Sunday, December 30, 2012

"ሕግህ ለእግሬ መብራት፣ ለመንገዴም ብርሃን ነው"



"አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤ ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል። የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።" 2. ጢሞ.314-17

መንፈሳዊውን
ጥበብና ዕውቀት በተመለከተ "ከመጽሐፍ ቅዱስ ይልቅ ራሱ መንፈሱ የእምነት ምንጭ ነው" የሚለው የአንዳንድ ወንድሞች አባባል "የበሰለ" ቢመስልም ነገር ግን ሚዛኑን የጠበቀ ባለመሆኑ ወደ ስህተት ያዘነበለ ነው። እንዲህ ዓይነቱ መረዳት ከተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚጣረሱ ብዙ የተለያዩ እንግዳ ትምሕርቶች ወደ ቤተክርስቲያን ሾልከው እንዲገቡና ብዙዎች ከጽድቅና ከሕይወት መንገድ ርቀው እንዲጠፉ ምክንያት ይሆናል። ለዚህም ማስረጃው በአገራችን ኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ በሰዎች እጅ ባልነበረባቸው ረጅም ዘመናት ውስጥ የተሰበኩት ልዩ ልዩ የሰው ድርሰቶች የፈጠሩት እንግዳ ሐይማኖት ነው።እምነት ከመስማት ነው፤ መስማትም በእግዚአብሔር ቃል!!” ስለዚህ በመጀመሪያ ደረጃ የእምነታችን ምንጭ ሊሆን የሚገባው የተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ወይም በእጃችን ያለው መጽሐፍ ቅዱስ ነው። እንዲህ ማለቴየእግዚአብሔር ቃልበእጃችን ባለው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሰው ፊደላት የተጻፈው ብቻ ነው ለማለት አይደለም። መነሻችንና መሠረታችን ግን የተጻፈውና እግዚአብሔር በዘመናት መካከል የተለየ ጥበቃ እያደረገለት ዛሬ በእጃችን ላይ እንዲገኝ ያደረገው መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

"ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤ ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል።" ዮሃ.2030-31

መጽሐፍ ቅዱሳችን በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የተጻፈ ብቻ ሳይሆን ከላይ 2ጢሞ.314-17 በጠቀስኩት የጳወሎስ መልእክት ላይ እንደምናነበው "የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት" መሆኑን ማንኛችንም አንስትም። ይህ መጽሐፍ እንደየደረስንበት መንፈሳዊ የዕድገት ደረጃ በተለያየ ልክና መጠን የምንረዳውን የእግዚአብሔር ሃሳብ የያዘ ሆኖ ተጀምሮ እስኪጨረስ ድረስ የሚነግረን ዋና መልእክትም በቀደመው አዳም ያጣነውን ክብር የሞላበት ሕይወት በክርስቶስ መልሰን ስለማግኘታችን ነው። በዚህም ምክንያት ወደተፈጠርንበት ዋና የእግዚአብሔር ዓላማ እርሱም እግዚአብሔርን ወደመምስል መድረስ የምንችልበትን ብቸኛ መንገድ ይጠቁመናል። እርሱም ክርስቶስ ነው። (2ጢሞ.312)

በመጽሐፍ
ቅዱሳችን ውስጥ የተገለጠው የእግዚአብሔር ሃሳብ በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ቀድተን የማንጨርሰው ባህር ነው። በዚህ ጥልቅ ባህር ውስጥ ራሳችንን ችለን መዋኘት እስክንጀምር ድረስ፣ ወይም በግልጽ አነጋገር በመንፈስ የተጻፈውን መፅሐፍ በመንፈስ በሆነ መገለጥ በየግላችን መረዳት እስክንችል ድረስ የሚያግዙንን አስተማሪዎች የአካሉ ራስ የሆነው ክርስቶስ በአካሉ ውስጥ አኑሮአል። እነዚህ አስተማሪዎች በተሰጣቸው ጸጋና ቅባት አማካኝነት በመንፈስ የተጻፈውን መጽሐፍ በመንፈስ እየተረጎሙ ያስተምሩናል። እኛም በእነርሱ አማካኝነት ደግሞም በጽሞናና በጸሎት ሆነን በየግላችን ቃሉን በምናነብበት ጊዜ በምናገኘው መረዳት መጠንና ልክ በመታዘዝና በታማኝነት መኖርና መመላለስ ስንጀምር በመንፈሳዊ ሕይወታችን እያደግንና እየጎለመሰን እንሄዳለን። ያኔም በፊደላት በወረቀት ላይ ተጽፎ የነበረውን ቃል የሕልውናችን ሕግ ይሆን ዘንድ በቅዱሱ መንፈስ አማካኝነት በልባችን ጽላት ላይ ተጽፎ እናገኘዋለን። ይሄም በእግዚአብሔር መንፈስ መመራት ወደምንችልበት ከፍታ ያወጣናል።

"ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።.... ስምዖን ጴጥሮስ። ጌታ ሆይ፥ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፤ እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ አምነናል አውቀናልም ብሎ መለሰለት። " ዮሃ.663-69

"እኔ የነገርኳችሁ ቃል መንፈስ ነው"

"በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።" ሮሜ.814

በእግዚአብሔር
ቃል ወይም ከላይ እንዳልኩት በክርስቶስ ትምሕርት መኖርና በመንፈስ መመላስ ሁለት የተለያዩ ነገሮች አይደሉም። በእግዚአብሔር መንፈስ መመራት ማለት በልባችን ውስጥ እየተጻፈ ካለው የእግዚአብሔር ቃል ውጪ በአንድ የሆነ ኃይል መነዳት ማለት አይደለም። እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ በሰጠን ጸጋና ጉልበት ክርስቶስ በነገረን ቃል መሠረት መመላለስ ስንጀምር በመንፈስ መመላለስ ጀምረናል ማለት ነው። እሱ የነገረን ቃል የሚመራን መንፈስም ጭምር ነው ይሄ የከበረ እውነት በእግዚአብሔር መንፈስ ለተቀባው ዳዊትም ተገልጦለት ነበር። "ሕግህ ለእግሬ መብራት፣ ለመንገዴም ብርሃን ነው" መዝ.119105
በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ያላደጉ ክርስቲያኖች "በእግዚአብሔር መንፈስ መመራት" ወይም በሰሙት ቃል መጠንና ልክ ለመኖር ወደሚችሉበት መንፈሳዊ ዓቅምና ችሎታ እስኪደርሱ ድረስ በእምነት የሚያበረታቷቸው፣ የሚመክሩዋቸውና የሚያጽናኗቸው፣ ደግሞም እንደየደረሱበት የዕድገት ደረጃ የሚመጥናቸውን መንፈሳዊ ምግብ የሚመግቡዋቸው፣ የሚጠብቋቸውና ከፊት ሆነው የሚመሯቸው እረኞችና አስተማሪዎች ያስፈልጓቸዋል። ከላይ በአጭሩ ለመግለጥ እንደሞከርኩትም በኤፌሶን መልእክት ምዕራፍ 4 ላይ የምናገኛቸው አገልግሎቶችም ዓላማቸው ይህ ነው።

"እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤ ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።" ኤፌ.411-13

እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ የመሠረተው አዲስ ኪዳን፤ ከአሮጌው ኪዳን የሚለይበት ዋነኛ ምክንያት አዲሱ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕግ በእግዚአብሔር መንፈስ አማካኝነት በልባችንና በአእምሮአችን ላይ የሚጻፍበት የሕይወት ዘመን ሂደት በመሆኑ ነው። ይሄ ሂደት ወደ ሙላትና ፍጽምና የሚደርሰው ግን በመጽሐፍ ተጽፎ የተሰጠን የክርስቶስ ትምሕርት በቃልም ቢሆን በስብከት አማካኝነት በልባችን ውስጥ ተዘርቶ ሲያድግ፣ አድጎም ፍሬ ሲያፈራ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ አሥራ ሶስት ላይ ስለዘሪው ምሳሌ ያስተማረውም ትምሕርት ለዚህ እውነት ዓይነተኛ ምሳሌ ነው።

"በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል።" ዮሃ.157-8

ዛሬ የክርስቶስን ቃል ከየት ነው የምናመጣው?? ከተጻፈልንና በእጃችን ካለው መጽሐፍ ውስጥ አይደለምን?? እያንዳንዳችን የደረስንበትንና ዛሬ ያለንበትን ሕይወት መጠንና ልኩን ለማወቅ፤ በቀላሉ "የተራራው ስብከት" በመባል የሚታወቀውንና ከማቴዎስ ምዕራፍ አምስት እሰከ ሰባትድረስ ባሉ ሦስት ምዕራፎች ብቻ የተጻፈውን የክርስቶስ ትምሕርት ማጥናት በቂ ነው። ያኔ - በሦስት ምዕራፎች ላይ ብቻ በተጻፈው በዚህ የክርስቶስ ትምሕርት መጠንና ልክ ራሳችንን ለማግኘት የሕይወት ዘመን ተጋድሎን እንደሚጠይቅ እናስተውላለን።

"ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል። ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት ገፋው፥ በዓለት ላይም ስለ ተመሠረተ አልወደቀም። ይህንም ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሰው ሁሉ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራ ሰነፍ ሰውን ይመስላል። ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት መታው፥ ወደቀም፥ አወዳደቁም ታላቅ ሆነ። ኢየሱስም ይህን ነገር በጨረሰ ጊዜ ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ፤ እንደ ጻፎቻቸው ሳይሆን እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበርና።" ማቴ.724-29

ይህን
ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው፡-

ጌታ
ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ቃል የተናገረው ከላይ ያነሳሁትንና "የተራራው ስብከት" በመባል የሚታወቀውን የከበረ ትምሕርት አስተምሮ ሲጨርስ ነው። ይህን ትምሕርት በዚህ ዘመን ያለነውን እኛን ያስተምረን ዘንድ ክርስቶስ እንደገና በሥጋ መገኘት አያስፈልገውም። እንሰማው ዘንድ ቃሉ በእጃችን ባለው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፎ እናገኘዋለን። ልናደርገው ወይም በሕይወት አካሄዳችን ልንመላለስበት የምንችለው ግን በስብከትም ይሁን በግል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ወቅት በጆሮአችን የምንሰማው ይህ ቃል በእግዚአብሔር መንፈስ አማካኝነት በልባችን ጽላት ውስጥ የተጻፈ እንደሆን ብቻ ነው። ቃሉ በልባችን ውስጥ የመጻፉ ነገር እውን የሚሆነው ደግሞ በእግዚአብሔር መንፈስ አሰራር ብቻ ሳይሆን በእኛም የልብ መዘጋጀት ጭምር ነው። ለዚህ መንፈስና ሕይወት ለሆነው ሕያው ቃል ልባችንን እንደመልካም መሬት ማዘጋጀት እንድንችል እግዚአብሔር ይርዳን!!!!

"በመልካም መሬት ላይም የወደቀ እነርሱ በመልካምና በበጎ ልብ ቃሉን ሰምተው የሚጠብቁት በመጽናትም ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።" ሉቃ.815

Monday, December 24, 2012

በክርስቶስ ኢየሱስ ባለ እምነት - የእግዚአብሔር ልጆች ነን!!!!!



የወንጌል ጠላት የሆነው የዚህ ዓለም ገዢ ዲያብሎስ፤ መሠረቱ ወይም መነሻው ግልጽና ቀላል የነበረውን የክርስቶስ ወንጌል፣ወደተወሳሰበ ሃይማኖታዊ ንትርክ ውስጥ በመክተት ብቸኛውን የሕይወት መንገድ ለማወላገድ ሙከራ ያደረገው ገና በሐዋርያቱ ዘመን ቢሆንም፤ ይህ ሙከራው የተሳካለት ግን ልክ ዛሬ በአገራችን እንደምናየው ሐይማኖትን ለፖለቲካ ጥቅማቸውና ለዙፋናቸው መደላደል እንደመሣሪያ ለመጠቀም ይፈልጉ በነበሩት የሮማ ነገሥታት አማካኝነት ከሦስተኛውና ከአራተኛው ክ/ዘመን ጀምሮ ባቀናበራቸው ጉባዔዎች ነው። በነዚህ ጉባዔዎች አማካኝነት እጅግ ግልጽ የነበረውና በሐዋርያቱ የተሰበከው የጽድቅና የሕይወት መንገድ ተጣመመ። አንድየነበረው እምነት ክርስትናም ወደተለያዩአፈንጋጭሃይማኖታዊ ቡድኖች ተከፋፈለ

