“የዘላለም ፍርድ” ትምሕርት “የመጀመሪያ”
ወይም መሠረታዊ ከሚባሉት የክርስትና ትምሕርቶች ውስጥ አንዱ ነው። ነገር ግን ስለዚህ “የመጀመሪያ” ስለተባለው ትምሕርት ዛሬ ያለው
መረዳትና አስተሳስብ ሐዋርያት የክርስትናን መሠረት በትምሕርታቸው በጣሉበት ዘመን ከነበረው ይዘትና መልክ በእጅጉ የተራራቀ ነው።
የሮማ ካቶሊክ ወንጌልን ለመስበክና ሰዎችን ወደ ክርስቶስ ለማምጣት ከተጠቀመችባቸው የሰው ብልሃቶች አንዱ አሕዛብ የየራሳቸውን ልምምድ ይዘው ወደ ቤተክርስቲያን እንዲገቡ
ማበረታታት ከመሆኑ በተጨማሪ፣ ሰዎች ክርስቲያን ካልሆኑ ፍጻሜ በሌለው የገሃነም እሳት እንደሚጠፉ ማስፈራራትም ነበር። ለዚህም
ነው በግሪኩ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውንና ቀጥተኛ ትርጉሙ “ዘመን/age” የሆነውን Aion የተባለውን አንዱን ቃል “Everlasting,
eternal. forever, forever and ever, world, world without end… በሚሉና የተለያየ ትርጉም ባላቸው
የእንግሊዝኛ ቃላት እንዲተኩ ተደርጎ፣ ሰዎች ስለ ዘላለም ፍርድ ያላቸው ግንዛቤ እንዲዛባ የተደረገው። ። እኛ ግን “የዘላለም ፍርድ” ማለት ምን ማለት እንደሆነ ጠልቀን ከመመርመራችን በፊት፣ ሁለቱን ቃሎች ለያይተን ብናጠናቸው በነገሩ ላይ የጠራ መረዳት እንዲኖረን ይረዳናል። ‘ዘላለም’ የሚለውንም ቃል ከማየታችን በፊት አስቀድመን ስለ እግዚአብሔር ፍርድ ብነንነጋገር ስለ ዘላለም ፍርድ የሚኖረን ግንዛቤ ይስተካከላል።
“በአሕዛብ መካከል እግዚአብሔር ነገሠ በሉ፤ እንዳይናወጥም ዓለሙን እርሱ አጸናው፣ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል። ሰማያት ደስ ይበላቸው፣ ምድርም ሐሴትን ታድርግ፣ ባሕርና ሞላዋ ይናወጡ፣ በረሃ በእርሷም ያሉ ሁሉ ሃሴትን ያድርጉ፣ የዱር ዛፎች ሁሉ በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይላቸዋል፤ ይመጣልና በምድርም ላይ ሊፈርድ ይመጣልና፤ እርሱም ዓለምን በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል።” (መዝ.96፡10-13)
‘ፍርድ’ ስለሚለው ቃል ስናስብ፣ ለዘመናት ከሰማነው የተዛባ መረዳት የተነሳ፤ ቶሎ ብሎ ወደ አእምሮአችን የሚመጣው፣ ማለቂያና ፍጻሜ የሌለው የእግዚአብሔር “የቁጣ እሳት” ወይም ደግሞ ብዙዎች ወደፊት ይሆን ዘንድ የሚጠብቁት “ያላመኑት ሁሉ በጅምላ ወደ ‘ዘላለማዊው’ የገሃነም እሳት” መጣላቸው ነው። ነገር ግን የእግዚአብሔር ፍርድ አሉታዊ ገጽታ እንዳለው ሁሉ አዎንታዊ ገጽታም ያለው እንደሆነ፣ ከዚህም በላይ ደግሞ እግዚአብሔር የሚፈርደው በጽድቅና በቅንነት እንዲሁም በዓላማ እንደሆነ ማወቁ በጣም አስፈላጊ ነው። ይህን አለማወቃችን ግን “አምላካችን” ነው ብለን የምንጠራው እግዚአብሔር በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ የአይሁድ ዘር የተባለውን ሁሉ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ቆርጦ በመነሳት በዓለም ታሪክ “አስከፊ” የተባለውን የጅምላ ጭፍጨፋ ካደረገው ሂትለር ጋር አንድ ይሆንብናል። ወይም ደግሞ የሥራ አርማቸውን የፍትህ - የትክክለኛ ፍርድ (Justice) መለያ ምልክት የሆነውን የሚዛን ምስል አድርገውና በማንም ላይ ምንም ዓይነት ብይን (Verdict) ከመስጠታቸው በፊት በብዙ ትዕግስትና ምርመራ የነገሩን ግራና ቀኝ፣ ፊትና ኋላ ካዩ በኋላ ለጥፋቱ ተገቢውን ቅጣት ከሚፈጽሙት የዚህ ዓለም ዳኞች ያንስብናል።
እግዚአብሔር ጻድቅ ፈራጅ ነው። ይህም ማለት ፍርዱ ይግባኝ የሌለው፣ ፍጹም ትክክልና ይህ ቀርቶታል የማይባል ነው። ነገር ግን እርሱ በኃጢአተኞችና በዓመጸኞች ላይ የሚፈርደው በንዴትና በብስጭት ተነሳስቶ ሳይሆን በጥበብና በማስተዋል ተሞልቶ ነው። በመሆኑም፣ ፍርዱ ዓላማና ግብ ያለው ከመሆኑ የተነሳ ውጢቱ የእርሱ መክበር ነው። የእግዚአብሔር ፍርድ ዓላማው “እርምት” (Correction) ነው። እስቲ አስቡት! ሁሉን ማድረግ የሚችል፣ “ህልቆ መሳፍርት” የሌለውን ዓለም በማይመረመር ጥበቡ የፈጠረ፣ ለእውቀቱና ለማስተዋሉ ወሰን የሌለው አምላክ፤..... ያለእርሱ ምንም ማድረግ የማይችሉትን ደካማ ፍጥረታቱን፣ የሰጣቸውን የሕይወት እስትንፋስ ወደራሱ ቢመልስና ቢሰበስብ በቅጽበት ዓይን “ወደ ምናምንነት” የሚለወጡትን የሰው ልጆች፣ በአንድ ወህኒ ውስጥ ዘግቶባቸው ለማይቆጠርና ፍጻሜ ለሌለው ዘመን በእሳት ጅራፍ ሲገርፋቸው ይኖራል??? አይባልም!!!! ይህ ማለት ግን እግዚአብሔር አይቀጣም፣ አይቆጣም፣ አይፈርድም….. ማለት ነው??? በጭራሽ!!!
ከእግዚአብሔር የፍርድ እጅ በታች መውደቅ እጅግ አስፈሪ ነው። እርሱ ከቅድስናው ክብር የተነሳ ኃጢአትን፣ ዓመጽንና ክፋትን ፈጽሞ ለማስወገድ ያለውን የማይለወጥ አቋሙን፣ ደግሞም የፍርዱን ጥልቀት - መጠንና ልኩን የገለጠው የልጁ የመስቀል ላይ ጣር ነው!!! ያኔ በቀራንዮው መስቀል ላይ ልጁ ስለ ሰዎች ሁሉ ከተቀበለው መከራና ፍዳ የተነሳ እግዚእብሔር ማንኛውም ሰው ከፍርድ በታች እንዲሆን ፈቃዱ አይደለም። ሁሉም በዚህ ሕይወት በሥጋ ሳሉ፣ በአንድያ ልጁ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በከፈተው የምሕረትና የጸጋ መንገድ ወደ ጽድቁና ወደ ቅድስናው ከፍታ እንዲደርሱ በጎ ፈቃዱ ነው። ከዘላለማዊ ሃሳቡ አንጻር ሲታይ ግን ይህ በዚህ ዘመንና ሕይወት ብቻ እንደማይሆንም የታወቀ ነው። ከዚህም የተነሳ በአንድም በሌላም መንገድ በዚህ ሕይወት ሳሉ የዚህ ጸጋ ተጠቃሚ ያልሆኑትን ከፍርድና ከኩነኔ በታች አድርጎ ሲቀጣ፤ “ፍቅር” የተባለው እግዚአብሔር ወደ “ጨካኝነትና አምባገነንነት” ተለውጦ አይደለም። አንዳንዶች እንደሚፈሩት የእግዚአብሔር ፍርድና ፍቅሩ ሁለት “የሚጋጩ” ባህሪያት አይደሉም። እርሱ ሲፈርድና ሲቀጣም፣ ሲራራና ሲምርም… ያው ፍቅር ነው። እግዚአብሔር እንደሰው ባይሆንም “ግራና ቀኝ እጆች” አሉት። “ግራ እጁን - The dark side of love ይሉታል። በሰው ልጆች እና በፍጥረቱ ሁሉ ላይ የሚፈርድበት፣ የሚቀጣበት፣ ገለባውን ከፍሬው የሚለይበት፣ ዝገቱንና ቆሻሻውን ሁሉ የሚያስወግድበት…. መለኮታዊ አሰራሩ ነው። (ይሄንን ጉዳይ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ “ፍጻሜ የሌለው ፍርድና ቅጣት፣ ሥቃይና መከራ... ከእግዚአብሔር ባህሪያት አንጻር እንዴት ይታያል??” የሚለውን ሃሳብ መመልከት ስንጀምር እንመለስበታለን።)
