“እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ እኔ አምላክ ነኝና ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለምና ወደ እኔ ዘወር በሉ፣
ትድኑማላችሁ፤ ቃሌ ከአፌ በጽድቅ ወጥታለች፣ አትመለስም፡- ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፣ ምላስም ሁሉ በእኔ
ይምላል ብዬ በራሴ ምያለሁ።” ኢሳ.45፡22-23
እግዚአብሔር ሁሉን ለማዳንና ወደራሱ ለመመለስ
ብቻ ሳይሆን፣ ሁሉን ይባርክ ዘንድ በራሱ ምሎአል። እርሱ በማይታጠፍ ቃሉ ይህን የማይሰበር ኪዳን ያደረገው
“የእምነት አባት” ከተባለው አብርሃም ጋር ነው። ይህ ኪዳን አይሰበርም፣ ከአፉም የወጣው ቃል ሳይፈጸም ወደእርሱ
አይመለስም። እርሱ ስሙ “ይሆዋ” ነው። የሰጠውን ተስፋ ይፈጽም ዘንድ የታመነ፣ ደግሞም ፈቃዱንና የወደደውን ሁሉ
ያደርግ ዘንድ እውቀት፣ ጥበብ፣ ማስተዋል፣ ጉልበት፣ ኃይልና ችሎታ ያለው ሕያውና እውነተኛ አምላክ!!!!!
“የእግዚአብሔርም መልአክ አብርሃምን ከሰማይ ሁለተኛ ጊዜ ጠራው እንዲህም አለው፡- እግዚአብሔር፡- በራሴ ማልሁ
ይላል፤ ይህን አድርገሃልና፣ አንድ ልጅህንም አልከለከልህምና በእውነት በረከትን እባርክሃለሁ፣ ዘርህንም እንደሰማይ
ከዋክብት በባህር ዳር እንዳለ አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳል፤ የምድር አሕዛብ ሁሉ በዘርህ
ይባረካሉ፣ ቃሌን ሰምተሃልና።” ዘፍ.22፡16-18
እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባህር ዳር እንዳለ
አሸዋ የሚበዛው፣ የጠላቶቹን ደጅ የሚወርሰውም ሆነ የምድር አሕዛብ ሁሉ የሚባረኩበት የአብርሃም ዘር አንድ ነው፤
እርሱም በመጽሐፍ “የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም” ተብሎ የተነገረለት የሕያው
እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ከሞት አስነስቶ በቀኙ ሲያስቀምጠው፣
በዚህ ዓለም (Gr. age) ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም ዓለም (Gr. age) ከሚጠሩት ስሞች ሁሉ በላይ የሆነ ስም ሰጥቶት
ነው። ይሄ ስም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ከሚጠሩት ስሞች ሁሉ በላይ የሆነ ብቻ ሳይሆን፣ በሰማይና በምድር
ከምድርም በታች ያለውን ፍጥረት ሁሉ ለእግዚአብሔር የመዋጀትና የማዳን ኃይልና ጉልበት ያለው ስም ነው። ሐዋርያው
ጳውሎስ ለፊሊጲስዩስ ክርስቲያኖች በጻፈው መልዕክቱ ውስጥ በግልጽ እንደተናገረው፤ በሰማይም ሆነ በምድር ከምድርም
በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከካሉ፣ ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ
ይመሰክራል።
“ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር፣ እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናል” (ሮሜ.10፡9-10)
ልብ በሉ!! ይህ ስም የሚጠራው በምድር ብቻ አይደለም፤ በላይ በሰማይም፣ከምድር በታችም ነው። ከምድር በታች ምን
አለ ይሆን??? ይህ ስም የሚጠራው በዚህ ዓለም ወይም በዚህ ዘመን ብቻ አይደለም፤ በሚመጡትም ዓለማትና ዘመናት
ጭምር እንጂ!!! አስተውሉ!!!! ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም የሚንበረከክ ጉልበት ያለው በምድር ብቻ አይደለም፤
በሰማይም፣ ከምድር በታችም ነው እንጂ!!! ከምድር በታች ምን ይኖር ይሆን??? እግዚአብሔር አብ ጌታ ኢየሱስ
ክርስቶስን ከሞት አስነስቶ “ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” ያለው፤ በቀደመው
ዘመን “ዘርህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳል” ብሎ ለአብርሃም የሰጠውን ተስፋ ሊፈጽም ነው።
እንዴ!!
“እግዚአብሔር” ብለን የምንጠራው አምላክ እኮ ስሙ “ይሆዋ” ነው። እርሱ የሰጠውን ተስፋ ይፈጽም ዘንድ የታመነ፣
ደግሞም ፈቃዱንና የወደደውን ሁሉ ያደርግ ዘንድ እውቀት፣ ጥበብ፣ ማስተዋል፣ ጉልበት፣ ኃይልና ችሎታ ያለው ሕያውና
እውነተኛ አምላክነው። ትዕቢቱ “እስከ ሰማይ ጥግ” የደረሰው ናቡክደናፆር፤ በሌላ ልብና በሌላ ሰውነት፣ ሰው
ከሚኖርበት ዓለም ተለይቶና፤ ጽድቅ በተትረፈረፈበት የእግዚአብሔር ፍርድ አማካኝነት ትህትናን ተላብሶ ፍጹም አዲስ
ሰው ከሆነ በኋላ የተናገረውን አድምጡ!! “በምድርም የሚኖሩ ሁሉ እንደምናምን ይቆጠራሉ፣ በሰማይም ሠራዊት በምድርም
ላይ በሚኖሩ መካከል እንደ ፈቃዱ ያደርጋል፣ እጁንም የሚከለክላት ወይም፡- ምን ታደርጋለህ? የሚለው ማንም
የለም።”
የእግዚአብሔር ኃይል ብዙ ሆኖ ሳለ የሚዋሹት ግን ጠላቶቹ ናቸው። በእርግጥም የሕያው
እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ በታች እስኪያደርግ ድረስ ይነግሣል። አለቅነትን፣
ኃይላትን፣ ስልጣናትን ሁሉ ይሽራል። “የመጨረሻ ጠላት” የተባለው ሞትም ከእግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ ላይ የሚወገደው
እርሱ “በማያልፍ ሕይወት ኃይል” በመልከ ፄዴቅ ሹመት የዘላለም ካህን በሆነበት ሰማያዊ አገልግሎቱ ነው።
ከእግዚእብሔር ፍጥረት ሁሉ ላይ ጠላትነትን አስወግዶ ሁሉ ከተገዛለት በኋላ እርሱ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ሲገዛ
እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆናል። ሁሉን የሚያድንበትና ሁሉን ወደራሱ የሚመልስበት ጥበብ፣ እውቀት፣ማስተዋል፣
ኃይልና ችሎታ ያለው በጉልበቱም ብርታት የሚራመደው ሕያው አምላክ እንዲህ ይላል፡- “በጽድቅ የምናገር ለማዳንም
የምበረታ እኔ ነኝ!!!!!!”
“የእግዚአብሔርም መልአክ አብርሃምን ከሰማይ ሁለተኛ ጊዜ ጠራው እንዲህም አለው፡- እግዚአብሔር፡- በራሴ ማልሁ ይላል፤ ይህን አድርገሃልና፣ አንድ ልጅህንም አልከለከልህምና በእውነት በረከትን እባርክሃለሁ፣ ዘርህንም እንደሰማይ ከዋክብት በባህር ዳር እንዳለ አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳል፤ የምድር አሕዛብ ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ፣ ቃሌን ሰምተሃልና።” ዘፍ.22፡16-18
እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባህር ዳር እንዳለ አሸዋ የሚበዛው፣ የጠላቶቹን ደጅ የሚወርሰውም ሆነ የምድር አሕዛብ ሁሉ የሚባረኩበት የአብርሃም ዘር አንድ ነው፤ እርሱም በመጽሐፍ “የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም” ተብሎ የተነገረለት የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ከሞት አስነስቶ በቀኙ ሲያስቀምጠው፣ በዚህ ዓለም (Gr. age) ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም ዓለም (Gr. age) ከሚጠሩት ስሞች ሁሉ በላይ የሆነ ስም ሰጥቶት ነው። ይሄ ስም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ከሚጠሩት ስሞች ሁሉ በላይ የሆነ ብቻ ሳይሆን፣ በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያለውን ፍጥረት ሁሉ ለእግዚአብሔር የመዋጀትና የማዳን ኃይልና ጉልበት ያለው ስም ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ ለፊሊጲስዩስ ክርስቲያኖች በጻፈው መልዕክቱ ውስጥ በግልጽ እንደተናገረው፤ በሰማይም ሆነ በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከካሉ፣ ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክራል።
“ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር፣ እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናል” (ሮሜ.10፡9-10)
ልብ በሉ!! ይህ ስም የሚጠራው በምድር ብቻ አይደለም፤ በላይ በሰማይም፣ከምድር በታችም ነው። ከምድር በታች ምን አለ ይሆን??? ይህ ስም የሚጠራው በዚህ ዓለም ወይም በዚህ ዘመን ብቻ አይደለም፤ በሚመጡትም ዓለማትና ዘመናት ጭምር እንጂ!!! አስተውሉ!!!! ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም የሚንበረከክ ጉልበት ያለው በምድር ብቻ አይደለም፤ በሰማይም፣ ከምድር በታችም ነው እንጂ!!! ከምድር በታች ምን ይኖር ይሆን??? እግዚአብሔር አብ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ከሞት አስነስቶ “ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” ያለው፤ በቀደመው ዘመን “ዘርህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳል” ብሎ ለአብርሃም የሰጠውን ተስፋ ሊፈጽም ነው።
እንዴ!! “እግዚአብሔር” ብለን የምንጠራው አምላክ እኮ ስሙ “ይሆዋ” ነው። እርሱ የሰጠውን ተስፋ ይፈጽም ዘንድ የታመነ፣ ደግሞም ፈቃዱንና የወደደውን ሁሉ ያደርግ ዘንድ እውቀት፣ ጥበብ፣ ማስተዋል፣ ጉልበት፣ ኃይልና ችሎታ ያለው ሕያውና እውነተኛ አምላክነው። ትዕቢቱ “እስከ ሰማይ ጥግ” የደረሰው ናቡክደናፆር፤ በሌላ ልብና በሌላ ሰውነት፣ ሰው ከሚኖርበት ዓለም ተለይቶና፤ ጽድቅ በተትረፈረፈበት የእግዚአብሔር ፍርድ አማካኝነት ትህትናን ተላብሶ ፍጹም አዲስ ሰው ከሆነ በኋላ የተናገረውን አድምጡ!! “በምድርም የሚኖሩ ሁሉ እንደምናምን ይቆጠራሉ፣ በሰማይም ሠራዊት በምድርም ላይ በሚኖሩ መካከል እንደ ፈቃዱ ያደርጋል፣ እጁንም የሚከለክላት ወይም፡- ምን ታደርጋለህ? የሚለው ማንም የለም።”
የእግዚአብሔር ኃይል ብዙ ሆኖ ሳለ የሚዋሹት ግን ጠላቶቹ ናቸው። በእርግጥም የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ በታች እስኪያደርግ ድረስ ይነግሣል። አለቅነትን፣ ኃይላትን፣ ስልጣናትን ሁሉ ይሽራል። “የመጨረሻ ጠላት” የተባለው ሞትም ከእግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ ላይ የሚወገደው እርሱ “በማያልፍ ሕይወት ኃይል” በመልከ ፄዴቅ ሹመት የዘላለም ካህን በሆነበት ሰማያዊ አገልግሎቱ ነው። ከእግዚእብሔር ፍጥረት ሁሉ ላይ ጠላትነትን አስወግዶ ሁሉ ከተገዛለት በኋላ እርሱ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ሲገዛ እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆናል። ሁሉን የሚያድንበትና ሁሉን ወደራሱ የሚመልስበት ጥበብ፣ እውቀት፣ማስተዋል፣ ኃይልና ችሎታ ያለው በጉልበቱም ብርታት የሚራመደው ሕያው አምላክ እንዲህ ይላል፡- “በጽድቅ የምናገር ለማዳንም የምበረታ እኔ ነኝ!!!!!!”
No comments:
Post a Comment