እግዚአብሔር በአንድያ ልጁ ወደ ምድር ወረደ - ብዙ ልጆችንም ይዞ ወደ ሰማይ አረገ!!!
“የእግዚአብሔር እድል ፈንታ ሕዝቡ ነው፤ ያዕቆብም የርስቱ ገመድ ነው። በምድረ በዳ በጥማት፣ የነፋስ ጩኸትም በሞላበት ውድማ አገኘው፤ ከበበው ተጠነቀቀለትም፤ እንደ አይን ብሌን ጠበቀው። ንስር ጫጩቶቹን እንደሚያወጣ፣ በእነርሱም ላይ እንደሚሰፍፍ፣ ክንፎቹን ዘርግቶ ወሰዳቸው፣ በክንፎቹም አዘላቸው። እግዚአብሔር ብቻውን መራው፤ ከእርሱም ጋር ሌላ አምላክ አልነበረም።” (ዘዳግም.32፡9-12)
በቀደመው ዘመን በግብጽ ምድር የነበረውን የሕዝቡን መከራ በእውነት ያየ፣ ጩኸታቸውንም የሰማና ሥቃያቸውንም ያወቀ እግዚአብሔር፣ … የባርነት ቀንበራቸውን ሰብሮ ከግብፃውያን እጅ ያድናቸው ዘንድ፣ ከጠላት እጅ አምልጠውና ከመከራቸው አርፈው በተትረፈረፈ በረከት ወደሚኖሩበት - ወተትና ማር ወደምታፈሰው፣ ወደ ሰፊይቱና ወደ መልካሚቱ ምድር የሚወስዳቸውን መንገድ ይመራቸው ዘንድ ወረደ። (ዘፀአት3፡8) …. እስቲ እዚህ ላይ አንዲት ጥያቄ እንጠይቅ፡- የሕዝቡን መከራ በእውነት ያየ፣ ጩኸታቸውንም የሰማ፣ ሥቃያቸውንም ያወቀ እግዚአብሔር እንዴት ወደ ግብጽ ወረደ???
“አሁንም ና፣ ሕዝቤን የእሥራኤል ልጆች ከግብጽ ታወጣ ዘንድ ወደ ፈርዖን እልክሃለሁ። ሙሴም እግዚአብሔርን፡- ወደ ፈርዖን የምሄድ የእሥራኤልንም ልጆች ከግብጽ የማወጣ እኔ ማን ነኝ? አለው። እርሱም፡- በእውነት እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔም እንደላክሁህ ምልክትህ ይህ ነው፤ ሕዝቡን ከግብጽ ባወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ ለእግዚአብሔር ትገዛላችሁ አለ።” (ዘፀአት3፡ 10-12)
በግብጽ ምድር ሳለ በወንድሞቹ ላይ የደረሰውን መከራ ተመልክቶ ጥቃታቸውን ለመከላከል የገዛ ጉልበቱንና ብርታቱን በመጠቀም ግብፃዊውን የገደለው ሙሴ፤ ከፈርዖን ፊት ኮብልሎና እጅግ ትሁት ሆኖ የአማቱን የዮቶርን በጎች በሚጠብቅበት በምድያም ምድር ነበር እግዚአብሔር ለዚህ የከበረ ተልዕኮ የጠራው። በግብጽ ሳለ የነበረው ጉልበቱና ብርታቱ አሁን የለም። ስለዚህም፡- ወንድሞቹን ከግብጽ ያወጣ ዘንድ እግዚአብሔር በእርሱ እጅግ የላቀውን ኃይልና ብርታቱን ሊገልጥ ትክክለኛው ጊዜ ደርሶ ወደፈርዖን ሊልከው እንዳሰበ ሲነግረው “የእሥራኤልን ልጆች ከግብጽ የማወጣ እኔ ማን ነኝ??” ብሎ ነበር እግዚአብሔርን የጠየቀው። የአባቶቹ የአብርሐም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክም፡- “በእውነት እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ” አለው። የሕዝቡን መከራ ያየ፣ ጩኸታቸውንም የሰማ፣ ሥቃያቸውንም ያወቀ እግዚአብሔር፣ በጸናችና በበረታች ክንድ የባርነት ቀንበራቸውን ሰብሮ ከፈርዖን አገዛዝ ነጻ ያወጣቸው ዘንድ፣…. ሙሴን ላከው፣ የእሥራኤል ቅዱስ በሙሴ ወረደ!!!!!
“የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፣ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፣ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፣ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል። የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት አምላካችንም የሚበቀልበትን እናገር ዘንድ፣ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ፣…. ልኮኛል።” (ኢሳ.61፡1-3)
“ጴጥሮስም አፉን ከፍቶ እንዲህ አለ፡- እግዚአብሔር ለሰው ፊት እንዳያደላ ነገር ግን በአሕዛብ ሁሉ እርሱን የሚፈራና ጽድቅን የሚያደርግ በእርሱ የተወደደ እንደሆነ በእውነት አስተዋልሁ። የሁሉ ጌታ በሚሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እየሰበከ ይህን ቃል ወደ እስራኤል ልጆች ላከ። ዮሐንስ ከሰበከው ጥምቀት በኋላ ከገሊላ ጀምሮ በይሁዳ የሆነውን ነገር እናንተ ታውቃላችሁ። እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፣ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስ የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፣ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረና።” (ሥራ፣10፡34-38)
በአዳም ከሆነው በደልና መተላለፍ የተነሳ፣ በዚህ ክፉ ዓለም ውስጥ ከዲያብሎስና ከገዛ ሥጋቸው ቀንበር ሥር ሆነው በኃጢአትና በሞት የሚሰቃዩትን የሰው ልጆች መከራ ያየ እግዚአብሔር፣ ከዚህ ጽኑ እሥራትና መከራ ነጻ ያወጣቸው ዘንድ፣ በእርሱ መልክ ይኖር የነበረውንና እጅግ የሚወደውን አንድያ ልጁን የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት አካባቢ ወደዚህ ምድር ላከው። ሁሉን ወራሽ ያደረገውና ዓለማትን የፈጠረበት ይህ አንድያ የእግዚአብሔር ልጅ ወደዚህ ምድር የመጣው፣ ቀድሞ በአባቱ ዘንድ በነበረው ክብር ሳይሆን፣ ስለ አባቱ ፈቃድ ሲል እጅግ ትሁት በመሆን ራሱን ባዶ አድርጎና ፍጹም ሰው ሆኖ ነበር። ለዚህም ነው በእግዚአብሔር ለተላከበት - ነፍሱን ስለሰው ልጆች ኃጢአት ቤዛ አድርጎ የመስጠትና ሰዎችን ሁሉ ከዲያብሎስ እሥራት ነጻ አውጥቶ ወደ እግዚአብሔር ክብር የመመለስ ዓላማ ብቁ ይሆን ዘንድ ፤ በሰላሳ ሶስት ዓመቱ በአጥማቂው ዮሃንስ እጅ ሲጠመቅ በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም የተቀባው።
የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ለ33 ½ ዓመታት በምድር ላይ ስለነበረው ቆይታ እጅግ በተለየና ጥልቅ በሆነ መንገድ የጻፈው “ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር” ዮሐንስ ነው። ከዚህ በታች የተጠቀሱት የክርስቶስ የራሱ ቃላት ከዚሁ ወንጌል የተወሰዱ ናቸው።
“…..ነፍሴን ደግሞ አነሳት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል። እኔ በፈቃዴ አኖራታልሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሳት ሥልጣን አለኝ፤ ይህችን ትዕዛዝ ከአባቴ ተቀበልኩ።…… እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፣ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።….. እኔ ስለራሴ ምንም እንኳ ብመሰክር ከወዴት እንደመጣሁ ወዴትም እንድሄድ አውቃለሁና ምስክርነቴ እውነት ነው…. የላከኝ አብ ከእኔ ጋር ነው እንጂ ብቻዬን አይደለሁምና እኔ ብፈርድ ፍርዴ እውነት ነው።….. በእኔ የሚያምን በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በእኔ አይደለም፣ እኔን የሚያይ የላከኝን ያያል። በእኔ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር እኔ ብርሐን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቼአለሁ።…. እኔ ከራሴ አልተናገርኩምና ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትዕዛዝ ሰጠኝ። ትዕዛዙም የዘላለም ሕይወት እንደሆነች አውቃለሁ። ስለዚህ እኔ የምናገረውን አብ እንደነገረኝ እንዲሁ እናገራለሁ።….. እኔን ያየ አብን አይቶአል…. እኔ የምናገረው ቃል ከራሴ አልናገረውም፣ ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል። እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፣ ባይሆንስ ስለራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ። …… እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።”
