻሉ ለጠየቁዋቸውም የሕዝብ አለቆችና ሽማግሌዎች በጊዜው የመለሱት መልስም ቀጥተኛና ግልጽ ነበር፡- “እናንተ በሰቀላችሁት፣ እግዚአብሔርም ከሙታን ባስነሳው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም…. መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተስጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” (ሥራ.4፡7-12)

ሐዋርያው ጳወሎስም ሰው ሁሉ ኃጢአት ካመጣው የሞት ፍርድ እየዳነ የእግዚአብሔርን ጽድቅ የሚቀበልበትን መንገድ ለሮሜ ሰዎች በጻፈው መልዕክቱ ውስጥ ተመሳሳይ በሆነ ግልጽና ቀጥተኛ በሆነ መንገድ ነበር የገለጸው፡- “ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር፣ እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና፣ በአፉም መስክሮ ይድናልና።” (ሮሜ.10፡9-10)

የሰዎችን መዳንና ወደእግዚአብሔር መመለስ የማይፈልገው ጠላት ዲያብሎስ፣ ሰዎች ይህን ብቸኛ ስም እንዳይጠሩ - ጠርተውም እንዳይፈወሱ የሚጠቀምበት ስልቱ በየዘመናቱ የተለያየ ነው። ለምሳሌ ገና ከጅምሩ ሐዋርያቱን ለማስቆም የሞከረበት ስልቱ ዛቻና ማስፈራራት ነበር። “በነዚህ ሰዎች ምን እንሥራ? የታወቀ ምልክት በእነርሱ እጅ እንደተደረገ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሁሉ ተገልጦአልና፣ ልንሸሽገውም ዘንድ አንችልም፤ ነገር ግን በሕዝቡ ዘንድ እንዳይስፋፋ ከእንግዲህ ወዲህ ለማንም ሰው በዚህ ስም እንዳይናገሩ እየዛትን እንዘዛቸው። ጠርተውም በኢየሱስ ስም ፈጽመው እንዳይናገሩና እንዳያስተምሩ አዘዙአቸው።” (ሥራ.4፡16-18)

በአገራችን ኢትዮጵያ ለዘመናት ከተሰበከው “ልዩ ወንጌል” የተነሳ፣ በተለያዩ እንግዳ ትምሕርቶች ተሸፍኖ የነበረው ይህ አንድና ብቸኛ ስም መገለጥና መሰበክ የጀመረው ከጥቂት አሥርት አመታት በፊት ነበር። “ኢየሱስ ያድናል! መዳን በሌላ በማንም የለም!...” የሚሉ ወገኖች በምድሪቱ ላይ ብቅ-ብቅ ማለት ሲጀምሩ፣ ጠላት የተለመደ ዛቻና ማስፈራራቱን ጀመረ። “በሰንዴና በዘይት ወደአገራችን ከገባው ከዚህ መጤና ሰልባጅ ሐይማኖት ልጆቻችሁን ጠብቁ!... ” እየተባለ በየአውደ ምሕረቱ ሲሰበክ፣ በየዕድሩ ማስጠንቀቂያ ሲነገር… በተቃራኒው ግን “ኢየሱስ ያድናል!!” የሚለው የምሥራች በዚህም በዚያም ያስተጋባ ነበር።

ዛሬ ጠላት ይህን አንድና ብቸኛ የሆነውን ስም የሚሸፍንበት ስልቱን ፈጽሞ ቀይሮአል። አሁን ዛቻና ማስፈራራቱ ወደ ማደናገርና ማወናበድ ተለውጦአል። “ኢየሱስ ያድናል!! መዳን በሌላ በማንም የለም!!... ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር፣ እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህ” የሚለውን ግልጽና ቀጥተኛ ወንጌል፣ “አርሱ እግዚአብሔር ነው አይደለም?? አማላጅ ነው ወይስ ተማላጅ?? ከአብና ከወልድ ማን ይበልጣል??... “ በሚሉ ጥያቄ መሰል ማደናበሪያ ቃላት ይሸፍንና ወንድሞችን ማለቂያ ወደሌለው ሙግት ውስጥ ይከታቸዋል። አላማውም ሰዎች “ኢየሱስ እርሱም ክርሰቶስና ጌታ እንደሆነ በአፋቸው እነዳይመሰክሩ - መስክረውም እንዳይድኑ፤ እግዚአብሔርም ከሙታና እንዳስነሳው በልባቸው እንዳያምኑ - አምነውም እንዳይጸድቁ ነውና የተሳካለት ይመስላል። ነገር ግን ይህ ስኬቱ ለጊዜው ነው። የወንጌሉ ብርሐን በጨለማው የሰዎች ልብ ውስጥ ይበራል። ጉልበት ሁሉ በኢየሱሰ ስም ይንበረከካል!!! መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክራል!!!!!!!

የራዕይ አስራ ሁለትዋ ሴት ማርያምም፣ እሥራኤልም አይደለችም፤ ቤተ ክርስቲያን ናት!!

by Tibebe Belay on Saturday, June 9, 2012 at 6:07am ·

በምዕራፍ 1፡19 ላይ ያለው ሀሳብ የራዕይ መጽሐፍን ለማጥናት የመጀመሪያው ቁልፍ ነው። “… ያየኸውን፣ አሁንም ያለውን ከዚህም በህዋላ ይሆን ዘንድ ያለውን ጻፍ።” በነዚህ ሦስት የጊዜ ሰሌዳዎች መሰረት የመጽሐፉን ምዕራፎች በጠቅላላ በሦስት ክፍሎች ከፍለን ስናጠና፣ ምዕራፍ አስራ ሁለትን የምናገኘው “ከዚህም በህዋላ” በሚለውና ዮሐንስ ራዕዩን ከመጻፉ በፊትም ሆነ እየጻፈ ያለበትን ጊዜ ሳይሆን ወደፊት የሚፈጸሙ ክስተቶችን (Future events) በያዘው በሦስተኛው ክፍል ውስጥ ነው። ከዚህም የተነሳ ምዕራፍ አሥራ ሁለት እስራኤልንም ሆነ ማርያምን የሚመለከት ሊሆን አይችልም።

ሁለተኛውን ቁልፍ የሚገኘው በዚሁ የመጀመሪያ ምዕራፍ ቁጥር 20 ላይ ነው። “በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላዕክት (Messengers) ናቸው፣ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።” በዚህ ጥቅስ መሰረት የራዕይ መጽሐፍ የጠለቀውን መንፈሳዊ እውነታ (Spiritual reality) በምልክታዊ አገላለፆች (Symbolic expressions) የሚገልጥና፣ ለማጥናትም ሆነ ለመተርጎም እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ ብቻ ሳይሆን ዮሐንስ “በጌታ ቀን በመንፈስ” ሆኖ የተቀበለው ራዕይ በመሆኑ፣ ልንረዳው የምንችለውም በዚያው ዮሐንስ በጻፈበት ቅዱሱ የእግዚአብሔር መንፈስ ገላጭነት ብቻ ነው።

እነዚህን ሁለት ቁልፎች ይዘንና ወደ ዋናው ሀሳባችን ተመልሰን እጅግ በጣም ጠቃሚና ገላጭ የሆኑትን ጥቂት ሀሳቦች ብቻ እንመልከት፡- “ታላቅም ምልክት በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጎናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች። እርስዋም ፀንሳ ነበር፣ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጨንቃ ጮኸች።…. አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደእግዚአብሔር ዙፋን ተነጠቀ…”

ልብ በሉ! ምልክቱ የታየው በሰማይ ነው። ይህም የሚያመለክተን የተዘረዘሩት ነገሮች ሁሉ የተገለጡት በመንፈሳዊው ክበብ  (Spiritual realm) መሆኑን ነው። ስለዚህም የተከሰቱት ነገሮች ሁሉ “በመደዴው” (Literally) የማንትረጉማቸው፣ የማንረዳቸውም ናቸው ማለት ነው። ሴቲቱ አንዲት ግለሰብ (ይህ ቃል ቅድስት ማርያምን የሚመለከት አይደለም) ፣ ጭንቀትዋና ምጥዋም ሴት እናቶቻችን ልጅ ሊወልዱ ሲሉ እንደምናየው ዐይነት፣ በብዙ ጭንቅና ምጥ የወለደችውም ወንድ ልጅ እንዲሁ አንድ ጨቅላ (ይህም ስለ ኢየሱስ የተነገረ አይደለም) … እንደሆኑ ልናስብ አይገባንም ማለት ነው።

ሴቲቱ የተጎናጸፈችው ፀሐይ ==== “የፅድቅ ፀሐይ” የተባለው ክርስቶስ በመሆኑ ይህን “ለሰው ሁሉ የሚያበራ እውነተኛው ብርሃን” የለበሰች ሴት ከቤተ ክርስቲያን ሌላ ማን ልትሆን ትችላለች?

በአስራ ሁለት ከዋክብት የተመሰሉት አክሊሎችዋ ===== በዘመንዋ ጅማሬ ላይ በምድር ላይ ደምቀው የነበሩት የአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ምሳሌ ነው።….

የሴቲቱ ምጥና ጭንቀት===== ቤተ ክርስቲያን በዘመናት መካከል ስለጽድቅ የምትቀበለው መከራ ምሳሌ ነው። “… ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል…” እያሉ የቀደሙት ደቀ መዛሙርት የተናገሩት ቃል፣ ቤተ ክርስቲያን - በየዘመናቱ ስለ እምነት የምትከፍለውን ዋጋ የምትቀበለውንም መከራ የሚያመለክት ብቻ ሳይሆን፤ በውስጥዋ ያሉ የእግዚአብሔር ልጆች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንዳይገቡ እንቅፋት ከሆነው “የሥጋ ስራ” ጋር በየግል ሕይወታቸው የሚያደርጉትን ግብ-ግብ የሚያመለክት ነው። በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ በውጭ ባለ ተጽዕኖ ብቻ ሳይሆን፣ በውስጣቸው ካለ ሥጋዊ ፍላጎትና ባሕሪይ የተነሳ በጽድቅ ለመኖር በሚያደርጉት ተጋድሎ መከራና ጭንቀት ይሆንባቸዋል።።          

የወለደችው ወንድ ልጅና ወደዙፋን መነጠቁ ======= ከላይ እንዳልኩት፣ ይሄ ወንድ ልጅ አንድ ጨቅላ ሕጻን እንደሆነ ካሰብን እንስታለን። በእንግሊዝኛው MAN CHILD ተብሎ የተተረጎመው ይህ ቃል “የበሰለ፣ ያደገ፤ ፍጹም የሆነ….” ማንነትን የሚያመለክት ሲሆን ይህ ደግሞ በየዘመናቱ የሥጋን፣ የዓለምንና የሠይጣንን ሀሳብ በሕይወት አካሄዳቸው እያሸነፉ፣ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራና በሙላት መግባት የሆነላቸውን “ድል ነሺዎች” (Overcomers) የሚያመለክት ነው። ቤተ ክርስቲያን - የብዙ ብልቶች ጥርቅም አካል (Corporate Body) እንደሆነች ሁሉ ከማህጸንዋ - ከመካከልዋ የሚወጣውም ወንደ ልጅ እንዲሁ የጥቂት ድል ነሺዎች ስብስብ ነው። ይሄ እውነት ደግሞ ከዘመናት በፊት ነቢዩ ዳንኤል “መንግሥትም ግዛትም ከሰማይም ሁሉ በታች ያሉ የመንግሥታት ታላቅነት ለልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ ይሰጣል፤” በማለት ስለ አንድ ሕዝብ ከተናገረ በህዋላ “መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፣ ግዛቶችም ሁሉ ይገዙለታል ይታዘዙለታልም።” በማለት ከክርስቶስ ጋር አሕዛብን ሁሉ ስለሚገዛውና ስለሚያስተዳድረው አንድ አካል ትንቢት ተናግሮአል። (ዳን.7፡27)   