ክርስትናየምንለው ምሥጢረ ሥላሴን የሚሰብክ ሃይማኖት (Religion) ሳይሆን፣ኢየሱስ እርሱም ክርስቶስና ጌታ የሆነውን የሕያው እግዚአብሔርን ልጅየሚሰብክ  እምነት(Faith) ነው። ሃይማኖት እጅግ ብዙ ነው።ክርስትናየምንለው እምነት ግን አንድ ነው። መሠረቱምምሥጢረ ሥላሴሳይሆንየሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።ይህአንድየተባለው እምነታችን የሚጀምረው ከስብከት ሞኝነት እንጂ ሃይማኖት ካወሳሰበው የምሥጢር ሥላሴ ትምሕርት አይደለም። ይህም የሆነው እግዚአብሔርበስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድንስለወደደ ነው። ለዚህም ነው የክርስቶስ ሐዋርያት ሰዎች ከጨለማ እሥራት የሚፈቱበትንና የሚድኑበትን ወንጌል፣ ይኸውም የተሰቀለውንና የሞተውን፣ ደግሞም ከሙታን የተነሳውን እርሱም ክርስቶስና ጌታ የተባለውን የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስን በቅንነትና በግልጽነት እየሰበኩ በስፍራ ሁሉ ይዞሩ የነበረው። እነርሱ ከዚህ ውጪ ሌላ ወንጌል አልሰበኩም።

ወንጌላዊው
ዮሃንስ እግዚአብሔር የሰጠንን ግልጽ ትዕዛዝ ሲናገር፡- “ትእዛዚቱም ይህች ናት፥ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናምን ዘንድ፥ ትእዛዝንም እንደ ሰጠን እርስ በርሳችን እንዋደድ ዘንድእንደሆነ ነግሮናል። መነሻው ግልጽና ቀላል የሆነውን የክርስቶስን ወንጌል ለእኛ ያስተላለፉልን የክርስቶስ ሐዋርያት እግዚአብሔር በሰጣቸው ዘመን ሁሉ ይህን የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ከመስበክና ከመናገር ውጪ፣እግዚአብሔር ስንት ነው? አንድ ነው - አንድም ሦስትም ነው - ሦስትም አንድም ነው…. ልጁ እግዚአብሔር ነው - አይደለም - ነውክርስቶስ ሁለት ባህሪይ አለው - የለም አንድ ነው፤ ሰው ነው - አምላክ ነው - ሰውና አምላክ ነው - ሰውና አምላክ በአንድነት ነው…. ” በማለት ራሳቸውንም ሆነ የሚሰሟቸውን ማለቂያ ወደሌለው ንትርክ ውስጥ አልከተቱም። ምክንያቱም “የእግዚአብሔር ምሥጢር” የተባለው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅነቱን አምነው በመታዘዝ ሲከተሉት ብቻ የሚያውቁት እንጂ በስብሰባና በውይይት በሚቀረጹ “አስተምህሮዎች” የሚረዱት ባለመሆኑ ነው።

ዛሬ በክርስትና ስም የሚጠሩ አብዛኛዎቹ የሐይማኖት ተቋማትና በነዚህም ተቋማት ውስጥ የተሰባሰቡት ወገኖች፤ “እከሌ ክርስቲያን ነው” ለማለት መመዘኛቸው ከስድስተኛው ክ/ዘመን ጀምሮ ሌላ መሠረት ሆኖ በክርስትና ውስጥ መሰበክ የጀመረውን “የአትናቴዎስ መግለጫ” የሚያምኑትንና የሚቀበሉትን ብቻ ነው። እንዲያውም በእነሱ አስተሳስብ አንድ ሰው የዘላለም ሕይወት ሊያገኝ የሚችለው ይህንኑ “አብ እግዚአብሔር ነው፣ ወልድ እግዚአብሔር ነው፣ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው፤ ቢሆንም አንድ እግዚአብሔር እንጂ ሦስት እግዚአብሔሮች አይደሉም.....” የሚለውን የአትናቴዎስ አስተምህሮ የተቀበለ እንደሁ ብቻ ነው።

