Monday, December 24, 2012

በክርስቶስ ኢየሱስ ባለ እምነት - የእግዚአብሔር ልጆች ነን!!!!!



የወንጌል ጠላት የሆነው የዚህ ዓለም ገዢ ዲያብሎስ፤ መሠረቱ ወይም መነሻው ግልጽና ቀላል የነበረውን የክርስቶስ ወንጌል፣ወደተወሳሰበ ሃይማኖታዊ ንትርክ ውስጥ በመክተት ብቸኛውን የሕይወት መንገድ ለማወላገድ ሙከራ ያደረገው ገና በሐዋርያቱ ዘመን ቢሆንም፤ ይህ ሙከራው የተሳካለት ግን ልክ ዛሬ በአገራችን እንደምናየው ሐይማኖትን ለፖለቲካ ጥቅማቸውና ለዙፋናቸው መደላደል እንደመሣሪያ ለመጠቀም ይፈልጉ በነበሩት የሮማ ነገሥታት አማካኝነት ከሦስተኛውና ከአራተኛው ክ/ዘመን ጀምሮ ባቀናበራቸው ጉባዔዎች ነው። በነዚህ ጉባዔዎች አማካኝነት እጅግ ግልጽ የነበረውና በሐዋርያቱ የተሰበከው የጽድቅና የሕይወት መንገድ ተጣመመ። አንድየነበረው እምነት ክርስትናም ወደተለያዩአፈንጋጭሃይማኖታዊ ቡድኖች ተከፋፈለ

ክርስትናየምንለው ምሥጢረ ሥላሴን የሚሰብክ ሃይማኖት (Religion) ሳይሆን፣ኢየሱስ እርሱም ክርስቶስና ጌታ የሆነውን የሕያው እግዚአብሔርን ልጅየሚሰብክ  እምነት(Faith) ነው። ሃይማኖት እጅግ ብዙ ነው።ክርስትናየምንለው እምነት ግን አንድ ነው። መሠረቱምምሥጢረ ሥላሴሳይሆንየሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።ይህአንድየተባለው እምነታችን የሚጀምረው ከስብከት ሞኝነት እንጂ ሃይማኖት ካወሳሰበው የምሥጢር ሥላሴ ትምሕርት አይደለም። ይህም የሆነው እግዚአብሔርበስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድንስለወደደ ነው። ለዚህም ነው የክርስቶስ ሐዋርያት ሰዎች ከጨለማ እሥራት የሚፈቱበትንና የሚድኑበትን ወንጌል፣ ይኸውም የተሰቀለውንና የሞተውን፣ ደግሞም ከሙታን የተነሳውን እርሱም ክርስቶስና ጌታ የተባለውን የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስን በቅንነትና በግልጽነት እየሰበኩ በስፍራ ሁሉ ይዞሩ የነበረው። እነርሱ ከዚህ ውጪ ሌላ ወንጌል አልሰበኩም።

ወንጌላዊው
ዮሃንስ እግዚአብሔር የሰጠንን ግልጽ ትዕዛዝ ሲናገር፡- “ትእዛዚቱም ይህች ናት፥ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናምን ዘንድ፥ ትእዛዝንም እንደ ሰጠን እርስ በርሳችን እንዋደድ ዘንድእንደሆነ ነግሮናል። መነሻው ግልጽና ቀላል የሆነውን የክርስቶስን ወንጌል ለእኛ ያስተላለፉልን የክርስቶስ ሐዋርያት እግዚአብሔር በሰጣቸው ዘመን ሁሉ ይህን የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ከመስበክና ከመናገር ውጪ፣እግዚአብሔር ስንት ነው? አንድ ነው - አንድም ሦስትም ነው - ሦስትም አንድም ነው…. ልጁ እግዚአብሔር ነው - አይደለም - ነውክርስቶስ ሁለት ባህሪይ አለው - የለም አንድ ነው፤ ሰው ነው - አምላክ ነው - ሰውና አምላክ ነው - ሰውና አምላክ በአንድነት ነው…. ” በማለት ራሳቸውንም ሆነ የሚሰሟቸውን ማለቂያ ወደሌለው ንትርክ ውስጥ አልከተቱም። ምክንያቱም “የእግዚአብሔር ምሥጢር” የተባለው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅነቱን አምነው በመታዘዝ ሲከተሉት ብቻ የሚያውቁት እንጂ በስብሰባና በውይይት በሚቀረጹ “አስተምህሮዎች” የሚረዱት ባለመሆኑ ነው።