በተለይ ይሄንን የመጨረሻ ሀሳብ ለማጠናከር፣ በዚሁ በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት በላካቸው በእያንዳንዳቸው መልክዕቶች መደምደሚያ ላይ ድል ለሚነሱት የተሰጡትንና ብዙ ክብር የሞላባቸውን ተስፋዎች እናገኛለን። በተለይ በሎዶቅያ ቤተ ክርሰቲያን ስም፣ ነገር ግን በየዘመናቱ ላሉ ድል ነሺዎች የተገባውን ተስፋ እናንብበው፡-
“እኔ ደግሞ ድል እንደነሣሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ፣ ድል ለነሣው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ።….” (ራዕይ.3፡21)

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ አማኞች ሁሉም ድል ነሺዎች አይደሉም። የተጠሩት (The called out – Ekklesia – Church) ብዙዎች ቢሆኑም፣ የታመኑትና መንግሥትን የሚካፈሉት፣ ወይም አሕዛብን ለመግዛትና ለማስተዳደር ብቃትና አመኔታን የሚያገኙት ግን በጣም ጥቂቶች ናቸው። እነዚህ ወደ ጌታችንና ወደ መድኃኒታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችሁዋል የተባሉት፣ ሐዋርያው ጴጥሮስ በሁለተኛው መልዕክቱ ምዕ.2፡2-11 እንዳመለከተን፣ በሕይወት ዘመናቸው መንፈሳዊውን ፍሬ በሙላት ማፍራት የሆነላቸው ብቻ ናቸው።

ይሄ ከላይ በጥቂቱ ለማሳየት የሞከርኩት በራዕይ 12 ላይ የሰፈረውን ሀሳብ በሙላት የመግለጽ አቅም ይኖረዋል ባይባልም ቅሉ፣ እስከ ዛሬ ድረስ ስለ ምዕራፉ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ስለ ራዕይ መጽሐፍ ያላችሁን ግንዛቤ ቆም ብላችሁ እንድታዩ ሊያደርጋችሁ እንደሚችል አልጠራጠርም። በመጨረሻም፣ በጳውሎስ ልመና ልመርቃችሁ!!! የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብና የመገለጥን መንፈስ ይስጣችሁ!!!!! 

የተቀበልነው፣ የቆምንበት፣ ደግሞም የዳንበት ወንጌል!!!!

by Tibebe Belay on Wednesday, June 13, 2012 at 6:16am ·

በአገራችን ኢትዮጵያ ረዥም ዘመን ያስቆጠረችው "ሰው ሰራሽ ሐይማኖት" እና፣ የዛሬ 2000 አመት አካባቢ በሕያው እግዚአብሔር እጅ የተመሠረተችው፣ አስቀድሞ በነቢያት የተነገረችውና ሁዋላም በሐዋርያቱ የተሰበከችው እምነታችን የብርሀንና የጨለማ ያህል ሰፊ ልዩነት አላቸው።

ሰው ሰራሽዋ ሐይማኖት፤ ሰዎች በአንድ እግራቸው በአግባቡ ባልተነገረ ወንጌል ላይ፣ በሌላ እግራቸው ደግሞ በአፈ-ታሪኮች ላይ እንዲቆሙና ዘመናቸውን በግራ መጋባት እንዲጨርሱ ስታደርግ፤ ከሐዋርያቱ የተቀበልናትና ክርስቶስ ብቻውን የእምነታችንንና የሕይወታችን መሠረት እንደሆነ በሚነግረን ወንጌል ላይ የተመሠረተችው እምነታችን ግን፣ ሰዎች በሁለቱም እግራቸው በጸናው ዐለት በክርስቶስ ላይ ብቻ ጸንተው እንዲቆሙ ታደርጋቸዋለች። 

"ወንድሞች ሆይ!! የሰበክሁላችሁን፣ ደግሞም የተቀበላችሁትን፣ በእርሱም ደግሞ የቆማችሁበትን፣ በእርሱም ደግሞ የምትድኑበትን ወንጌል አሳስባችሁዋለሁ።... እኔ ደግሞ የተቀበልኩትን ወንጌል ከሁሉ በፊት ሰጠሁዋችሁ፣ እንዲህ ብዬ፡- መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለኃጢአታችን ሞተ፣ ተቀበረም፣ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሳ..." (1ቆሮ.15:1-4)

በሐይማኖት አጥር ውሰጥ በግራ መጋባት ተዘግቶባቸው የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ይህን ወንጌል በቃላቸው ያውቁታል። ነገር ግን ከራሳቸው ሕይወት ጋር ያለው ቁርኝት ምን እንደሆን በአግባቡ ስላልተነገራቸው በሁለት እግሮቻቸው አልቆሙበትም፣ ደግሞም አልዳኑበትም። ክርስቶስ ስለኃጢአታቸው ሞቶ፣ ስለበደላቸውም የከበረች ሕይወቱን ከፍሎ እያለ፤ ወደሰማዩ አባታቸው ፊት በድፍረት በመቅረብ የኃጢአት ይቅርታና ምሕረትን፣ ደግሞም እንዲሁ - በጸጋ  የተሰጣቸውን የዘላለም ሕይወት ለመቀበል ይሸማቀቃሉ። ስለዚህም መምሕራኖቻቸው ሌላ ዘዴ፣ ሌላ መንገድ፣ሌላ አማራጭ ...በሌላ ሦስተኛ ወገን በኩል ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንደሚቻል  ይነግሩዋቸዋል። ስለዚህም ከእምነት መንገድ ስተዋል። በክርስቶስ ወንጌል ከተገለጠው የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ሀሳብም በብዙ ሺህ ማይልስ ርቀው ቆመዋል።

በሐይማኖት አጥር ውስጥ በግራ መጋባት ተዘግቶባቸው የሚኖሩ ወገኖች ሁሉ፣ክርስቶስ ስለኃጢአታቸው እንደሞተ፣ እንደተቀበረ፣ በሦስተኛውም ቀን እንደተነሣ የሚናገረውን ወንጌል በቃላቸው ያንበለብሉታል እንጂ አልቆሙበትም፣ ደግሞም አልዳኑበትም።  እግዚአብሔር ከሁሉ በሚበልጠው የኃይሉ ታላቅነት ክርስቶስን ከሙታን ሲያስነሳው፣ እነርሱም አብረው እንደተነሡ አያውቁም። ስለዚህም በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ በሞት ፍርሐት እየተሸማቀቁ ይኖራሉ። መምሕራኖቻቸው ስለትንሣኤ የሰበኩዋቸው "ሌላ ወንጌል" ነው። ሐዋርያቱ የሰበኩት የከበረ ወንጌል ግን እንዲህ ይላል፡-
"እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለጠጋ ስለሆነ፣ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሳ በበደላችን ሙታን እንክዋን በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወትን ሰጠን፤ በጸጋ ድናችሁዋልና፣ በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለጠግነት ያሳይ ዘንድ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን።" (ኤፌ.2፡4-7)

በሐይማኖት መቃብር ውስጥ የተዘጋባቸው ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምጽ የሚሰሙበት ጊዜ ይመጣል። እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ!!!!

“ያለ ድንግል ማርያም አማላጅነት አለም አይድንም??”

by Tibebe Belay on Thursday, June 14, 2012 at 8:39am ·

በመሰረቱ ጥያቄው በራሱ የተሳሳተ ነው። ምክንያቱም “በማርያም አማላጅነት አለም ይድናል ወይስ አይድንም?” ተብሎ ከመጠየቁ በፊት፣ “ማርያም አማላጅ ናት??” የሚለውን ጥያቄ አስቀድመን መመለስ ይኖርብናል። የዚህን ጥያቄ ትክክለኛውን መልስ ስናገኝ ደግሞ ከላይ በርዕሱ ላይ የተጠየቀው ጥያቄ በራሱ ከመንገድ ይወገዳል ወይም ጥያቄ መሆኑ ይቀራል።

ማርያም አማላጅ ናት?
ለዚህ ጥያቄ ትክክለኛውን መልስ ሊሰጥ የሚገባው በእጃችን ያለው መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ከእርሱ ውጪ የሆኑት መልሶች ሁሉ መልሶች ሳይሆኑ ወንድማችን ያሬድ አሻግሬ እንዳለው፣ “ሰዎች አይናቸውን ከኢየሱሰ ላይ እንዲያነሱ የሚያደርግ” የጠላት ዲያብሎስ ስልት ነው። በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ የተገለጠው፣ የክርስቶስ መካከለኝነትና ምልጃ (The mediating & intercession of Jesus Christ) እንጂ የማርያም ወይም የመላእክት ወይም የቅዱሳን መካከለኝነትና ምልጃ አይደለም። ስለዚህ ወንድሞቻችን “የማርያምን አማላጅነት” ብቻ ሳይሆን “ያለማርያም አማላጅነት አለም አለመዳኑን እንድንረዳ” ወደነአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የምስጋና ቃላት እና ወደ   “መፃህፍተ ቅዳስያትና አርጋኖ” የመሩንም ለዚሁ ነው።

=>“አንድ እግዚአብሔር አለና፣ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፣ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶሰ ኢየሱሰ ነው፤” 1ጢሞ.2፡5
=>“…የሞተው፣ ይልቁንም ከሙታን የተነሳው፣ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፣ ደግሞ ስለእኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” (ሮሜ.8፡34)
=>“ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደእኛ የተፈተነ ነው እንጂ፣ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀካህናት የለንም። እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።” (ዕብ.4፡15-16)  
=>“ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና፣ ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደእግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።” (ዕብ.7፡25)
=>“ክርስቶስ በእጅ ወደተሰራች የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደምትሆን ቅድስት አልገባምና፣ ነገር ግን ስለእኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደእርስዋ ወደሰማይ ገባ።” (ዕብ.8፡24)

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱትን የሓዋርያት ትምሕርቶች ያስቀመጥኩት ‘አይናቸውን በጨው አጥበው’፣ “ክርሰቶስ አሁን እየፈረደ ነው እንጂ እየማለደ አይደለም” ለሚሉት ጭፍን የሐይማኖት ጠበቃዎች ሳይሆን (እነርሱም አንድ ቀን ይሄ በአጉል የሐይማኖት ቅናት የደነደነ ልባቸው በቃሉ መዶሻ እንደሚሰበር አምናለሁ) ይልቁንም እንደቤርያ ሰዎች “ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን?” እያሉና ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ወደ እውነት - ወደ ክርስቶስ ለመመለስ የተዘጋጀ ልብ ላላቸው ሁሉ ነው።

ወገኖቼ ሰሙኝ!! “ያለ ድንግል ማርያም አማላጅነት ዓለም አይድንም??” የሚል ጥያቄ ፈጽሞ አይጠየቅም። “ማርያም አማላጅ ናት፣ ያለማርያም አማላጅነት ዓለም አይድንም…” የሚለው “ትምሕርት” ፤ ስለመተላለፋችን ቆስሎ ስለበደላችን የደቀቀው ፣ ደግሞም “ደዌን የሚያውቅ - የህማም ሰው” የተባለውና በድካማችን ሁሉ ሊራራልን የሚችለው የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ “እናንት ደካሞች ሸክም የከበደባችሁ ሁሉ፣ ወደእኔ ኑ ፣ እኔም አሳርፋችሁዋለሁ” እያለ የዚህ ዓለም ደካሞችን የሚጣራበትን የርህራሄ ድምፅ ሰዎች እንዳይሰሙ ጠላት ዲያብሎስ በፈጠረው ግርግርና ሁካታ መሀል የሚነገር የሐሰተኛ ነቢያት ቃል ነው። በክርስትና ውስጥ እንዲህ አይነት ትምሕርት የለም። እውነተኛ ክርስቲያኖችም ይሄን የመሰለ ጥያቄ አያነሱም። ምክንያቱም ጥያቄ የሚነሳው የተማርነው አልገባ ሲለን ነው። የተከተልነው ክርስቶስም ሆነ፣ ክርስቶስን የሰበኩን ሐዋርያት እንዲህ አይነት ትምሕርት አላስተማሩንም።   