በግብጽ ምድር የነበረውን ጩኸት ሰምቶ ሕዝቡን ከባርነት ቀንበር ነጻ ለማውጣት በሙሴ ወርዶ የነበረው እግዚአብሔር፤ ከዘላለም ዘመናት በፊት ያቀደውን ሰዎችን ሁሉ የማዳንና ወደክብሩ የመመለስ ዓላማ ይፈጽም ዘንድ፣ መንፈስ የሆነውና “የማይታይ አምላክ” የተባለው እግዚአብሔር በአንድያ ልጁ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ወደዚህ ምድር ወረደ። “እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ…. “ በማለት ሐዋርያው ጳውሎስ የተናገረውም ይህንን እውነት ነው። ሙሴ በቀደመው የእግዚአብሔር ሃሳብ ላይ የሰለጠነውና የታመነው “እንደ ሎሌ” ነበር። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የሁሉ ወራሽ፣ የሁሉም ጌታ ነውና እርሱ የእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ ላይ እንደ ልጅ የታመነ ነው። ስለዚህም እግዚአብሔር በልጁ ይፈጽመው ዘንድ ያሰበውን ፈቃዱን ለማድረግ ከእርሱ ጋር (WITH Him) ነበረና “የላከኝ አብ ከእኔ ጋር ነው” አለ። ደግሞም አብ በእርሱ (IN Him) እርሱም በአባቱ ነበረና፡- “እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ” በማለት መሰከረ። ስለዚህም የዘመናት ሃሳቡን ይፈጽም ዘንድ በልጁ ሆኖ ወደምድር የወረደው እግዚአብሔር፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ያደርግ ዘንድ የወደደውን ፈቃዱን ሁሉ ከፈጸመ በሁዋላ፣ ከሙታን ባስነሳው ከልጁ ጋር በልጁም ሆኖ አረገ - በክብር ከፍ ከፍ አለ።
“አምላክ (Elohim) በእልልታ፣ እግዚአብሔር (Jehovah) በመለከት ድምጽ አረገ።” (መዝ.47፡5)
በዚህ የቆሬ ልጆች መዝሙር የተገለጠው ጥልቅ የመለኮት ሃሳብ ይህን መልእክት ለሚያነቡ ሁሉ የተገለጠ እንዲሆን ጸሎቴ ነው። በዚህ መዝሙር ላይ የምናገኛቸው ሁለት ስሞች እንዲሁ ተለያይተው የተቀመጡ አይደሉም። በአማርኛችን “አምላክ” ተብሎ የተጠቀሰው ቃል የሒብሪው አቻው “ኤሎሂም” ተብሎ የሚታወቀውና በትክክል ወደ አማርኛችን ብንመልሰው “አምላክ” ከሚለው የነጠላ መጠሪያ ስም ይልቅ “አማልክት” የሚለውን ከአንድ በላይ ለሆኑ አካላት የምንጠቀምበትን ቃል ይሰጠናል። ይህን ለመረዳት አንድ ምሳሌ እንውሰድ፡- ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ “የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ” በማለቱ ከአይሁድ ለደረሰበት ተቃውሞ፡- “መጽሐፉ ሊሻር አይችልምና እነዚያን የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት (ኤሎሂም) ካላቸው፣ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ስላልሁ እናንተ አብ የቀደሰውን ወደ ዓለምም የላከውን፡- ትሳደባለህ ትሉታላችሁን?” በማለት የሰጠው መልስ ቀድሞ በመጽሐፋቸው እንዲህ ተብሎ የተጻፈውን በመጥቀስ ነበር፡-
“እግዚአብሔር በአማልክት (ሒብሪው ‘ኤል’ - ኃያላን) መካከል ቆመ፣ በአማልክትም (ኤሎሂም) መካከል ይፈርዳል።……. አኔ ግን፡- አማልክት (ኤሎሂም) ናችሁ፣ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ፤ ነገር ግን እንደ ሰው ትሞታላችሁ፣ ከአለቆችም እንደ አንዱ ትወድቃላችሁ አልሁ። God standeth in the congregation of the mighty; he judgeth among the gods…. I have said, Ye are gods; and all of you are children of the most High. KJV (መዝ.82፡1 -6)
እንግዲህ በመለከት ድምጽ ከእግዚአብሔር(Jehovah) ጋር ያረጉት አማልክት(Elohim) የልዑል ልጆች ሁሉ ሲሆኑ፣ በእነዚህ ልጆች መካከል ቀዳሚና ራስ የሆነው ግን “ከሙታንም በኩር” የተባለው የሕያው እግዚአብሔር አንድያ ልጅ ጌታ ኢያሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ “የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ” ነው። ጌቶችና ነገሥታት የተባሉት፣ መከራውን የተካፈሉና ከእርሱ ጋር አብረው የሚንግሡት “የልዑል ልጆች” እንደሆኑ ያስተዋልን ስንቶች እንሆን??? እርሱ በነዚህ ብዙ ወንድሞቹ መካከል በኩር ሆኖ የቤተ ክርስቲያን ማለትም የአካሉ ራስ ሲሆን፣ እግዚአብሔርም “የክርስቶስ ራስ” እንደሆነ በመጽሐፋችን በግልጽ የተጻፈ ነው። (1ቆሮ.11፡3) እግዚአብሔር ክርስቶስን ከሙታን ሲያስነሳውና በቀኙ ሲያስቀምጠው፣ ከእርሱ ጋር አብሮ ያስነሳቸውና በሰማያዊም ስፍራ ከክርስቶስ ጋር ያስቀመጣቸው ብዙ ልጆች እንዳሉ ሐዋርያው ጳውሎስ ለኤፌሶን ቅዱሳን በጻፈው መልእክቱ ውስጥ እንዲህ ገልጦታል፡-
“ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለጠጋ ስለሆነ፣ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፤ በጸጋ ድናችሗልና፣ በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለጠግነት ያሳይ ዘንድ፣ ከእርሱ ጋር አስነሳን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን” (ኤ.ፌ.2፡4-7)
የክብር አባት፣ የጌታችንም የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ፣ በልጁም በኩል የገለጠውን ዘላለማዊ ሃሳቡንም ለመረዳት እንድትችሉ የጥበብና የመገለጥን መንፈስ እንዲስጣችሁ እለምናለሁ። በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን!!!!

No comments:
Post a Comment