ዛሬ በክርስትና ስም የሚጠሩ አብዛኛዎቹ የሐይማኖት ተቋማትና በነዚህም ተቋማት ውስጥ የተሰባሰቡት ወገኖች፤ “እከሌ ክርስቲያን ነው” ለማለት መመዘኛቸው ከስድስተኛው ክ/ዘመን ጀምሮ ሌላ መሠረት ሆኖ በክርስትና ውስጥ መሰበክ የጀመረውን “የአትናቴዎስ መግለጫ” የሚያምኑትንና የሚቀበሉትን ብቻ ነው። እንዲያውም በእነሱ አስተሳስብ አንድ ሰው የዘላለም ሕይወት ሊያገኝ የሚችለው ይህንኑ “አብ እግዚአብሔር ነው፣ ወልድ እግዚአብሔር ነው፣ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው፤ ቢሆንም አንድ እግዚአብሔር እንጂ ሦስት እግዚአብሔሮች አይደሉም.....” የሚለውን የአትናቴዎስ አስተምህሮ የተቀበለ እንደሁ ብቻ ነው።

ጳውሎስና ሲላስ የተሰቀለውንና ከሙታን የተነሳውን ክርስቶስን በመስበካቸው በወህኒ እንደተጣሉና ነገር ግን በታሰሩበት ወህኒ ውስጥ ሆነው እግዚአብሔርን በዜማ ሲያመሰግኑ የወህኒው መሠረት ተናውጦና ደጆቹም ተከፍተው እስራታቸው መፈታቱን፣ በዚህም የደነገጠው የወህኒ ጠባቂ ያመለጡ መስሎት ራሱን ሊያጠፋ ሲሞክር ጳውሎስ እንዳስጣለው፣ የወህኒው ጠባቂም በጳውሎስና በሲላስ እግር ስር ተደፍቶጌቶች ሆይ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል??” ብሎ መጠየቁን በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 16 ላይ እናነባለን። ይህንን መልእክት ለሚያነቡ ክርስቲያኖች ሁሉ አንድ ጥያቄ ልጠይቅ፡- ይህን ጥያቄ የተጠየቃችሁት አናንተ ብትሆኑ ምን ትመልሳላችሁ??? “የአትናቴዎስ መግለጫየሚለው፡- “አንድ ሰው እንዲድን ከፈለገ፣ አንድ ሲሆኑ ሦስት- ሦስት ሲሆኑ ደግሞ አንድ በሆኑት በእግዚአብሔር አብ፣ በእግዚአብሔር ወልድ፣ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ማመን አለበት …. እንዲህ ብሎ ያላመነ ለዘላም ይጠፋል….” ነው። ይህን መግለጫ ታነቡለታላችሁ??? ጳወሎስ ግን “እድን ዘንድ ምንማድረግ ይገባኛል??” ብሎ ለጠየቀው ለዚያ የወህኒ ጠባቂ የመለሰለት መልስ ይህ ነበር፡-“በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን፣ አንተና ቤተሰቦችህም ትድናላችሁ!!”

ክርስትናችን የሚጀምረው ከእግዚአብሔር ዳግመኛ በመወለድና የእግዚአብሔር ልጅነትን ጸጋ በመቀበል ነው። ይህን የልጅነት ጸጋ የሚሰጠን ደግሞ ክርስቶስና ጌታ ነው ብለን የእግዚአብሔር ልጅ በሆነው በኢየሱስ ማመናችን ነው። ታሪኩን በሐዋርያት ሥራ 8 ላይ የምናነበው ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ከኢሳያስ መጽሐፍ ምዕ.53 ጀምሮ ስለኢየሱስ ወንጌልን የሰበከለትፊሊጶስንእነሆ ውሃ እንዳልጠመቅ ምን ይከለክለኛል፤ብሎ በጠየቀው ጊዜ፡- “በፍጹም ልብህ ብታምን ተፈቅዶልሃል፤እንዳለው እናነባለን። ፊሊጶስ ለኢትዮጵያዊው ጃንደረባ የሰበከለት ወንጌል ዛሬ ሃይማኖት ከነአትናቴዎስ ተቀብሎ እንደሚያስተጋባው ዓይነት አለመሆኑን የምንረዳው፣ ከጃንደረባውየእምነት መግለጫነው።ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አምናለሁ!!!!!!!!!!!!!!!!"

በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በነፍሱ ምስክርነት አለው። በእግዚአብሔር የማያምን እግዚአብሔር ስለልጁ የመሰከረውን ምስክር ስላላመነ ሃሰተኛ አድርጎታል። እግዚአብሔርም የዘላለም ሕይወት እንደሰጠን፣ ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው። ልጁ ያለው ሕይወት አለው፣ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።” (1ዮሃ.510-12)

ወንድሞች
ሆይ!! እናንተም ይህን የነፍስ ምስክርነት በየግላቸሁ ስሙት!! መጽሐፍ እንደሚናገረውየእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን መንፈስ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራልእኔምየአትናቴዎስን መግለጫሳይሆን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውንና የገለጠውን ይህን ቃል በመስማቴ፣ በማመኔም ነው የእግዚአብሔር ልጅ የሆንኩትና ክርስቲያን ተብዬ የተጠራሁት። በእግዚአብሔር ልጅ በማመን ያገኘሁትንና በነፍሴና በመንፈሴ ውስጥ ያለውን ይህን ሕያው ምስክርነት ማንም ሊወስድብኝ አይችልም።    

No comments:

Post a Comment