በየዘመናቱ የተነሱና ዛሬም ያሉ የወንጌል ባለአደራዎችስ “እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል??” እያሉ ለሚጠይቁአቸው የዚህ ዓለም ጎሰቁዋሎች ሁሉ፤ “በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን፣ አንተና ቤተሰቦችህም ትድናላችሁ” እያሉ መልካሙን የምሥራች ይሰብካሉ። በእውነት የክርስቶስ ኢየሱስ ምስክሮች የሆኑና በእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል የተቀቡ የቃሉ ባለአደራዎችስ “መዳን በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” የሚለውን ግልጽና የማያሻማ የመዳን መንገድ ለሰዎች ሁሉ ያሳያሉ። በእውነት በእግዚአብሔር የተጠሩ የመንግሥቱ ሠራተኞች፤ ለሚጠይቁአቸው ሁሉ መልስ የሚሰጡት በልባቸው ውስጥ ተሰውሮ ከተቀመጠው ዘላለማዊው “የጥበብና የእውቀት መዝገብ” ነው እንጂ፣ በሕይወት በኖሩበት ጥቂት ዘመን የተናገሩት ነገር እውነት ይሁን ሐሰት ከማይታወቁ ሰዎች ማስታወሻ ላይ አይደለም። እነዚህ የወንጌል ባለአደራዎች ቃላቸውም ሆነ ስብከታቸው ክርስቶስ ነው።

“በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ቆረጬ ነበርና።” (1ቆሮ.2፡2)                
· · · Share · Delete

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ - የአዲስ ኪዳን መካከለኛ!!!

by Tibebe Belay on Friday, June 15, 2012 at 8:45am ·

“አንድ እግዚአብሔር አለና፣ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ ነው። እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፣ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፣ እኔም ለዚህ ነገር አዋጅ ነጋሪና ሐዋርያ በእምነትና በእውነትም የአሕዛብ አስተማሪ ለመሆን ተሾምሁ፣ እውነትን እናገራለሁ አልዋሽም።” (1ጢሞ.2፡5-7)

የዕብራውያን ጸሐፊ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን “የአዲስ ኪዳን መካከለኛ” ብሎታል። አዲሱ ኪዳን የዘመኑ እርዝመት ከመቼ እስከ መቼ ይሆን?? አዲሱ ኪዳን ባለበትና በጸናበት ዘመን ሁሉ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱሰ ክርስቶስ የኪዳኑ መካከለኛ ነው። ሐዋርያው ጳወሎስም “አንድ እግዚአብሔር አለና፣ በእግዚአብሔር በሰው መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፤(እዚህ ላይ ልብ በሉ!! ‘በእግዚአብሔርና በሰው መካከል የነበረው መካከለኛ ደግሞ አንድ ነበር’ አላለም) እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።” በማለት የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ መካከለኝነት የነበረና ዛሬም ያለ እንዲሁም ከእግዚአብሔር የተለየው ፍጥረት ሁሉ ወደእግዚአብሔር ተመልሶ ፍጻሜ እስከሚሆን ድረስ ወደፊትም የሚቀጥል እንደሆነ ነግሮናል። ታድያ በዚህ መልዕክቱ ላይ ጳወሎስ “ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ” በማለት ስለአንድ ያለፈ፣ ያለቀና የተጠናቀቀ ሂደት በሚጠቁም ቃል የተናገረው ስለምንድነው?? ስለመካከለኝነቱ?? በጭራሽ!!! ራሱን ለሁሉ ቤዛ አድርጎ ስለመስጠቱ ነው እንጂ!!! “…ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፣ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፣….”

የዛሬ 2000 ዓመት አካባቢ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ በመምጣቱ የተፈጸመና የተጠናቀቀ የእግዚአብሔር ሀሳብ አለ። ይሄ ክርስቶስ ከአብ የተሰጠውና በሥጋ በመምጣቱ የፈጸመው የከበረ ሥራ ደግሞ ነፍሱን ለሰው ልጆች ሁሉ ቤዛ አድርጎ በመስጠት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን ጠላትነት በሞቱ ያስወገደበት የማስታረቅ ሥራ ነው። ይሄ የማስታረቁ ሥራ አንድ ጊዜ የተጠናቀቀና የማያዳግም ሥራ ነው። ደግሞም ይህን በሥጋ የመጣበትን ስራ ፈጽሞ በክብር በአባቱ ቀኝ ከተቀመጠበት ጊዜ ጀምሮ፣ “የኁዋለኛው ጠላት” (The last enemy) የተባለው ሞት ከእግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ ላይ ተሽሮና እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ሆኖ ፍጻሜ እስከሚሆን ድረስ፣ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ ባለው የሊቀክህነት አገልግሎቱ የሚፈጽመውና ገና ያልተጠናቀቀ የማዳን ሥራ አለ። ይሄ እውነት ሲበራልን ነው፣ የክርስቶሰ የአዲሰ ኪዳን መካከለኝነት በሥጋ በመምጣቱና ቤዛውን በመክፈሉ ብቻ “ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ” የተጠናቀቀ እንዳልሆነ የምንረዳው።

“ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፣ ይልቁንም ከታረቅን በህዋላ በሕይወቱ እንድናለን፤ ይህም ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን አሁን መታረቁን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ እንመካለን።” (ሮሜ.5፡10-11)

ልብ በሉ!! መታረቃችን በሞቱ የተጠናቀቀና የተፈጸመ ነው፣ ክርስቶስ ኢየሱሰ ዛሬ ስለመታረቃችን አንዳች የሚያደርገው ነገር የለም፣ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ ያለው ሊቀ ካህን እንደቀደሙት ካህናት ዕለት ዕለት ስለበደልና ስለኃጢአት የሚሆን ማናቸውንም አይነት መስዋዕት አያቀርብም፣ ለመስቀል ሞት ራሱን አሳልፎ ሲሰጥ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎታል፣ እግዚአብሔርም ይህንን መስዋዕት ወዶ ተቀብሎታል፣ እንዲያውም እርሱ ራሱ በክርስቶስ ሆኖ ዐለሙን ሁሉ ከራሱ ጋር አስታርቆአል፣ ከእንግዲህ የማንንም በደል አይቆጥርም….. እኛም ዛሬ ሰዎች ሁሉ ይህን በመስቀል ላይ የተከፈለላቸውን ዋጋ እንዲያዩና፣ በእነርሱና በእግዚአብሔር መካከል የነበረው ጠላትነት በክርስቶስ ሞት እንደተወገደ እንዲረዱ የተሰቀለውን ክርስቶስን እየሰበክን ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ እንላለን። ስለዚህ የክርስቶስ የማስታረቅ ሥራ የተጠናቀቀ ነው ማለት ነው። ይህ ማለት ግን መካከለኝነቱ ተጠናቅዋል ማለት ነው?? አይደለም!!! “… ይልቁንም ከታረቅን በህዋላ በሕይወቱ እንድናለን!!”

መታረቃችን በሞቱ ነበር። መዳናችን ግን በሕይወቱ ነው። ለመታረቃችን መካከለኛ የነበረው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ዛሬም ለመዳናችን መካከለኛ ነው። መዳናችን በሕይወቱ - “በማያልፍ ሕይወት ኃይል” በመልከ ጸዲቅ ሹመት የዘላለም ሊቀ ካህን በሆነበት ሰማያዊ አገልግሎቱ ነው። ለዚህም ደግሞ “የእውነተኛይቱ ድንክዋን አገልጋይ” ተብሎአል። እዚህ ላይ ጨምረን ልናውቅ የሚገባው፣ ምልጃውም ከማያልፈው ሕይወቱና በግርማው ዙፋን ቀኝ ካለው ሰማያዊ አገልግሎቱ ጋር የተቆራኘ መሆኑ ነው፤ “የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው፣ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፣ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።” እንዲሁም፣ “ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ በእርሱ ወደእግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።” የተባልነውም በዚሁ ምክንያት ነው ። (ሮሜ.8፡34 ዕብ.7፡25)

እንግዲህ ከዚህ በላይ ሐዋርያቱ በግልጽ ባስተማሩት የክርስቶስ የአዲስ ኪዳን መካከለኝነትና ምልጃ ላይ፣ የወንጌል ጠላት በተለይ በአገራችን ኢትዮጰያ የፈጠረው ውዥንብር ዓላማው፤ እንደተለመደው በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን አንዱን ኢየሱስ ክርስቶስን ከሰው ልብና አእምሮ በማውጣት፣ ይሄ የመካከለኝነት ስልጣንና ኃላፊነት ያልተገባቸውን ሰዎችና መላእክት በቦታው ላይ ለማስቀመጥ ነው። በዚህ ተንኮልና ሴራው ደግሞ፣ በሰዎችና በእግዚአብሔር መካከል የነበረው ጠላትነት እንዲቀጥልና ሰዎች ከኃጢአትና ከሞት ሕግ እየዳኑ የዘላለም ሕይወት ተስፋ ተካፋዮች እንዳይሆኑ በብርቱ እየተጋ ነው። ከሁሉ በላይ እጅግ በጣም የሚያሳዝነውና ልብ የሚሰብረው፣ ወንድሞቻችን በሐይማኖት ቅናት ተነሳስተውና ማርያምን፣ ቅዱሳን ሰዎችንና ቅዱሳን መላእክትን ያከበሩ እየመሰላቸው የዚህ ክፉ ጠላት መሳሪያ መሆናቸው ነው። ነገር ግን ከዚህ የጥፋት መንገድ ተመልሰው የጽድቅ አገልጋዮች እንዲሆኑ በቃልም፣ በጸሎትም ተጋድሎአችን ይቀጥላል።

ከእግዚአብሔር ጋር የነበረን ጠላትነት በሞቱ ተወግዶ መታረቃችን ከተፈጸመ ጊዜ ጀምሮ፤ በመንፈስ፣ በነፍስና በሰውነታችን - በሁለንተናችን መዳና ሆኖልን በአዳም ውድቀት የተነጠቅነውን የልጅነት ክብር ፈጽሞ እስክንለብስ ድረስ፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በእኛና በእግዚአብሔር መካከል ያለ መካከለኛ፣ የአዲስ ኪዳን ዋስ፣ ጠበቃ፣ አማላጅ፣ ጌታ፣አዳኝ፣ ሊቀ ካህን፣ የበጎች ትልቅ እረኛ፣ የእምነታችን ራስና ፈጻሚ…. አማራጭና አቁዋራጭ የሌለው ብቸኛ የሕይወት መንገድ ነው። ስለዚህ ዛሬም፣ ነገም… በዚህች ምድር ላይ እንመላለስባቸው ዘንድ እግዚአብሔር ቆጥሮ በሰጠን ጥቂቶቹ ዓመታቶቻችን ሁሉ እርሱን ብቻ እንሰብካለን!!!!!!!!!!!!                                

የክርስቶስ ሊቀ ክሕነትና እውነተኛይቱ ድንኩዋን!! (ክፍል 3)

by Tibebe Belay  ·

“እኔ ላደርገው ዘንድ የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርኩህ…”

በሥጋው ወራት ይፈጽመው ዘንድ ከአባቱ የተቀበለውን ሥራ ፈጽሞ በምድር ያከበረው የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ዛሬም በሰማያት በግርማው ቀኝ የተቀመጠ የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኩዋን አገልጋይ ነው። እግዚአብሔር በክርስቶስ ይፈጽመው ዘንድ የጀመረው የከበረ ሥራ የዛሬ 2000 ዓመት አካባቢ ልጁን ወደዚህ ምድር በላከበት ወቅት የተጠናቀቀ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱሳችንን ጠጋ ብለን ስናነብ፤ እግዚአብሔር ዓለማትን ሁሉ የፈጠረው በክርስቶስና ለክርስቶስ (በልጁና ለልጁ) መሆኑን፣(ቆላ.1፡15-16 ዕብ.1፡2) በአዳም አለመታዘዝ ምክንያት ከእርሱ ተለይቶ የነበረውን ፍጥረቱን ሁሉ ወደራሱ የመለሰውም ቤዛውን በከፈለው አንድያ ልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ፣ እንዲሁም ደግሞ “በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል”(ኤፌ.1፡10) መሆኑን እንረዳለን። ታድያ ከዚህ የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዕቅድ አንጻር፣ እርሱ በክርስቶስ ሊያደርገው ያሰበው ሥራ ሁሉ ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ በሥጋ ሆኖ በተመላለሰባቸው 33 ½ ዓመታት ውስጥ ተጠቃሎ ተፈጽሞአል ማለት ይቻላል??   