“ፍርድህን በምድር ላይ ባደረግህ ጊዜ በምድር ላይ የሚኖሩ ጽድቅን ይማራሉና…..” ኢሳ.26፡9
ይሄንን እውነት በሐይማኖት ቤት ከሚኖሩት ይልቅ በፍርድ ቤት አካባቢ የሚሰሩ ሰዎች ጠንቅቀው ያውቁታል። በአንድ ጉዳይ በተፈጸመ ወንጀልና ጥፋት ላይ ትክክለኛና ሚዛኑን የጠበቀ ፍርድ በመስጠት በምድር ላይ ያለውን የፍትህ ሥርዓት የሚጠብቁ የሕግ ባለሙያዎች፤ ጥፋተኝነቱ በተረጋገጠ አንድ ሰው ላይ እንደጥፋቱ ክብደትና ቅለት፣ “የአምስት፣ የአሥር፣ የአሥራ አምስት…. የዕድሜ ልክ ጽኑ እሥራት” እያሉ የቅጣት ፍርድ ሲወስኑ፤ በልባቸውና በሃሳባቸው ያለው ዋና ነገር - ግባቸውና ዓላማቸው፣ ያ ሰው በዚያ ጥፋት ዳግመኛ እንዳይገኝ ለእርሱም ሆነ ለሌሎች ትምሕርት መስጠት ነው። እንዲያውም ባለፈው ዓመት ከዚህ ዓለም ያለፉት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር በሐዘኑ ሰሞን ይወደሱ ከነበሩባቸው ጉዳዮች አንዱ፣ “እስር ቤቶችን ወደ ማረሚያ ቤትነት ለውጠዋል” የሚል ነው። ታድያ የዚህ ዓለም ሰዎች ይህን ጥበብ ከወዴት አመጡት???
እግዚአብሔርን ከዚህ ዓለም ሰዎች አሳንሰውና፣ በዓመጸኞችና በኃጢአተኞች ላይ የሚበይነው ፍርድና ቅጣት ምንም ውጤት የሌለውና “ዓላማ ቢስ” እንደሆነ አድርገው፡- “እርሱ እግዚአብሔር ያላመኑትን ወይም የምድርን ዓመጸኞችና ኃጢአተኞች ሁሉ ማለቂያና ፍጻሜ በሌለው ‘የዘላለም እሳት’ ይቀጣቸዋል” ብለው የሚያስተምሩ “ቲዮሎጂያንስ”፤ ወላጅ አባቶች ወይም እናቶች ናቸው። እነዚህ ወገኖች ከወለዷቸው ልጆቻቸው መካከል ዓመጸኞች አይጠፉም። እነርሱ “ዓመጸኛ” ልጆቻቸውን መልካም እንዲሆኑላቸው ለማድረግ የማይቆፍሩት ጉድጓድና “የማይበጥሱት ቅጠል” የለም። ስለነእርሱ ወደ እግዚአብሔር ከመማለድና ከመጸለይ ጀምሮ “አለ” የሚባለውን ብልሃት ሁሉ ያፈላልጋሉ። አንዳንድ የአባትነት ትዕግሥታቸውን መጠቀም ያልቻሉ ወላጆች፣ በቅጣት መልክ ወደ “ፀባይ ማረሚያ” ወይም “ግብረ ገብነትን” ወደሚያስተምሩና ሐይማኖት ቀመስ ወደሆኑ “አዳሪ” ትምሕርት ቤቶች በማስገባት ልጆቻቸውን ከፊታቸው ያርቃሉ። ምንም እንኳን ከፊታቸው ቢያርቋቸውም፣ ሲወጡና ሲገቡ፣ ሲበሉና ሲጠጡ፣ አንዳንዴም ከእንቅልፋቸው እየባነኑ ሳይቀር ስለእነርሱ ማሰባቸውን አያቋርጡም። በመጨረሻም እግዚአብሔር ረድቶአቸው ልጆቹ ወደሚፈለገው መልካምነት ሲመጡ ደስታቸው ፍጻሜ የለውም። ታድያ እነርሱ “ክፉዎች” ሆነው ሳሉ ስለልጆቻቸው ባህሪይ መለወጥ እንዲህ መጨነቅን ካወቁ “የሁሉ አባት” የተባለው የሰማይ አምላክ ደግሞ በእርሱ መልክና ምሳሌ ለፈጠራቸው የሰው ልጆች ሁሉ እንዴት ይበልጥ “አይጨነቅ!!!!”
