የጽድቅና የሕይወት ጠላት የሆነው ዲያብሎስ በአገልጋዩ በሐይማኖት በኩል በዘመናት መካከል ይፈጽመው ዘንድ የሚተጋበት ዋና ዓላማው፣ እግዚአብሔር ከሙታን ያስነሳውን፣ በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም ዓለም ከሚጠሩት ስሞች ሁሉ በላይ የሆነውን ስም ሰጥቶትና ጌታም ክርስቶስም አድርጎት በቀኙ ያስቀመጠውን ኢየሱስን፣ ከቻለ ስሙን ከምድር ገጽ ላይ ለመደምሰስ፣ ካልቻለ ደግሞ ሰዎች ስለ እርሱ ባላቸው መረዳት ላይ ውዥንብርና ግራ መጋባትን መፍጠር ነው። ይኸው “የክርስቶስ ተቃዋሚ” ሰዎች ሁሉ ይድኑበት ዘንድ ከሰማይ በታች የተሰጣቸውን ይህን አንድ ስም በእምነት እንዳይጠሩ፣ ጠርተውም እንዳይድኑ ከልባቸውና ከአንደበታቸው ላይ ለመንጠቅ ግርግር መፍጠር የጀመረው፣ የክርስቶስ ሐዋርያት በጌታቸው የተሰጣቸውን ተልዕኮ በመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ቅባት ለማገልገል ‘ሀ’ ብለው በጀመሩበት ማለዳ ነበር።
የበዓለ ሃምሳ ዕለት በመንፈስ ቅዱስ “ጉሽ” የሰከሩት ሓዋርያት “እንግዲህ ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእሥራኤል ወገን ሁሉ ይወቅ” በማለት በእጃቸው የነበረውን የዘላለም ወንጌል መስበክ ሲጀምሩ፣ ሶስት ሺህ የሚያህሉ “ነፍሳት” ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ተጨመሩ። በዚሁ እግሮቻቸው - “በሰላም ወንጌል”፣ ወደ ቤተ መቅደስ ተጉዘው ከእናቱ ማሕጸን ጀምሮ መራመድ ተስኖት የነበረውን አንካሳ “በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሳና ተመላለስ” በማለት አዘለሉት። እርሱም ስለሆነለት ድንቅ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደቤተመቅደስ ገባ። በዚህም ተአምር መደነቅና መገረም የያዛቸው አምስት ሺህ ነፍሳት ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሲጨመሩ የካህናት አለቆችና የመቅደስ አዛዥ ሰዱቃውያን ግን ድንጋጤ ወደቀባቸው። በኢየሩሳሌምም ስብሰባ አድርገውና እነዮሐንስን በመካከል አቁመው፡- “በምን ኃይል ወይስ በማን ስም እናንተ ይህን አደረጋችሁ?” ብለው ጠየቋቸው።
“በዚያን ጊዜ ጴጥሮስም መንፈስ ቅዱስን ተሞልቶ እንዲህ አላቸው፡- እናንት የሕዝብ አለቆችና ሽማግሌዎች፣ እኛ ዛሬ ለድውዩ ሰው ስለተደረገው መልካም ሥራ ይህ በምን እንደዳነ ብንመረምር፣ እናንተ በሰቀላችሁት እግዚአብሔርም ከሙታን ባስነሳው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይህ ሰው ደህና ሆኖ በፊታችሁ እንደቆመ ለእናንተ ለሁላችሁ ለእሥራኤልም ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን። እናንተ ግንበኞች የናቃችሁት የማዕዘን ራስ የሆነው ይህ ድንጋይ ነው። መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” (ሥራ 4፡8-13)
ከዚህን ዕለት ጀምሮ ነው ያ የወንጌል ጠላት የሆነው “የጨለማው ገዢ” ይህንን ሰዎች ሁሉ ይድኑበት ዘንድ ከሰማይ በታች የተሰጣቸውን አንድና ብቸኛ ስም ለማጥፋት የመጀመሪያ ሙከራውን ያደረገው። አሁንም እነዚያን አገልጋዮቹን በሸንጎአቸው ለምክር እንዲቀመጡ ጠራቸው። እነርሱም ፡- “በነዚህ ሰዎች ምን እንሥራ? የታወቀ ምልክት በእነርሱ እጅ እንደተደረገ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሁሉ ተገልጦአልና እንሸሽገውም ዘንድ አንችልም፤ ነገር ግን በሕዝቡ ዘንድ አብዝቶ እንዳይስፋፋ ከእንግዲህ ወዲህ ለማንም ሰው በዚህ ስም እንዳይናገሩ እየዛትን እንዘዛቸው ብለው እርስ በእርሳቸው ተማከሩ። ጠርተውም በኢየሱስ ስም ፈጽመው እንዳይናገሩና እንዳያስተምሩ አዘዟቸው” (ሥራ.4፡16-18) ሐዋርያቱ ግን በዲያበሎስ ዛቻና ማስፈራሪያ ሳይደናገጡ ይህን ሰዎች ሁሉ ይድኑበት ዘንድ ከሰማይ በታች የተሰጠውን አንድና ብቸኛ ስም “እኛ ግን የተሰቀለውን፣ የሞተውን፣ እግዚአብሔርም ከሙታን ያስነሳውንና ጌታም ክርስቶስም አድርጎ በቀኙ ያስቀመጠውን ኢየሱስን እንሰብካለን!!” እያሉ ለምድር ወገኖች ሁሉ በሐይማኖት መርዝ ያልተመረዘውንንና በሰው ትምሕርት ያልተበከለውን ንጹሁን የመዳን ወንጌል እየሰበኩ ሰዎችን ወደእግዚአብሔር መንግሥት መጨመራቸውን ቀጠሉ።