ነቢዩ ዳዊት በመዝ.(40) ላይ ስለ ክርስቶስ በተናገረው ትንቢት መሠረት፣ ክርስቶስ የዛሬ 2000 ዓመት አካባቢ በተዘጋጀለት ሥጋ ወደዚህ ምድር ሲመጣ፣ “እነሆ አምላክ ሆይ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ” ማለቱ ተጽፎአል። ታድያ ክርስቶስ በሥጋ በመምጣቱ የፈጸመው የእግዚአብሔር ፈቃድ ምንድነው?? ይህን ጥያቄ እጅግ ሰፊ በሆኑ የተለያዩ መልሶች መመለስ ቢቻልም፣ ዋናው ግን ራሱን ስለኃጢአት መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር የሚታረቅበትንና ወደ እግዚአብሔር የሚመለስበትን ቤዛ ለመክፈልነው። (ዕብ.10፡5-10) ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር የመጣበትን የእግዚአብሔር ፈቃድና ዓላማ ለማጠናቀቅ በተቃረበበት ጊዜ እንዲህ አለ፡- “እኔ ላደርገው ዘንድ የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርኩህ፤ አህንም አባት ሆይ ዐለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።” (ዮሃ.17፡4-5)

ታድያ ክርስቶስ በምድር ይሠራው ዘንድ ከአብ የተቀበለውን ሥራ ከፈጸመ በሁዋላ ነገር ሁሉ አበቃ ማለት ነው?? አይደለም። የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰው ሁሉ ሞትን ከቀመሰ በሁዋላ እግዚአብሔር ከሙታን ሲያስነሳው፤ “ጠላቶችህን ሁሉ ከእግርህ በታች እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” የሚል ተስፋ ሰጥቶት እንደሆነ በመጽሐፋችን በግልጽ ተጽፎ እናገኛለን። አሁን ሁሉ ከእግሩ በታች እንደተገዛለት ገና አናይም። ለዚህም ነው ጌታ ኢየሱስ ክርሰቶስ ዛሬም በግርማው ቀኝ በተቀመጠበት የሊቀ ክህነት አገልግሎቱ በሥራ ላይ ነው የምንለው። በተደጋጋሚ እንዳልነው፣ ክርስቶስ በምድር - በሥጋው ወራት የሠራው ሥራ ስለኃጢአት ሥርየት የሚሆነውን ፍጹም መሥዋዕት አንድ ጊዜ ማቅረብ ነው። ይሄ ዛሬ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ ያለው ሰማያዊ ሥራውና አገልግሎቱ ግን፣ በዚህ አንድ ጊዜ ባቀረበው ፍጹም መሥዋዕት በኩል ወደእግዚአብሔር ለሚቀርቡት ሕይወትን ማካፈልና መስጠት ነው። ከእግዚአብሔር ጋር መታረቃችን በሞቱ፣ መዳናችን ደግሞ በሕይወቱ በማያልፍ ሕይወት ኃይል በመልከ ጼዴቅ ሹመት የዘላለም ሊቀ ካህን ተብሎ በተጠራበት ሰማያዊ አገልግሎቱ የሆነበትም ምክንያት ይኸው ነው።

 “ስለእነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና፤ ስለዚህ በእርሱ ወደእግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።” (ዕብ.7:25)
“ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፣ ይልቁንም ከታረቅን በህዋላ በሕይወቱ እንድናለን።" (ሮሜ.5፡10)
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሳኤው ኃይል የሞትን መውጊያ ሰብሮ በሰማያት በግርማው ቀኝ ከተቀመጠበት ጊዜ ጀምሮ እጁን አጣምሮ የመላዕክትን ዝማሬ እየሰማ አይደለም። ይልቁንም በሥጋው ወራት ቤዛውን ከፍሎ ጠላቶች የነበርነውን እኛን ከእግዚአብሔር ጋር በማስታረቅ የጀመረውን የመዋጀት፣ የመቀደስና የማንጻት ሥራ እየሰራ ነው። ክርስቶስ የቤተ ክርስቲያን - የኣካሉ ራስ ነው ስንል፣ አካሉን የሚገዛና የሚያስተዳድር ነው ማለታችን ብቻ ሳይሆን፤ ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔርን በፍጥረቱ መካከል የምታወርድ - የምትገልጥ መቅደስና ድንኩዋን እንድትሆን፤ በሕይወቱ ሙላት፣ በቅድስናው ውበት፣ በጽድቁ ልክና መጠን… የሚያንጻትና የሚያዘጋጃትም እርሱ ራሱ ነው ማለታችን ነው። በሞቱ ከእግዚአብሔር ጋር ያስታረቀንን እኛን በሕይወቱ ያድነናል - ቅዱሳንና ፍጹማን አድርጎም በአባቱ ፊት ያቀርበናል። ይሄ ደግሞ የማንም ልመናና ምልጃ የሚፈጽመው ሳይሆን፣ ክርስቶስ ራሱ በሰማያት (በመንፈሳዊ ክብሩ) ባለው የሊቀ ክህነት አገልግሎቱ ብቻ የሚከናወን ነው።      
“እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁ ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ፣ (to present you holy and without blemish and UNREPROVEABLE before him) በፊት የተለያችሁን ክፉ ሥራችሁንም በማድረግ በአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ፣” (ቆላ.1።21-22)

በዚህም የከበረ ሰማያዊ አገልግሎቱ በምድር ያከበረውን አባቱን ዛሬም በሚበልጥ ክብርና ኃይል በመንፈሳዊ አካሉ - በቤተ ክርስቲያን - በወንድሞቹ መካከል ሆኖ እያከበረው ነው። “የሚቀድሰውና የሚቀደሱት ሁሉ ከአንድ ናቸውና፤ ስለዚህም ምክንያት፡- ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ በማኅበርም መካከል በዜማ አመሰግንሃለሁ…” ያለው ክቶ ማነው??? (ዕብ.2፡13)

የክርስቶስ ሊቀ ክሕነትና እውነተኛይቱ ድንኩዋን!! (ክፍል 2)

በክፍል አንድ መልእክታችን፣ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰማያዊ ሊቀ ክህነት ለምን በመልከ ጼዴቅ ሹመት ወይም ሥርዓት እንደሆነ በጥቂቱ ለማየት ሞክረናል። መልከ ጼዴቅ የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካሕን በመሆኑ፣ በሰማያት በግርማው ቀኝ የተቀመጠው የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎትም እነዚህን ሁለት የአገልግሎት ሹመቶች (Offices) ማለትም ንግሥናንና ክህነትን የያዘና ያጠቃለለ እንደሆነም ተመልክተናል። ጨምረንም ሰማያዊው ሊቀ ካህን ይህን ሰማያዊ አገልግሎቱን የሚፈጽምባት ማለትም በንግሥናው የሚገዛትና በክህነቱ የሚያነጻት፤ የምትበልጥ፣ የምትሻል፣ በሰው እጅ ያልተተከለችና ያልተሰራች፣ ለዚህ ፍጥረት ያልሆነች… የተባለችው “እውነተኛይቱ ድንኩዋን” ከብዙዎች ዓይን እንደተሰወረች አመልክተን ነገር ግን የዚችን መንፈሳዊትና ሰማያዊት ድንኩዋን ምንነት እንድንረዳ፣ እንደ ምሳሌና ጥላ ያገለገለችውንና በቀደመው ኪዳን የነበረችውን ድንኩዋን በእርስዋም ውስጥ ይደረግ ስለነበረው አገልግሎት በጣም በጥቂቱ ተመልክተን ነበር።

በቀደመው ኪዳን በነበረው አገልግሎትና የአገልግሎት ሥርዓት ምሳሌነትና አስረጂነት የተገለጠው የእግዚአብሔር መንፈሳዊና ዘላለማዊ ሥርዓት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ መንፈስ የሆነው አምላካችን እጅግ ጥልቅ የሆነውን ሰማያዊ ሀሳቡን ለእኛ ለማስረዳት በዙሪያችን ያሉና በፍጥረታዊ አዕምሮ ልንረዳቸው የምንችላቸውን ቃላት ይጠቀማል።  የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፣ የእግዚአብሔር መቅደስ፣ የእግዚአብሔር ቤት፣ የእግዚአብሔር ሕንጻ፣ የእግዚአብሔር እርሻ፣ የእግዚአብሔር ድንኩዋን፣ የእግዚአብሔር ከተማ፣ የእግዚአብሔር ገነት፣ የእግዚአብሔር መንግሥት፣ የእግዚአብሔር ዙፋን------ እነዚህ ሁሉ ስለአንድ መንፈሳዊ አካል የተነገሩ የተለያዩ መገለጦች (Manifestations)፣ በተለያየ መንፈሳዊ ከፍታ ላይ ስለሚገኝ አንድ ሕዝብ - የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚናገሩና እጅግ የጠለቀ መንፈሳዊ ምሥጢር የያዙ፣ ነገር ግን በፍጥረታዊ ቁዋንቁዋ የተነገሩ መንፈሳዊ እውነታዎች መሆናቸውን የምትረዱበትን የጥበብና የመገለጥ መንፈስ እንዲሰጣችሁ በአምላኬ ፊት እንበረከካለሁ።

እግዚአብሔር መንፈስ በመሆኑ ምክንያት፣ እርሱ የሚኖርበትን የመንፈሳዊ ዓለም እውነታዎች በፍጥረታዊ አእምሮ ሊረዱትም ሆነ በፍጥረታዊ ቃላት ሊገልጡት አስቸጋሪ ነው። መንፈስ የሆነው እግዚአብሔር የሚኖረው ማንም ሊያየው በማይችል ብርሐን ውስጥ - በሰማያት - በመንፈሳዊ ከፍታዎች ላይ ነው። እኛ ደግሞ በአዳም በሆነው አለመታዘዝ ምክንያት ከእርሱ ተለይተን ወደዚህ ድቅድቅ ጨለማና ኃጢአት ወደሞላበት ምድር ወድቀናል። ሰለዚህም መንፈሳዊውን እውነታ የምንረዳበትም ሆነ የምናስተውልበት አቅም የለንም። አዳም ከመውደቁና ከእግዚአብሔር ከመለየቱ በፊት ያደርግ እንደነበረውም የእግዚአብሔርን ድምጽ መስማት አንችልም።

የሰው ቁዋንቁዋ መንፈሳዊውን እውነታ እንዳንረዳ በእኛና በመንፈሳዊው ዓለም መካከል ቆሞ የሚከላከል ትልቅ አጥር (barrier)ነው። መንፈሳዊውን ነገር በፍጥረታዊ ቃል ለመግለጽም ሆነ ለመረዳት አስቸጋሪ ብቻ ሳይሆን ሕገ ወጥም ነው። ጳውሎስ ወደ ሦስተኛው ሰማይ - ወደ ገነት - ከፍ ወዳለው መንፈሳዊ መገለጥ በተነጠቀ ጊዜ “ሰው ሊናገር የማይገባውን የማይነገረውን ቃል” (Inexpressible words which is NOT LAWFUL for a man to utter) እንደሰማ ተናገረ። ስለዚህም “ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለሆነ ሊያውቀው አይችልም። መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል፣ ራሱ ግን በማንም አይመረመርም። እንዲያስተምረው የጌታን ልብ ማን አውቆት ነው? እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።” በማለት አንድ ሰው መንፈሳዊውን ነገር ሊረዳም ሆነ ሊመረምር ስለሚችልበት አንድ ልብ ወይም መንፈሳዊ አእምሮ - ስለክርስቶስ ልብ - the mind of Christ. ተናገረ። (2ቆሮ. 12፡1-5 1ቆሮ.2፡14-16)

