"ልጆች ሆይ ኃጢአታችሁ ስለስሙ ተሰርዮላችኋልና ይህን እጽፍላችኋለሁ: አባቶች ሆይ ከመጀመሪያ የነበረውን
አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ: ጎበዞች ሆይ ክፉውን አሸንፋችኋልና እጽፍላችኋለሁ..." 1ዮሓ 2:12-13
በእግዚአብሔር ዘላለማዊ እቅድና ሓሳብ መሰረት በፍጥረታዊው አለም መገኘታችንና በዚህም ዓለም ያለውን ፍጥረታዊ ህይወት መለማመዳችን (ፍጥረታዊው ሕይወት ኃጢአትና አመጽ የሞላበት የጨለማ ሕይወት እንዳልሆነ ልብ ይሏል) ወደ መንፈሳዊውና ሰማያዊው ሕይወት ለመድረስ ለምናደርገው መንፈሳዊ ጉዞ እንደ ምሳሌና ማስረጃ ነው:: አንድ ሰው - ሙሉ ሰው ሆኖ በዚህ ምድር ላይ መንቀሳቀስ ከመጀመሩ በፊት የአባቱ ዘርና የእናቱ እንቁላል በእናቱ ማሕጸን ውስጥ ከተገናኙ በሗላ የሚከናወነው የጽንስ ሂደት ደግሞም መወለዱና ማደጉ የሚነግሩንና የሚያስተምሩን የጠለቀ መንፈሳዊ እውነታ አለ::
=>"ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም; በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ::" (1ጴጥ.1:23);
=>"ለፍጥረቱ የበኩራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን" (ያዕ1:18)
=>"ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው, እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከስጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም::" (ዮሓ1:12-13)
=>"ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል:" (1ዮሓ5:1)
በነዚህ የተባረኩ ሐዋርያዊ ትምህርቶች መሰረት, ወደዚህ ፍጥረታዊ ዓለም ከሥጋና ከደም የተወለደ አንድ ሰው፣ ወደመንፈሳዊው ዓለም - ከእግዚአብሔርዳግመኛ ይወለድ ዘንድ አስፈላጊና መሰረታዊ የሆኑ ሁለት "ነገሮችን" እናገኛለን:: "የማይጠፋው ዘር"የተባለው የእግዚአብሔር ቃልና እና እምነት:: "እምነት ከመስማት - መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው፣" በመንፈስ የሚገለገለውንና "የመዳናችሁ ወንጌል" የተባለውን "የእውነት ቃል" በእምነት መቀበላችን ነው ከእግዚአብሐር ዳግመኛ የሚወልደን:: የዚህን ህያው እውነት መሰረት የምናገኘው ደግሞ የእምነት አባት ከተባለው አብርሃምና ትውልድ ሁሉ ብጽዕናዋን ከሚመሰክርላት ድንግሊቱ ማርያም ሕይወት ነው::
የሣራ ማህጸን ደርቋል; የእርሱም ጉልበት ደክሟል:: ነገር ግን አብርሃም, የተሰጠውን ተስፋ, የመጣለትንም የእግዚአብሐር ቃል በእምነት ይዞ ሲበረታ በራዕይ የመጣለትና "ወደ ሰማይ ተመልከት ከዋክብትንም ልትቆጥራቸው ትችል እንደሆነ ቁጠር - ዘርህም እንዲህ ይሆናል::" የሚለው የእግዚአብሔር ቃል ሥጋ ሆነ!! የተጠበቀውም የተስፋው ዘር ተወለደ::
ለአንድ ወንድ ታጨች እንጂ ወንድ ፈጽሞ አልደረሰባትም: ማሕጸኗም አልተከፈተም - ድንግል ነች:: ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርስዋ ገብቶ "ማርያም ሆይ, በእግዚአብሔር ፊት ጸጋን አግኝተሻልና አትፍሪ:: እነሆም ትጸንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ..." የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል አመጣላት:: አንድ ጥያቄ ነው የጠየቀችው: "ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል?" "መንፈስ ቅዱስ ባንቺ ላይ ይመጣል, የልኡሉም ኃይል ይጸልልሻል.." የመልአኩ መልስ ነበር:: ከዚያም "እነሆኝ የጌታ ባርያ እንደቃልህ ይሁንልኝ" ብላ የመጣላትን ቃል በእምነት ስትቀበል ለዘመናት ሲጠበቅ የነበረው የተስፋው ዘር, አለማት የተፈጠሩበት የእግዚአብሔር ቃል በድንግሊቱ ማሕጸን ውስጥ ሥጋ ሆነ- ጊዜውም ሲደርስ አዳኙ ተወለደ::
በዓለም ሁሉ - በዘመናት መካከል የሚሰበከውና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሚገለገለው የመዳናችን ወንጌል የሆነው ክርስቶስ - የእግዚአብሔር ቃል - ዘር ነው:: እርሱ ኃጢአታችንን በደሙ ያነጻ በሞቱም ከአብ ጋር ያስታረቀን በትንሳኤውም የሞትን መውጊያ የሰበረ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ የሚሰበከውን የወንጌል ቃል በእምነት በተቀበልን ጊዜ በመንፈሳችን ማሕጸን ተዘርቶ በመለኮት ጥበብና እውቀት አዲስና መንፈሳዊ ሰው አድርጎ ይወልደናል:: የሰማነውን የእውነት ቃል በእምነት በተቀበልን ጊዜ በአዲስ ልደት የእግዚአብሔር ልጆች እንሆናለን:: ለዚህም ነው ሓዋርያው ጴጥሮስ "እንግዲህ ክፋትን ሁሉ ተንኮልንም ሁሉ ግብዝነትንም ቅናዓትንም ሓሜትንም አስወግዳችሁ, ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደሆነ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደተወለዱ ሕጻናት ተንኮል የሌለበትን የቃሉን ወተት the pure milk of the word ተመኙ::" የሚለን:: (1ጴጥ1:1-3)
በመንፈሳዊው ሕይወት ይህ የመጀመርያው የእድገት ደረጃችን ሲሆን, በዚህ ጊዜ አዲስ የተወለዱ ሕጻናት ፍቅርን, እንክብካቤንና ጥንቃቄን እንደሚሹ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የመዳናቸውን ወንጌል ሰምተውና የሕያው እግዚአብሔር ልጅ የሆነውን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኛቸውና ጌታቸው አድርገው የተቀበሉ አዳዲስ ክርስቲያኖችም የሚያስፈልጋቸው ይኽው ጥንቃቄና እንክብካቤ ነው:: ለዚህም ነው ሓዋርያው ዮሃንስ "ትልቁ የበጎች እረኛ" ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መንጋውን በሦስት የመንፈሳዊ እድሜ ደረጃ ከፍሎ እንደሰጣቸው እንዲሁ "ልጆች፣ጎበዞች፣ አባቶች" እያለና የመልእከቱንም ጭብጥ በሶሶት ደረጃዎች ከፍሎ ሲጽፍ የምናገኘው:: "ልጆች ሆይ ኃጢአታችሁ ስለስሙ ተሰርዮላችኋልና እጽፍላችኋለሁ!!!" (የሚቀጥል)

No comments:
Post a Comment