እዚህ ላይ እስቲ ባለፈው ሰሞን “እግዚአብሔር ሥራውን ይመዝናል…” በሚል ርዕስ ስለ እግዚአብሔር ፍርድ ከጻፍኩት ጽሁፍ ላይ የትዕቢተኞች ሁሉ ዋና የነበረውን ንጉሥ፣ እግዚአብሔር ጥበብና ማስተዋል በተሞላበት ፍርዱ አማካኝነት እንዴት አድርጎ ትሁትና እግዚአብሔርን የሚያውቅ፣ የሚያከብርና የሚያመልክ ስብዕና እንዳለበሰው የሚናገረውን ክፍል እንደገና እንመልከተው፡-
“የሰው ልጆች፣ በተለይም ሐይማኖተኞች ስለ እግዚአብሔር ፍርድ ሲያስቡ ቶሎ ብሎ ወደልባቸው የሚገባው ማለቂያና ፍጻሜ የሌለው የእግዚአሔር ቁጣና ጭካኔው እንጂ፣ ጽድቅ በተትረፈረፈበት ፍርዱ ውስጥ የሚያገኝው ክብርና በትዕቢተኞችና በዐመፀኞች ሕይወት ውስጥ የሚያመጣው የከበረ የማንነትና የሕይወት ለውጥ አይደለም። የዚህ ስህተት መነሻና ምንጩ ደግሞ ከሰባኪዎቻቸው የሚሰሙት ቅጥ የሌለው ዛቻና ማሰፈራሪያ ነው። ከእግዚአብሔር የፍርድ እጅ በታች የመውደቅን አስፈሪነትም ሆነ ከዚህ ክቡር እጅ በታች ከወደቁ በህዋላ የሚገኘውን የሕይወት ለውጥ ሊናገር የሚችል እንደናቡከደናፆር ያለ ሰው ማንም የለም። ለሰባት ዘመን (የዘመኑ ቁጥር ፍጹሙን የእግዚአብሔር አሰራር ያሳየናል) የቆየው የእግዚአብሔር ፍርድ አዲሱን ናቡከደነፆር እንዲህ ይገልፀዋል፡-
“ዘመኑም ከተፈጸመ በህዋላ እኔ ናቡከደነፆር ዓይኔን ወደሰማይ አነሳሁ፣ አእምሮዬም ተመለሰልኝ፣ ልዑሉንም ባረክሁ፣ ለዘላለም የሚኖረውን አመሰገንሁ፣ አከበርሁትም፣ ግዛቱ የዘላለም ግዛት ነውና። በምድርም የሚኖሩ ሁሉ እንደምናምን ይቆጠራሉ፣ በሰማይም በሚኖሩ መካከል እንደ ፈቃዱ ያደርጋል፣ እጁንም የሚከለክላት ወይም፡- ምን ታደርጋለህ የሚለው የለም። በዚያን ጊዜም አእምሮዬ ተመለሰልኝ፣ ለመንግሥቴም ክብር ግርማዬና ውበቴ ወደ እኔ ተመለሰ፣ አማካሪዎቼና መክዋንንቶቼም ፈለጉኝ፣ በመንግሥቴም ውስጥ ጸናሁ፣ ብዙም ክብር ተጨመረልኝ። አሁንም እኔ ናቡከደነፆር የሰማይን ንጉሥ አመሰግናለሁ፣ ታላቅም አደርገዋለሁ፣ አከበረውማለሁ። ሥራው ሁሉ እውነት፣ መንገዱም ፍርድ ነውና፣ በትዕቢትም የሚሄዱትን ያዋርድ ዘንድ ይችላልና።” (ዳን.4፡34-37)
ከሰባቱ ዘመን ፍርድ በህዋላ የተገኘው ናቡከደነፆር ይሄ ነው። ልዑሉ በሰዎች መንግሥት ላይ የሚሰለጥን፣ መንግሥትንም ለሚወደው የሚሰጥ፣ ግዛቱም የዘላለም ግዛት የሆነ፣ በሰማይና በምድር መካከል እንደ ፈቃዱ የሚያደርግ፣ ትዕቢተኞችን የሚያዋርድ፣ ለትሁታኑ ፀጋን የሚሰጥ አምላክ መሆኑን የሚያውቅ ናቡከደነፆር!! እግዚአብሔርን የሚያመልክ፣ የሚያከብርና የሚያመሰግን ናቡከደነፆር!! አዲሰ ልብና አዲስ አእምሮ ከውበት ከመንግሥት ክብርና ግርማ ጋር የተመለሱለት ናቡከደነፆር!! እጅግ በጣም የሚገርመው ነገር ግን እንዲህ አይነቱ ሰው የተገኘው “የእግዚአብሔር ሕዝብ” ተብለው ከሚጠሩት እሥራኤላውያን መካከል አልነበረም!!!”
“ፍርድህን በምድር ላይ ባደረግህ ጊዜ በምድር ላይ የሚኖሩ ጽድቅን ይማራሉና…..”

No comments:
Post a Comment