ስለዚህ ሰው በዳግመኛ ልደት ብቻ ሊገኝ በሚችለው በዚህ አዲስ ልብና መንፈስ ጎልምሶና ጠንክሮ የእግዚአብሔርን መንፈስ ነገር በሙላት ወደሚረዳበት መንፈሳዊ ከፍታ እስኪወጣ ድረስ፣ እግዚአብሔር በዙሪያችን የሚገኙትን ፍጥረታዊ ነገሮች እየተጠቀመ ስለመንፈሳዊው ዓለም እውነታዎች ያስረዳናል። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ይከተለው ለነበረው ሕዝብ የእግዚአብሔር መንግሥት ምን እንደምትመስል ለማስረዳት “የእግዚአብሔርን መንግሥት በምን እንመስላታለን? ወይስ በምን ምሳሌ እንመስላታለን?” እያለ፣ በዙሪያቸው ሊያዩአቸው በሚችሉ እና ከየዕለት ኑሮአቸው ጋር በእጅጉ የተቆራኙ ነገሮችን እየተጠቀመ ሲያስረዳቸው እናያለን። ሰማይ፣ ምድር፣ ወንዝ፣ ቤት፣ በር፣ ገበሬ፣ ዘር፣ እርሻ፣ ውሀ፣ ባህር፣ በግ፣ ፍየል፣ ተራራ፣ ሸለቆ፣ እባብ፣ ዘንዶ፣ ባል፣ ሚስት፣ ጋለሞታ፣ ሴት፣ ወንድ ልጅ፣ ከተማ፣ አውሬ፣ ዙፋን…. እነዚህና የመሳሰሉት ሌሎች በዙሪያችን የምናውቃቸው ነገሮች ሁሉ በመጽሐፍ ቅዱሳችን (በተለይም በዮሃንስ ራዕይ መጽሐፍ ውስጥ) በተለያየ ጊዜ የተጠቀሱና መንፈሳዊውን ነገር ማየት እንድንችል የእግዚአብሔር መንፈስ እንደምሳሌነት የተጠቀመባቸው የሰው ቃላቶች ናቸው።

ታድያ እነዚህን መንፈሳዊውን እውነታ እንድናስተውል የሚጠቅሙንን ምልክታዊ ቃላት፣ በመደዴው (Literally) ከተረዳናቸው ወይም አጣመን ከተረጎምናቸው እግዚአብሔር ሊገልጥልን ከሚፈልገው እውነት እንስታለን። ለዚህም ነው ዛሬ በዚህ “በመጨረሻው ዘመን” የምንገኝ ክርስቲያኖች በተለይም የዮሃንስን ራዕይ መጽሐፍ የተረዳንበት መንገድ በእጅጉ የተዛባ በመሆኑ፣ ….በቅርብ ዓመታት ውስጥ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ “በአምባላይ ፈረስ” ላይ ተቀምጦና ዕልፍ አዕላፍ ሰራዊቱን አስከትሎ ወደዚህ ምድር በመምጣት፣ በመካከለኛው ምሥራቅ በምትገኘው የኢየሩሳሌም ከተማ የመጨረሻውንና “አርማጌዶን” የተባለውን ጦርነት ከታላለቅ የአሕዛብ ነገሥታት ጋር አድርጎና ድል ነስቶ፣ ከዚያም  መንግሥቱን በእሥራኤል ምድር እንደገና መስርቶና “በዳዊት ዙፋን ላይ” ተቀምጦ ዓለምን ሲያስተዳድር ለማየት የምንጠብቀው። ወይም ደግሞ ሌሎቻችን በዚህ ምድር ላይ ሊመጣ ካለው “ታላቅ መከራ” ለማምለጥ “በአየር ተነጥቅን”፣ በሰማያት ካለው ንጉሳችን ጋራ “በአየር ተገናኝተን” እና፣ በሰማያዊው ንፍቀ - ዓለም (Universe) ውስጥ በምትገኝና “አዲሲቱ ኢየሩሳሌም” ተብላ በምትጠራ አንዲት በወርቅና በተለያዩ የከበሩ ድንጋዮች በተንቆጠቆጠች ከተማ ውስጥ ዘላለማዊ ኑሮአችንን ለመጀመር “የመነጠቃችንን” ወይም ደግሞ ቀናችን ደርሶ የምንሞትበትን ጊዜ በጉጉት የምንጠብቀው።

“አዲስ ሰማይና አዲሰ ምድርንም አየሁ፣ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፣ ባሕርም ወደፊት የለም። ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ለባልዋ እንደተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ። ታላቅም ድምጽ ከሰማይ፡- እነሆ የእግዚአብሔር ድንኩዋን በሰዎች መካከል ነው፤ ከእነርሱም ጋር ያድራል፣ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤ እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፣ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፣ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።” (ራእይ.21፡1-4)  

የክርስቶስ ሊቀ ክህነትና እውነተኛይቱ ድንኩዋን!! (ክፍል 1)

by Tibebe Belay  ·

“እንግዲህ ክርስቶስ ደግሞ ሊቀ ካህናት ሊሆን ራሱን አላከበረም፤ ነገር ግን፡- አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ ያለው እርሱ ነው፤ እንደዚሁም በሌላ ሥፍራ ደግሞ፡- አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ ይላል። እርሱም በሥጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትና ምልጃን አቀረበ፣ እግዚአብሔርን ስለመፍራቱም ተሰማለት፤ ምንም ልጅ ቢሆን ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤ ከተፈጸመም በሁዋላ በእግዚአብሔር እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ስለተጠራ ለሚታዘዙለት የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው። , (And being perfected, he became the source of eternal salvation for all who obey him, having been designated by God to be a high priest according to the order of Melchizedek.) ዕብ.5፡5-10

የክርስቶስ የሊቀ ክህነት አገልግሎቱ የጀመረው ለዓለም ሁሉ የኃጢአት ማስተሰሪያና ቤዛ አድርጎ ራሱን በመስቀል ላይ ባቀረበ ጊዜ ቢሆንም፣ በመልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ የተጠራው ግን ሁሉን ፈጽሞና ከሞት ተነስቶ በእግዚአብሔር ቀኝ ከተቀመጠ በሁዋላ ነው። ለዚህም ነው “በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህን አለን፣ እርሱም የመቅደስና የእውነተኛቱ ድንኩዋን አገልጋይ ነው…” በማለት የዕብራውያን ጸሐፊ የነገረን።

ክርስቶስ በዙፋን ላይ የተቀመጠ ሊቀ ካህን የሆነበትን ምክንያት መረዳቱ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። እርሱ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ “ሊቀ ካሕናት” ተብሎ የተጠራበት ሥርዓት የአሮን ሳይሆን የመልከ ጼዴቅ መሆኑ ይህን የከበረ እውነት ለመረዳት የሚያስችለንን አንዳች ምሥጢር ይዞአል። በብለይ ኪዳኑ ሥርዓትና አገልግሎት የክህነቱ ሥልጣን የሌዊን ዘር ብቻ ተከትሎ የሚሄድ ሲሆን፣ ነገሥታት የሚሾሙት ደግሞ ከይሁዳ ነገድ ብቻ ነበር። በዚህ በአዲሱ ኪዳን መንፈሳዊ ሥርአት ግን አንዱ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለቱንም ማለትም ንጉሥነቱንም ሆነ ክህነቱን በአንድነት የጠቀለለበት ምክንያት፣ የክህነት ሹመቱ በመልከ ጼዴቅ ሥርዓት በመሆኑ ነው። በእግዚአብሔር ልጅ የተመሰለው መልከ ጼዴቅ ደግሞ “የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን” ነው። (ዕብ.7፡1-3)

ስለዚህ እግዚአብሔር “አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ” ብሎ የማለለት አንድያ ልጁ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በዙፋን ላይ ሲቀመጥ የነገሥታት ንጉስ ወይም ፈራጅ ሆኖ ብቻ ሳይሆን፣ ስለሕዝቡ ድካም የሚማልድ ሊቀ ካህንም ሆኖ ነው ማለት ነው። ይህ የከበረ እውነት ከብዙ ወንድሞቻችን አእምሮ በመሰወሩ ምክንያት ነው “ዛሬ ክርስቶስ የሚፈርድ ንጉሥ እንጂ የሚማልድ ካህን አይደለም” ወደሚል ስሕተት ውስጥ የገቡት። የገዛ ስህተታቸውን ለማጽደቅ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ላይ በግልጽ የተጻፉትን ቃላት እስከ መለወጥ የሚደርስ ሌላ ትልቅ ስህተት መፈጸማቸው ግን ወደ ፍርድ የሚመራ ድፍረት በመሆኑ “ከተጻፈው አትለፍ” የሚለው ሐዋርያዊ ምክር ከዚህ ፍርድ እንዲያድናቸው እንጸልያለን።

በራዕይ መጽሐፍ ምዕራፍ አምስት ላይ እንደምናነበው፣ መጽሐፉን የዘረጋውና ማሕተሙን የፈታው ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፤ በዙፋኑ፣ በአራቱ እንሰሶችና በሽማግሌዎቹ መካከል እንደታረደ በግ ቆሞ መታየቱ የሚገርም ነው። አንበሳው በግ ነው፤ በጉም አንበሳ ነው። ንጉሡ ካህን ነው፣ ካህኑም ንጉሥ ነው። የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የነገሥታት ንጉስና የካህናት አለቃ ነው። እነዚህ ሁለት መጠሪያዎች ግን የተሰጡት ያለ አገልግሎት አይደለም። በአብ ቀኝ የተቀመጠው የነገሥታት ንጉሥ የአካሉ - የቤተ ክርስቲያን ራሰ በመሆኑ አካሉን በመንፈሱ እየገዛና እያስተዳደረ መሆኑ የማያጠራጥር እውነት እንደሆነ ሁሉ፤ ይህቺኑ አካል ነውርና ነቀፋ የሌላት ቅዱስ አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት ለማቅረብ እየተጋ መሆኑም ልንረዳው የተገባ እውነት ነው። በሰማያት በግርማው ቀኝ የተቀመጠውና በመልከ ጼዴቅ ሹመት የዘላለም ሊቀ ካህን የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ “የእውነተኛይቱ ድንኩዋን አገልጋይ” የሆነበትም ምሥጢር ይኸው ነው። ሆኖም አገልግሎቱን የሚፈጽምባት ማለትም በንግሥናው የሚገዛትና በክህነቱ የሚያነጻት ይቺ ድንኩዋን ከብዙዎች ዓይን ተሰውራለች።     

“ነገር ግን ክርስቶስ ይመጣ ዘንድ ላለው መልካም ነገር ሊቀ ካህናት ሆኖ፣ በምትበልጠውና በምትሻለው በእጆችም ባልተሠራች ማለት ለዚህ ፍጥረት ባልሆነች ድንኩዋን የዘላለም ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም። የኮርማዎችና የፍየሎች ደም በረከሱትም ላይ የተረጨ የጊደር አመድ ሥጋን ለማንጻት የሚቀድሱ ከሆኑ፣ ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን??” (ዕብ.9፡11-14)

ክርስቶስ የገዛ ደሙን ይዞ የገባው፣ ደሙ የፈሰሰበት የማንጻትና የመቀደስ ዓላማ ወደሚፈጸምበት ሥፍራ ነው። በዚሁ በዕብራውያን ምዕራፍ ዘጠኝ ከቁጥር አሥራ ዘጠኝ ጀምሮ እንደምናነበው፣ በቀደመው ኪዳን ሙሴ የጥጆችንና የፍየሎችን ደም የረጨው በድንኩዋኒቱና በማገልገያው ዕቃ ሁሉ ላይ  ነው። በመሆኑም ድንኩዋኒቱም ሆነ የማገልገያ ዕቃዎቹ ሁሉ ከተረጩት ደም የተነሳ በመንጻታቸውና በመቀደሳቸው እግዚአብሔር ይመለክባቸውና ይከብርባቸው ዘንድ ብቁ ይሆኑ ነበር ማለት ነው። የሙሴ ድንኩዋን ምሳሌና ጥላ ሆና ያገለገለቻትና የምትበልጥ፣ የምትሻል፣ በሰው እጅ ያልተተከለችና ያልተሰራች፣ ለዚህ ፍጥረት ያልሆነች… የተባለችውም እውነተኛይቱ ድንኩዋን እግዚአብሔር ይመለክባትና ይከብርባት ዘንድ፣ ከፍየሎችና ከጥጆች ደም እጅግ በሚበልጥና በከበረ ደም መንጻት አለባት። ታድያ፣ ክርስቶስ የዘላለም ቤዛነትን አግኝቶና ነውር የሌለበትን ክቡር ደሙን ይዞ የገባው ወዴት ነው?? ይሄ ክቡር ደም የፈሰሰውስ ማንን ሊያነጻና ሊቀድስ ነው??

“ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን??”         

Wednesday, June 27, 2012

እግዚአብሔር ሥራውን ይመዝናል - ጥቂት ስለ እግዚአብሔር ፍርድ!!

በዘመናት ውስጥ በምድር ላይ ከኖሩት ሰዎች መካከል በትህትናቸው የተመሰከረላቸው ሰዎች የመኖራቸውን ያህል ደግሞም በትዕቢታቸው ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች የወደቁ ሰዎችን ታሪክ አንብበናል። ከእነዚህ ትዕቢተኞች መካከል እንደባቢሎኑ ንጉስ- ናቡከደነፆር ከፍተኛው የትዕቢት ደረጃ ላይ የደረሰ ማንም አልነበረም። በትንቢተ ዳንኤል መጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበውን ታሪኩን እንደምናነበው ከአሕዛብ ነገሥታት መካከል እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ ያደረገው ደግሞም ያለ ልክ ያዋረደው እንደ ናቡከደነፆር ያለ ንጉስ ማንም የለም።

የንጉሱ ናቡከደናፆር ትዕቢት እጅግ በጣም ከፍተኛው ደረጃ ላይ መድረሱ የታወቀው፣ ከፍ ባለው የቤተ መንግሥቱ ሰገነት ላይ ቆሞ ፣ “… ይህቺ እኔ በጉልበቴ ብርታት ለግርማዬ ክብር የመንግሥት መኖሪያ እንድትሆን ያሠራህዋት ታላቂቱ ባቢሎን አይደለችምን?” ብሎ በተናገረበት ጊዜ ነበር። እጅግ አስፈሪውም የእግዚአብሔር ፍርድ በዚህ ትዕቢተኛ ንጉስ ላይ የመጣው ይሄው የትዕቢት ቃሉ ከአፉ በወጣበት ቅጽበት ነበር። ልቡ ከሰው ልብ ተለወጠ፣ የአውሬም ልብ ተሰጠው፣ ጠጉሩም እንደንስር ጥፍሩም እንደወፎች እስኪረዝም ድረስ ከሰዎች ተለይቶ ተሰደደ፣ እንደበሬም ሳር በላ፣ አካሉም በሰማይ ጠል ረሰረሰ። አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ! ፍርድህ እንዴት አስፈሪ ነው!! ደግሞም ጽድቅ የተትረፈረፈበት ነው!!!!

እግዚአብሔር ሥራውን የሚመዝን፣ በጥበብና በማስተዋል የተሞላ፣ ለዕውቀቱም ወሰን የሌለው ድንቅ አምላክ ነውና በዚህ ትዕቢተኛ ንጉስ ላይ እንዲህ አይነቱን አስፈሪ ፍርድ ሲበይን ግን ያለ ዓላማ አልነበረም። በዚህ አስፈሪ ፍርድ ውስጥ የነበረው የልዑሉ ዓላማና ፍርዱም የሚጸናበት ጊዜ ለንጉሱ እንዲህ ተነቦለት ነበር።
“ልዑሉም በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሠለጥን፣ ለሚወደውም እንዲሰጠው እስክታውቅ ድረስ ከሰዎች ተለይተህ ትሰደዳለህ፣ መኖሪያህም ከምድር አራዊት ጋር ይሆናል፣ እንደ በሬም ሣር ትበላ ዘንድ ትገደዳለህ፣ ሰባት ዘመናትም ያልፉብሃል።” (ዳን.4፡32)

የሰው ልጆች፣ በተለይም ሐይማኖተኞች ስለ እግዚአብሔር ፍርድ ሲያስቡ ቶሎ ብሎ ወደልባቸው የሚገባው ማለቂያና ፍጻሜ የሌለው የእግዚአሔር ቁጣና ጭካኔው እንጂ፣ ጽድቅ በተትረፈረፈበት ፍርዱ ውስጥ የሚያገኝው ክብርና በትዕቢተኞችና በዐመፀኞች ሕይወት ውስጥ የሚያመጣው የከበረ የማንነትና የሕይወት ለውጥ አይደለም። የዚህ ስህተት መነሻና ምንጩ ደግሞ ከሰባኪዎቻቸው የሚሰሙት ቅጥ የሌለው ዛቻና ማሰፈራሪያ ነው። ከእግዚአብሔር የፍርድ እጅ በታች የመውደቅን አስፈሪነትም ሆነ ከዚህ ክቡር እጅ በታች ከወደቁ በህዋላ የሚገኘውን የሕይወት ለውጥ ሊናገር የሚችል እንደናቡከደናፆር ያለ ሰው ማንም የለም። ለሰባት ዘመን (የዘመኑ ቁጥር ፍጹሙን የእግዚአብሔር አሰራር ያሳየናል) የቆየው የእግዚአብሔር ፍርድ አዲሱን ናቡከደነፆር እንዲህ ይገልፀዋል፡-
“ዘመኑም ከተፈጸመ በህዋላ እኔ ናቡከደነፆር ዓይኔን ወደሰማይ አነሳሁ፣ አእምሮዬም ተመለሰልኝ፣ ልዑሉንም ባረክሁ፣ ለዘላለም የሚኖረውን አመሰገንሁ፣ አከበርሁትም፣ ግዛቱ የዘላለም ግዛት ነውና። በምድርም የሚኖሩ ሁሉ እንደምናምን ይቆጠራሉ፣ በሰማይም በሚኖሩ መካከል እንደ ፈቃዱ ያደርጋል፣ እጁንም የሚከለክላት ወይም፡- ምን ታደርጋለህ የሚለው የለም። በዚያን ጊዜም አእምሮዬ ተመለሰልኝ፣ ለመንግሥቴም ክብር ግርማዬና ውበቴ ወደ እኔ ተመለሰ፣ አማካሪዎቼና መክዋንንቶቼም ፈለጉኝ፣ በመንግሥቴም ውስጥ ጸናሁ፣ ብዙም ክብር ተጨመረልኝ። አሁንም እኔ ናቡከደነፆር የሰማይን ንጉሥ አመሰግናለሁ፣ ታላቅም አደርገዋለሁ፣ አከበረውማለሁ። ሥራው ሁሉ እውነት፣ መንገዱም ፍርድ ነውና፣ በትዕቢትም የሚሄዱትን ያዋርድ ዘንድ ይችላልና።” (ዳን.4፡34-37)

ከሰባቱ ዘመን ፍርድ በህዋላ የተገኘው ናቡከደነፆር ይሄ ነው። ልዑሉ በሰዎች መንግሥት ላይ የሚሰለጥን፣ መንግሥትንም ለሚወደው የሚሰጥ፣ ግዛቱም የዘላለም ግዛት የሆነ፣ በሰማይና በምድር መካከል እንደ ፈቃዱ የሚያደርግ፣ ትዕቢተኞችን የሚያዋርድ፣ ለትሁታኑ ፀጋን የሚሰጥ አምላክ መሆኑን የሚያውቅ ናቡከደነፆር!! እግዚአብሔርን የሚያመልክ፣ የሚያከብርና የሚያመሰግን ናቡከደነፆር!! አዲሰ ልብና አዲስ አእምሮ ከውበት ከመንግሥት ክብርና ግርማ ጋር የተመለሱለት ናቡከደነፆር!! እጅግ በጣም የሚገርመው ነገር ግን እንዲህ አይነቱ ሰው የተገኘው “የእግዚአብሔር ሕዝብ” ተብለው ከሚጠሩት እሥራኤላውያን መካከል አልነበረም!!!!!

“አትታበዩ ፣ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፣ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና…..
እግዚአብሔር ይገድላል ============  ያድናልም፣
ወደ ሲዖል ያወርዳል ==============  ያወጣል።
እግዚአብሔር ድሀ ያደርጋል ========= ባለጠጋም ያደርጋል፣
ያዋርዳል========================  ደግሞም ከፍ - ከፍ - ከፍ - ከፍ ያደርጋል”  (1ሳሙ.2፡3-7)

በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ በጽድቅ ይፈርድ ዘንድ ሥልጣንን ከአባቱ የተቀበለው የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱሰ ክርስቶሰ እንዲህ ይላል፡-
“… ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፣ ሞቼም ነበርሁ እነሆም ከዘላለም እስከ ዘላለም ሕያው ነኝ ፣ የሞትና የሲዖል መክፈቻ አለኝ።”  (ራዕ.1፡18)

'ነጻ ፈቃድ - Free will' ያለው ማነው???

by Tibebe Belay  ·

“ለሰው ልጅ የተሰጠውን ነጻ ፈቃድ እግዚአብሔርም ሆነ ሰይጣን አይጋፉትም። ይህ ማለት እግዚአብሔር በግድ ሰዎችን አያጸድቅም። ሰይጣንም በግድ ሰዎችን ኃጢአት አያሰራም። «ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል።» ያዕ ፩፡ ፲፬። እግዚአብሔር የመዳን (የሕይወት) ጥሪ፡ ሲያቀርብ ሰይጣን የኃጢአት (የሞት) ጥሪ ያቀርባል። ሰው ከሁለቱ አንዱን መምረጥ ይችላል። የመረጠውን ነገር ውጤት ግን ይቀበላል እንጂ አይመርጥም።”

የዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ ከላይ የምታነቡት በእሕት ታምረ ጽዮን የቀረበው ሀሳብ ነው። በመሰረቱ ይህ ሀሳብ ሁሉም ሐይማኖቶች የሚቀበሉት ሲሆን በዘመናት መካከል እየዳበረ የመጣና በሁሉም ዘንድ እውነትነቱ ጥርጥር የሌለው እስኪመስል ድረስ ተቀባይነትን ያገኘ ሃሳብ ነው። ነገር ግን እውነቱ ከብዙዎች ተሰውሮአል። ይህን ለመረዳት እንዲህ ብለን እንጠይቅ፣ የሰው ልጅ ነጻ ፈቃድ አለው?? በእርግጥ ነጻ ፈቃድ ያለው ማነው??

“… እኔ ግን ከኃጢአት በታች ልሆን የተሸጥኩ የሥጋ ነኝ። የማደርገውን አላውቅምና፤ የምጠላውን ያን አደርጋለሁና ዳሩ ግን የምወደውን እርሱን አላደርገውም።” (ሮሜ.7፡14-15)
እግዚአብሔር አዳምን ፈጥሮ በዔደን ገነት ሲያኖረው በሞትና በሕይወት መካከል መምረጥ የሚችል ነጻ ፈቃድ ያለው ፍጡር አድርጎት ነበር። ለዚህም ነው “… ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ።” የሚል ትዕዛዝ የሰጠው። ነገር ግን አዳም በእባቡ ተንኮል፣ በሴቲቱም መታለል ምክንያት ሞትን መረጠ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የሰው ዘር በሙሉ፣የቀደመው አባቱ አዳም በመረጠለት በዚህ ክፉ ምርጫ ሰበብ የኃጢአትና የሞት ባሪያ ሆኖ በምድር ላይ መብዛቱን ጀመረ። ታድያ፤ ማነው ይህን የወደቀ ሰው በሞትና በሕይወት፣ በመልካምና በክፉ፣ በጽድቅና በኃጢአት… መካከል መምረጥ የሚችልበት “ነጻ ፈቃድ”፣ መርጦም የወደደውን ማድረግ የሚችልበት ኃይልና ጉልበት ያለው ፍጡር ነው ብሎ የሚከራከር?? ሰው ሁሉ ኃጢአትን እያደረገ የሚሞተው በራሱ ፈቃድና ምርጫ ነው ብሎ የሚያስብ፣ ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም መግባቱን፣ በኃጢአትም ምክንያት ሞት ለሰው ሁሉ መድረሱን፣ ደግሞም “ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ...” ተብሎ መጻፉን መጽሐፉን ገልጦ ያንብብ!!!