ከላይ እንዳልነው፣ የጽድቅና የሕይወት ጠላት የሆነው ዲያብሎስ በአገልጋዩ በሐይማኖት በኩል በዘመናት መካከል ይፈጽመው ዘንድ የሚተጋበት ዋና ዓላማው፣ እግዚአብሔር ከሙታን ያስነሳውን፣ በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም ዓለም ከሚጠሩት ስሞች ሁሉ በላይ የሆነውን ስም ሰጥቶና ጌታም ክርስቶስም አድርጎ በቀኙ ያስቀመጠውን ኢየሱስን፣ ከቻለ ስሙን ከምድር ገጽ ላይ ለመደምሰስ፣ ካልቻለ ደግሞ ሰዎች ስለ እርሱ ባላቸው መረዳት ላይ ውዥንብርና ግራ መጋባትን በመፍጠር ከጽድቅና ከሕይወት መንገድ ማሳሳት ነው። ውዥንብር በመፍጠር ግራ የማጋባት አጀንዳውን እጅግ በጠለቀና በረቀቀ መልኩ የፈጸመው፣ በተለይም ከ325ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት በጠራቸው ሸንጎዎች ላይ ባረቀቃቸውና ባጸደቃቸው “የሐይማኖት መግለጫዎች” ነው። በዚያን ጊዜም፣ በክርስቶስ ሓዋርያት የተሰበከውን ግልጽና የማያሻማ የጽድቅና የሕይወት መንገድ ከመጣመሙም በላይ፣ ሰዎች በክርስቶስ ባላቸው እምነት ከእግዚአብሔር ዳግመኛ ሲወለዱ በሚቀበሉት መንፈሳዊ አእምሮ ብቻ ሊመረምሩና ሊረዱ የሚችሉትን “የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር”፣ በፍጥረታዊው አእምሮአቸው እንዲመረምሩና አቋማቸውንም “በአብላጫ ድምጽ” እንዲወስኑ በማድረግ፣ እስከዛሬ ድረስ በክርስትና ውስጥ እየበዛ ለመጣው ግራ መጋባትና መከፋፈል ምክንያት የሆነውን ጠንካራ መሠረት ጥሏል።
ሐዋርያት፣ አሕዛብን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱሰ ስም እያጠመቁና እርሱ ያዘዛቸውን እያስተማሩ ደቀ መዛሙርት እንዲያደርጉ በክርስቶስ የተሰጣቸው መመሪያ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ነገር ግን እነርሱ በአብ፣ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ወንጌልን አልሰበኩም፣ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ድውዮችን አልፈወሱም፣ አጋንንትን አላወጡም፣ ሙታንን አላስነሱም፣ እጃቸውን ወደግራና ወደቀኝ እያወናጨፉ “አላማተቡም”…. የሰበኩት አንድ ወንጌል፣ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶሰ ስለስዎች ሁሉ ኃጢአት እንደሞተ፣ እንደተቀበረና በሦስተኛውም ቀን እግዚአብሔር ከሙታን አስነስቶ በቀኙ እንዳስቀመጠው የሚናገረውንና፣ ይህን በማመን ስለሚገኘው የእግዚአብሔር ልጅነት ጸጋ እና ለሰዎች ሁሉ እንዲያው ስለተሰጠው የዘላለም ሕይወት ተስፋ የሚያበስረውን ወንጌል ነው !! የሰዎችን እምነትና ሕይወት “እንደብልሃተኛ የአናጺ አለቃ” የመሰረቱትም ሆነ ያነጹት፤ በተፈተነው፣ በከበረውና መሠረቱ በጸናው የጽዮኑ አለት በክርስቶስ ላይ ነበር።
ሐዋርያቱ የሰበኩት ክርስትና የተመሠረተው፣ “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ!” በሚለው በሰማያት ካለው አባት በመጣው ሰማያዊ መገለጥ ላይ ነበር። ለዚህም ነው፡- “ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል፣ ….. ኢየሱስም የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ከሚያምን በቀር ዓለምን የሚያሸንፍ ማነው? ….. በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በነፍሱ ምስክር አለው፤ በእግዚአብሔር የማያምን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የሰጠውን ምስክር ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል። እግዚአብሔር የዘላለምን ሕይወት እንደሰጠን፣ ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው። ልጁ ያለው ሕይወት አለው፣ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም” (1ኛዮሐ. 5፡1-12) እያሉ ግልጽ በሆነና ውዥንብር በማይፈጥር ትምሕርት የሕይወትን መንገድ የሰበኩት። የእግዚአብሔር መንፈስ እጃቸውን ይዞና አእምሮአቸውን ተቆጣጥሮ የጻፉትም መልእክት ለምን እንደተጻፈ ሲናገሩም እንዲህ አሉ፡-
“ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤ ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ታምኑ ዘንድ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል።” (ዮሐ.20፡30-31)

No comments:
Post a Comment