ጳውሎስና ሲላስ የተሰቀለውንና ከሙታን የተነሳውን ክርስቶስን በመስበካቸው በወህኒ እንደተጣሉና ነገር ግን በታሰሩበት ወህኒ ውስጥ ሆነው እግዚአብሔርን በዜማ ሲያመሰግኑ የወህኒው መሠረት ተናውጦና ደጆቹም ተከፍተው እስራታቸው መፈታቱን፣ በዚህም የደነገጠው የወህኒ ጠባቂ ያመለጡ መስሎት ራሱን ሊያጠፋ ሲሞክር ጳውሎስ እንዳስጣለው፣ የወህኒው ጠባቂም በጳውሎስና በሲላስ እግር ስር ተደፍቶጌቶች ሆይ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል??” ብሎ መጠየቁን በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 16 ላይ እናነባለን። ይህንን መልእክት ለሚያነቡ ክርስቲያኖች ሁሉ አንድ ጥያቄ ልጠይቅ፡- ይህን ጥያቄ የተጠየቃችሁት አናንተ ብትሆኑ ምን ትመልሳላችሁ??? “የአትናቴዎስ መግለጫየሚለው፡- “አንድ ሰው እንዲድን ከፈለገ፣ አንድ ሲሆኑ ሦስት- ሦስት ሲሆኑ ደግሞ አንድ በሆኑት በእግዚአብሔር አብ፣ በእግዚአብሔር ወልድ፣ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ማመን አለበት …. እንዲህ ብሎ ያላመነ ለዘላም ይጠፋል….” ነው። ይህን መግለጫ ታነቡለታላችሁ??? ጳወሎስ ግን “እድን ዘንድ ምንማድረግ ይገባኛል??” ብሎ ለጠየቀው ለዚያ የወህኒ ጠባቂ የመለሰለት መልስ ይህ ነበር፡-“በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን፣ አንተና ቤተሰቦችህም ትድናላችሁ!!”

ክርስትናችን የሚጀምረው ከእግዚአብሔር ዳግመኛ በመወለድና የእግዚአብሔር ልጅነትን ጸጋ በመቀበል ነው። ይህን የልጅነት ጸጋ የሚሰጠን ደግሞ ክርስቶስና ጌታ ነው ብለን የእግዚአብሔር ልጅ በሆነው በኢየሱስ ማመናችን ነው። ታሪኩን በሐዋርያት ሥራ 8 ላይ የምናነበው ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ከኢሳያስ መጽሐፍ ምዕ.53 ጀምሮ ስለኢየሱስ ወንጌልን የሰበከለትፊሊጶስንእነሆ ውሃ እንዳልጠመቅ ምን ይከለክለኛል፤ብሎ በጠየቀው ጊዜ፡- “በፍጹም ልብህ ብታምን ተፈቅዶልሃል፤እንዳለው እናነባለን። ፊሊጶስ ለኢትዮጵያዊው ጃንደረባ የሰበከለት ወንጌል ዛሬ ሃይማኖት ከነአትናቴዎስ ተቀብሎ እንደሚያስተጋባው ዓይነት አለመሆኑን የምንረዳው፣ ከጃንደረባውየእምነት መግለጫነው።ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አምናለሁ!!!!!!!!!!!!!!!!"

በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በነፍሱ ምስክርነት አለው። በእግዚአብሔር የማያምን እግዚአብሔር ስለልጁ የመሰከረውን ምስክር ስላላመነ ሃሰተኛ አድርጎታል። እግዚአብሔርም የዘላለም ሕይወት እንደሰጠን፣ ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው። ልጁ ያለው ሕይወት አለው፣ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።” (1ዮሃ.510-12)

ወንድሞች
ሆይ!! እናንተም ይህን የነፍስ ምስክርነት በየግላቸሁ ስሙት!! መጽሐፍ እንደሚናገረውየእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን መንፈስ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራልእኔምየአትናቴዎስን መግለጫሳይሆን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውንና የገለጠውን ይህን ቃል በመስማቴ፣ በማመኔም ነው የእግዚአብሔር ልጅ የሆንኩትና ክርስቲያን ተብዬ የተጠራሁት። በእግዚአብሔር ልጅ በማመን ያገኘሁትንና በነፍሴና በመንፈሴ ውስጥ ያለውን ይህን ሕያው ምስክርነት ማንም ሊወስድብኝ አይችልም።