እስራኤላውያን ለአራት መቶ አመታት በግብጽ ምድር በነበሩበት ጊዜ ሁሉ የፈርዖን ባሪያዎች ነበሩ። ነጻ አውጪው ሙሴ እስኪመጣ ድረስ በዚያ የባርነት ምድር በእግር ብረት ታስረው የፈርዖንን ጡብ ከመጠፍጠፍ ውጪ ሌላ ምን ምርጫ ነበራቸው?? ሰለዚህም “አባቶቻችሁ በግብጽ ምድር በባርነት በነበሩ ጊዜ…” ተብሎ ተጻፈባቸው። የወደደውን ማድረግ ለማይችልና በባርነት ላለ ሕዝብ የሚያስፈልገው ቀንበሩን ሰብሮ ነጻነቱን የሚያውጅለት ነጻ አውጪ እንጂ “ምርጫ” አይደለም። (በረሀብ ይሰቃይ ለነበረ ሕዝብ ‘ለምን ኬክ አይበሉም’ የሚል ‘የምግብ ምርጫ’ ያቀረበችውን ልዕልት ስም ረሳሁት) ለዚህም ነው እግዚአብሔር “በግብጽ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፣ ከአስገባሪዎቻቸውም የተነሳ ጩኸታቸውን ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም አውቄአለሁ፣ ከግብጻውያንም እጅ አድናቸው ዘንድ…..” ብሎና ሙሴን ለዚህ ዓላማ አስነስቶ “በበረታችና በፀናች ክንድ” ሕዝቡን ከግብጽ ምድር አውጥቶ በምድረ በዳው መንገድ ወደተስፋይቱ ምድር የመራቸው።

እዚህ ላይ አንድ የከበረ እውነት ላካፍላችሁ!! ከላይ እንዳልኩት በባርነት ላለ ሕዝብ የሚያስፈልገው ነጻ አውጪ እንጂ “ምርጫ” አይደለም። ይህን የሚያውቀው የእስራኤል አምላክ ለሕዝቡ የሕጉን ትዕዛዝ የሰጣቸው ደግሞም የሕይወትና የሞት፣ የበረከትና የመርገም…. ምርጫዎችን በፊታቸው ያቀረበው በግብጽ ምድር በባርነት ባነበሩበት ጊዜ ሳይሆን፣ በጸናችና በበረታች ክንድ ከዚያ የባርነት ምድር አውጥቶአቸው በምድረ በዳው በኩል ወደተስፋይቱ ምድር ይመራቸው በነበረበት ጊዜ ነው።
“በፊታችሁ ሕይወትንና ሞትን፣ በረከትንና መርገምን እንዳስቀመጥሁ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ። እንግዲህ አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጥ፤ እግዚአብሔርም ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም እነዲሰጣቸው በማለላቸው በምድሪቱ ትቀመጥ ዘንድ እርሱ ሕይወትህ የዘመንህም ርዝመት ነውና አምላክህን እግዚአብሔርን ትወደው ትጠባበቀውም ቃሉንም ትሰማ ዘንድ ምረጥ።” (ዘዳ.30፡19-20)

“የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው። ለድሆች የምስራች እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፣ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፣ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።” (ኢሳ.61፡1)
ይህ ከሁሉ አስቀድሞ በራሱ በወንጌሉ ባለቤት በክርስቶስ ከዚያም በዘመናት ሁሉ መካከል የወንጌል ሰባኪነትን አደራ በተቀበሉና በእግዚአብሔር መንፈስ ተቀብተው በተላኩ እውነተኛ የቃሉ አገልጋዮች የተሰበከና የሚሰበክ “የመንግሥት ወንጌል” ነው። በእግዚአብሔር መንፈስና ኃይል ብቻ ሊነገር የሚችለውና ሌላ ማንንም ሳይሆን ክርስቶስን ብቻ የሚሰብከው ይህ ወንጌል ለሰዎች ሲነገር አስቀድሞ የሚያደርገው የሚሰሙትን ሁሉ ከዚህ ዓለም ባርነትና ከሰይጣን እስራት መፍታት ነው። ሰው አስቀድሞ የእግዚአብሔር የማዳኑ ኃይል በሆነው የክርስቶስ ወንጌል ከሰይጣን ባርነት ካልተፈታ፣ በዓለም እስር ቤት ውሰጥ ያለና ከኃጢአት በታች እንዲሆን ለገዛ ስጋው የተሸጠ ባሪያ ነው። ያኔ በጸናችውና በበረታችው የእግዚአብሔር ክንድ አማካኝነት ቀይ ባህር ተከፍሎላቸው ከፈርዖን ሰራዊት ያመለጡትና፣ “ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባህር ጣለ!” የሚል የነጻነት መዝሙር እየዘመሩ ወደተሰጣቸው የበረከት ምድር መትመም እንደጀመሩት እስራኤላውያን፤ ይህን ወንጌል ሰምተው በእውነት ከሰይጣን እስራት የተፈቱ ወገኖች ብቻ፣ “በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አውጣን!!...” የሚለውን የአዲሰ ኪዳን የነጻነት መዝሙር ሊዘምሩ ይችላሉ። ይህ ነጻነታቸውም የሚመራቸው አግዚአብሔርን በመስማትና በመታዘዝ ወደሚወረሰው የዘላለም ሕይወት ተስፋ ነው። አሁን ከላይ ለጠየቅነው ጥያቄ መልስ እንስጥ!!! በእርግጥ በሞትና በሕይወት፣ በጽድቅና በኃጢአት፣ በበረከትና በመርገም፣ በመልካምና ክፉ…. መካከል የመምረጥ ነጻነትን ያገኙት እነዚህ የክርስቶስን ወንጌል በመቀበል ከአግዚአብሔር መንፈስ ዳግመኛ የተወለዱ የእግዚአብሔር ልጆች ብቻ ናቸው።

“እንግዲህ ወንድሞች ሆይ ዕዳ አለብን፣ እንደሥጋ ፈቃድ ግን እንኖር ዘንድ ለሥጋ አይደለም። እንደሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞቱ ዘንድ አላችሁና፤ በመንፈስ ግን የሰውነትን ሥራ ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ። በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።” (ሮሜ.8፡12-14)

Tuesday, June 26, 2012

The Savior of The World

By J. Priston Eby Part.1

GOD HAS A PLAN!

AMONG all the questions that men have asked, there is one that is of supreme interest and importance. Why are we here? What is our destiny? What lies beyond the grave for the Christian, for the unbeliever? For old, for young? For our fellow citizens, and for the teeming masses in far-away lands serving strange gods? These questions were raised by one of the great poets of all times. I am speaking now of that American genius of letters, Edgar Allen Poe - an incomparable genius, and yet a man whose life was destroyed by unbelief. Millions of people have read his masterpiece, "The Raven," but few, I am afraid, have ever grasped the real spiritual significance of the struggle that was going on in the soul of this man. He asked four very significant questions - questions which every living soul, at one,' time or another, must raise to God. First, Is there a God who comforts? Is there a God who can assuage the pain of life? (In this case it is the poignant pain of the loss of a loved one, his beloved Lenore.) Is there "some water from the river of paradise, the water of Nephenthe," which can take away the heartache that is driving him insane? Secondly, he asks, Is there really a Christ? Does He live? Is there a balm in Gilead? Is there One who can smoothie the wrinkled brow and soften the hard heart? Thirdly, he asks, Is there some place, some heaven, some distant Eden or future world where we shall be joined again with our loved ones? And, finally, Is there any hope that the darkness and hopelessness and despair of this life will be lifted? But always he directs his questions to his own unbelief which is personified in that grim and ghastly raven, a picture of doubt and unbelief. A few years after writing those chilling words, Poe became insane. Regaining his sanity, he drank himself to death, and this genius was found dead in the gutter.
Untold billions of human beings have lived and died without hearing the gospel of salvation through our Lord Jesus Christ. What has become of them? Is there no hope? For more than six thousand years generations of men, like the grass, have appeared and in a few fleeting years withered and vanished. Whence came those countless billions of human beings, and where do they go? This is the problem which has preoccupied the world's thought since the dawn of history. This is the question about which philosophers have theorized and theologians have dogmatized. Unquestionably the problem of the eternal destiny of mankind is the question of questions! It concerns every individual and touches everything of enduring interest. Life is a vapor that appears for a while and vanishes away. But there is a beyond! What is that beyond to be?
God has a plan I Indeed, God has a wonderful plan for this world! It is a plan of which the architectural drawings were made in eternity. It encompasses the minutest detail of all of creation. I assure you that when time has run its course, and the veil is dropped upon the final scene, we shall discover that that plan has been worked out to its very tiniest detail, just as God had planned it in eternity - that His will has been done!
That is an amazing thought because it often seems as if the world is flying off unattended, like a chariot where the driver has fallen off, the horses are running wild, the reins are flapping in the breeze, and it is threatening to go over the precipice at any moment. Yet the Scriptures would have us know that God, the sovereign Lord of history, has His hands firmly upon those reins and that His plan is coming to pass. Think about it! Our God is perfect in all His attributes. He is perfect in His power. He is perfect in His holiness and justice. He is perfect in His love and mercy. He is perfect in His wisdom and in His omniscience. Therefore, His plan must be perfect. Indeed it is a perfect plan!
This is not to deny that the world is filled with many evils; that all about us we see that sin and evil and disease and death cling to man. It is not to shut our eyes to those realities, but it is to open our eyes to the realization that God sovereignly overwhelms all these things to bring about His own will. God has created this world. Even though Satan let chaos loose into the midst of the creation, God created Satan and God knew precisely what this angel of destruction would contribute. He knew of the chaos and the sin that would be introduced into the peaceful calm of those Elysium fields. Yet God created him anyway. God knew that with sin would come the perfect judgment of God upon that sin, which means sickness, death, judgment, disillusionment and decay. Yet, God ordained all these things so that He might overcome them for good.
Central to the whole plan of God is Jesus Christ and His greater glory, but even more amazing is the realization that God has planned for us to share His glory and to work out for us our good as well. God has a perfect plan. My friends, I want you to understand one thing. This plan needs no human support! In Madrid, Spain, there exists the Escorial, one of the greatest cathedrals ever built by man. For centuries the kings of Spain have been buried there. When that magnificent structure was under construction, the architect designed a vast arch, perhaps bigger than anything that had been built before. However, that arch was so flat at the top that the reigning king was frightened by the prospect of the tremendous weight of the roof collapsing on his head. He commanded the architect to build a column from the floor all the way to the center of that arch to hold it up. The architect protested vehemently that it was not needed, but the king insisted and, over the laments of the architect, the column was built. The king worshipped contentedly in the vast structure, having seen to it himself that the ceiling would not fall. The years went by, the church stood, and the king finally died. Only then did the architect reveal that between the top of the column and the bottom of the arch there was a quarter of an inch of space. In all these hundreds of years that have passed the arch has not sunk so much as a quarter of an inch. Today a board is still passed over the column and under the arch for all to see. So it is with the plan of God - that over-arching plan that encompasses all of reality and all of life. It needs no human support to hold it up. God is the LORD OF ALL and He is working out His purposes in our lives, in all of the world, and through the whole universe.
Read the words of that magnificent hymn: "God moves in a mysterious way His wonders to perform; He plants the footsteps in the sea, And rides upon the storm." What a beautiful hymn! Many people may not know how William Cowper was brought to write that hymn. His life was in shambles. He was not a Christian. He was filled with despair and discouragement. In fact, so overcome with despair was he that he determined to take his life by taking poison. Instead of dying, he became deathly ill. He bought a gun and tried to shoot himself, but the gun would not go off. In great anger, he threw the gun away, got a rope and tried to hang himself. The rope broke. So then, in utter desperation, he hired a carriage in London and instructed the driver to take him to the Thames River. The driver could not find the Thames River! The fog had settled in so thickly on the town that even a London cabdriver got lost! After several hours he brought Cowper back to his apartment. He went up to his room, totally dismayed, and his eyes fell upon a Bible. He opened that Bible and began to read. He read of the love of a heavenly Father who loved even William Cowper. Astonished by the events that had just taken place, he read of the sovereign providence of God working all things after the counsel of His own will. He embraced Him as his Saviour and wrote the wonderful words of that great hymn.
Perhaps I ought to state here for the benefit of some of my readers, that the idea that God HAS a plan may be to them a new one. According to the view of most Christians, God has no definite, prearranged plan, but is simply endeavoring to do the best He can through human instrumentality to repair the ruin that sin has made, and, though thus far the majority of the race have been overwhelmed in that ruin, yet in the end truth will triumph and sin will be confined in an eternal prison house.
As some ignorantly misjudge the skill and wisdom of a great architect and builder by his unfinished work, so also many in their ignorance now misjudge God by His unfinished work; but by and by, when the rough scaffolding of sin, death, and redemption has been removed, and the rubbish cleared away, God's FINISHED WORK will universally declare His infinite wisdom and power; and His plans will be seen to be in harmony with His glorious character.
Since God tells us that He has a definitely fixed purpose, and that all His purposes shall be accomplished, it behooves us, as His children, to inquire diligently what those plans are, that we may be found in harmony with them. Notice how emphatically the Lord affirms the fixedness of His purpose: "The Lord of hosts has sworn, saying, Surely as I have thought, so shall it come to pass; and as I have purposed, so shall it stand." "The Lord of hosts has purposed, and who shall disannul it?" "I am God, and there is none else; I am God, and there is none like me... My counsel shall stand, and I will do all My pleasure ... Yea, I have spoken it, I will also bring it to pass; I have purposed it, I will also do it" (Isa. 14:24-27; 46:9-11). Therefore, however haphazard or mysterious God's dealings with men may appear, those who believe this testimony of His Word must acknowledge that His original and unalterable plan has been, and still is, progressing systematically to completion.
When we think of a plan, we think of something involving more than just a single element. An architect's plan for a building consists of drawings and specifications descriptive of its several floors, including styles of plumbing, decoration, arrangement of rooms, etc. Unless each floor of the building is to be identical to every other floor, necessarily the drawings and specifications for any given floor do not harmonize with the details of the other floors. No one, however, would construe this to mean that the architect is incompetent, nor that his plans and specifications are contradictory. God's plan, like the plan of a building, is also made up of many parts. Instead of different floors, however, it embraces EPOCHS AND AGES. Through each of these ages the divine plan has steadily progressed toward completion. Only when it is complete, and mankind sees the result, will they all be able to appreciate the wisdom, justice, love and power of the Divine Architect. -Ps. 72:1-20

“እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ!!!” (ክፍል 1)

በቀደመው ኪዳን ይቀርቡ የነበሩ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቁርባን፣ የኃጢአትና የበደል መሥወዕት እንዲሁም የቅድስናና የደህንነት መሥወዕቶች ሁሉ፣ ምሳሌነታቸው ይመጣ ስላለው የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር። የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት አካባቢ  ወደ ምድር የመጣበትን የአባቱን ዓላማና ፈቃድ ለመፈጸም ልክ በሠላሳ ዐመቱ በሰዎች መካከል በይፋ በተገለጠበት ጊዜ፣ በመንገድ ጠራጊው በዮሃንስ በኩል የመጣው የእግዚአብሔር ምስክር “እነሆ የዓለምን ሁሉ ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ!” የሚል ነበር። ለሦስት ዓመት ተኩል ያህልም በእርሱ በነበረው የእግዚአብሔር መንፈስ “መልካም እያደረገና ለዲያብሎስ የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ” የእግዚአብሔርን መንግሥት ከሰበከ በህዋላ፤ በተካፈለው ሥጋና ደም በኩል ከሰይጣንና ከዚህ ክፉ ዓለም የመጣበትን ፈተና ሁሉ አሸንፎ በፍጹም ቅድስና የጠበቀውን ነውርና ዕድፍ የሌለውን ራሱን ለዓለም ሁሉ የሚሆን የኃጢአትና የበደል መሥዋዕት አድርጎ በመስቀል ላይ አቀረበ። አባቱም ይህንን ቅዱስና ሕያው መሥዋዕት ተቀበለ። የዓለምን ሁሉ ኃጢአትና በደልም በእርሱ ላይ አኖረ። ስለዚህም በአዳም በደል ምክንያት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ገብቶ የነበረው ጠላትነት በክርስቶስ ሞት ተወግዶ መታረቅ ሆነ። “… እግዚአብሔርም በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፣ በደላቸውንም አይቆጥርባቸውም ነበር፤….” (2ቆሮ. 5፡19)

አለማወቃቸው ነው እንጂ፤ እግዚአብሔር ዘር፣ቀለም፣ ጾታ፣ ሐይማኖት…. ሳይለይ፣ በየትኛውም ዓለም - በማንኛውም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ የሰው ልጆችይቅርታንና ምሕረትን አድርጎአል። ነገር ግን ኃጢአትን በተመለከተ በክርስቶስ ኢየሱስ የተገለጠው የእግዚአብሔር ዓላማ ይቅርታ ማድረግ ብቻ አይደለም። ማዳንም ነው!!! ሰዎች የኃጢአት ይቅርታ ማግኘት ብቻ ሳይሆን፣ ከኃጢአት ኃይልና ሕግ ነጻ መውጣት ይኖርባቸዋል። ከኃጢአት መዳን የሚባለውም ይሀ ነው። ከኃጢአት መዳን ማለት ደግሞ ከሞት መዳንም ማለት ነው። ለዚህም ነው በሞቱ ዓለሙን ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ያስታረቀው ብቻ ሳይሆን በሕይወቱ የሚያምኑትን ሁሉ የሚያድነው መሲሕ ገና ከመጸነሱ እንዲህ የሚል የምሥራች በመላእክት አንደበት ለዮሴፍ የተነገረው፡- “እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።” (ማቴ.1፡21)

የኃጢአት ይቅርታ በማግኘትና ከኃጢአት በመዳን መካከል ያለውን ልዩነት ለመረዳት፣ በተለይ ሐዋርያው ጳውሎስ ለሮሜ ክርስቲያኖች የጻፋቸውን የመጀመሪዎቹን ስምንት ምዕራፎች በጸሎትና (እግዚአብሔር በመንፈሱ እንዲያስተምረን) በጽሞና ሆነን ማጥናት ያስፈልጋል። ይህን መልዕክት በጥንቃቄ ስናጠና፣ በመልዕክቱ ውስጥ “ኃጢአት” የሚለው ቃል በሁለት መልኩ ተገልጦ እናገኘዋለን። የመጀመሪያው በእግዚአብሔር ፊት የተደረገ በደል ወይም በድርጊት የተፈጸመ ኃጢአትን (Committed Sin) የሚመለከት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ሰዎች ይህን በደልና ኃጢአት ይፈጽሙ ዘንድ በውስጣቸው ሆኖ የሚያነሳሳቸውን የኃጢአት ሕግ (The principle or the law of sin) የሚመለከት ነው። ማንኛውም ከሥጋና ከደም የተወለደ ሰው ሁሉ ወደዚህ ዓለም የሚገባው ከዚህ የኃጢአት ሕግ ጋር ነው። ለዚህም ነው ንጉሡ ዳዊት “እነሆ በዓመፃ ተጸነስሁ፣ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ” በማለት ይህን እውነት አስቀድሞ የገለጸው። ወንድሞቼ፣ ሰው ከፊተኛው አዳም የተካፈለውን ይህን የኃጢአት ሕግ ከሆነ “የውርስ ኃጢአት” የሚል ስም የሰጡት፤ ሰው ሁሉ ክርስቶስ ኢየሱስ በቀራንዮ መስቀል ላይ በከፈለው ዋጋ ወይም ደግሞ እነርሱ እንደሚያምኑት በሕጻንነቱ ሲጠመቅ ከዚህ “የውርስ ኃጢአት” አልዳነም - አይድንምም። ይህን እውነት በቅጡ ለመረዳት ከላይ በሁለት መልኩ የከፈልነውን ሀሳብ አንድ በአንድ እንመልከት፡-

1. በእግዚአብሔር ፊት የተደረገ በደል ወይም በድርጊት የተፈጸመ ኃጢአት (Committed sin)

“ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና፣ የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤“ (ሮሜ.3፡23)

ሰው በአዳም አለመታዘዝ ምክንያት ከእግዚአብሔር ከተለየበት ማለዳ ጀምሮ ነው ዓመጽን መለማመድ የጀመረው። ይህም በአዳም የበኩር ልጅ በቃየን የተገለጠ ነው። እኔ ገና ከሕጻንነቴ ጀምሮ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ የሰራሁትን በደልና ኃጢአት ልቆጥረው አልችልም። ይሄ ጉዳይ ደግሞ የእኔ ብቻ ሳይሆን፣ ከስጋና ከደም በመወለድ ወደዚህ ዓለም የመጡ የሰው ልጆች ሁሉ ታሪክ ነው። በእግዚአብሔር ፊት የፈጸምነውና እየፈጸምን ያለነው በደል፣ የተለማመድነውም ኃጢአት አይነቱ የአንዳችን ከአንዳችን ቢለያይም ያው ሁሉም ዓመጽ፣ ሁላችንም አመጸኞች ነን። በውጭ ሲታዩ የመላእክት ልጆች የሚመስሉት የሐይማኖት አባቶችም ሆኑ፣ ሰዎች ሁሉ እያዩት በመንገድ ላይ የሚወላገደው ሰካራም ያው ኃጢአተኞች ናቸው። ሐይማኖት የፈጠረውን ግብረ-ገብ ከልጅነቱ ጀምሮ እየፈጸመ ያደገው “የሞራል ስው” እና ወላጆቹ ሲያደርጉ ያየውን ዛፍና ወንዝ እያመለከ ያደገውም ብላቴና በእግዚአብሔር ፊት በደለኞች ናቸው። ያኔ በክርስቶስ ፊት ሊወግሩዋት ድንጋይ ተሸክመው የመጡት ሐይማኖተኞችም ሆኑ፣ በምንዝር የተያዘችው ያቺ ሴት…. ሁሉም ኃጢአትን በመሥራታቸው የእግዚአብሔር ክብር የጎደላቸው የአዳም ዘሮች ናቸው። ስለዚህ “እግዚአብሔር ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን ከኃጢአት በታች ዘግቶታል” (ሮሜ.11፡32)

ታድያ፤ እግዚአብሔር ሁሉን የማረው፣ በዘመናት መካከል ሰዎች የፈጸሙትን በደል ሁሉ እንዳልፈጸሙት አድርጎ የቆጠረው፣ የተወው፣ የረሳው …. በቀራንዮ መስቀል ላይ በቀረበው የኃጢአትና የበደል መሥዋዕት፣ ጌታ የኢየሱስ ክርስቶሰ በከፈለው ውድ ዋጋ…. ነው። ከእንግዲህ ሰዎች ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቃቸውን ይወቁ!! በእነርሱና በእግዚአብሔር መካከል የነበረው የጥል ግድግዳ በመስቀሉ ደም እንደፈረሰ ይመኑ!!! ከምሕረቱና ከጸጋው ባለጠግነት ይጠግቡ ዘንድ በክርስቶስ በሆነው ቤዛነት በኩል እየቀረቡ “የእግዚአብሔርን ጽድቅ” ይቀበሉ!!! በፊት ያደረጉትን ኃጢአት ሁሉ ይቅር ብሎ፣ በደላቸውን ላይቆጥር እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም አዲስ ኪዳን አድረጎአልና!!!!!!

“ሁሉ ኃጢአትን ሰርተዋልና፣ የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ። እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስረያ አድርጎ አቆመው፤ ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ስለመተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፤” (ሮሜ.3፡23-25)